Sunday, November 23, 2014

መልካምና ክፉ ልጅ


   በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ሜን!


ልጅህ፥ ክፉ ከሆነ፦

* እንደ ቃየል በቅናት ካደገ የገዛ ወንድሙን ይገድላል። (ዘፍ ፬፥፭)

* እንደ ካም ካደገ ያንተኑ ሃፍረት ይገልጥብሃል። (ዘፍ ፱፥፳፩-፳፪)

* እንደ ዲና ካደገች ሂዳ ከጠላቶችህ ትወዳጃለች። (ዘፍ ፴፬፥፩)

* እንደ ዔሳው ካደገ ምቀኛ ይሆንብሃል። (ዘፍ ፲፯፥፵፩-፵፭)

* እንደ ይሁዳ ልጆች ካደገ የከፋ ይሆንብሃል። (ዘፍ ፴፰፥፩-፲፩)

* እንደ ሮቤል ካደገ ሚስትህን ይቀማሃል። (ኩፍ ፳፰፥፴፭-፵፬)

* እንደ አፍኒንና ፊንሐስ ካደገ ታቦት ሻጭ ይሆንብሃል። (፩ኛ ሳሙ፪፥፲፪)

* እንደ አምኖን ከደገ የገዛ ኅህቱን ይደፍርብሃል። /፪ኛ ሳሙ ፲፫፥፩-፲፱)

* አንደ አቤሴሎም ካደገ አንተንም ያሳድድሃል። (፪ኛ ሳሙ ፲፯፥፳፩-፳፬)

ልጅህ፥ መልካም ከሆነ፦ 

* አንደ ሴምና ያፌት ካደገ ሃፍረትህን ይደብቅልሃል። (ዘፍ ፱፥፳፫)

* አንደ ዮሴፍ ካደገ በችግርህ ደራሽ ይሆንልሃል። (ዘፍ ፴፱፥፯-፳፫)

* እንደ ይስሐቅ ካደገ ታማኝ ሆኖ ራሱን ይሰዋል። (ዘፍ ፳፪፥፱)

* እንደ ሳሙኤል ካደገ የእግዚአብሔር ሰው ይሆንልሃል። /፩ኛ ሳሙ ፫፥፲፯-)

* እንደ ዳዊት ካደገ የአገርህን ጠላት ያጠፋልሃል፤ በሰውም በእግዚአብሔር ፊት የተወደደ ይሆንልሃል። /፩ኛ ሳሙ ፲፯፥፴፬-፶፬)

"ልጆች ኖሩህ (በክርስቶስ ፍቅር) ምከራቸው፤ ከሕፃንነታቸው ጀምረህ ትሕትናን አስተምራቸው።" (ሲራ ፯፥፳፫)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ ክብር ለድንግል ማርያም!

ምንጭ፦ ዛክ ኢትዮጵያ

No comments:

Post a Comment