Monday, May 4, 2015

ጀማል ማነው? ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት


ኤፍሬምና ጓደኞቹ

ጀማልየተባለ ሙስሊም ወንድማችን በሊቢያ ከተሠዉ ክርስቲያኖች ጋር አብሮ ተሠዉቷል እየተባለ ሲነገር ቆይቷልበአካባቢው የነበሩ የዓይን እማኞችና ሌሎችም የቅርብ ምንጮች ታሪኩ የተሳሳተ መሆኑን ቢናገሩም ሰሚ ለማግኘት ግን አልተቻለም፡፡ አንዳንዶቹም ታሪኩን የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች ፍቅር ማሳያ አድርገው ተሟግተዋል፡፡ እንደ እኔ ግን ይህንን ታላቅ ፍቅር ለማሳየትጀማልየተባለ መሥዋዕት መፍጠር አያስፈልገንም፡፡ ፍቅሩ ነበረ፤ አለ፡፡ ተጨማሪ ፈጠራው አያስፈልገውም ነበር፡፡

ኤፍሬም ሰማዕት ዘሊቢያ
ጀማልነው ተብሎ ሲነገርለት የነበረው ወንድማችን ግን ኤፍሬም የተባለ ኤርትራዊ፣ ቃኘው ሠፈር ይኖር የነበረ ክርስቲያን ነው፡፡ ቤተሰቦቹ ሁለት መርዶ እንደመጣባቸው እየገለጡ ነው፡፡ በአንድ በኩል በአሰቃቂ ሁኔታ በአይሲስ መሠዋቱ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞሙስሊምነው መባሉ ነው፡፡

      ኖርዌይ የነበሩ ኤርትራውያን ክርስቲያኖች ወዲያው ነበር ነገሩን የተቃወሙት፡፡ ነገር ግን አሥመራ ያሉት ቤተሰቦቹ እስኪረዱ ድረስ ትክክለኛ ስሙን ለመግለጥ አልተፈለገም፡፡ በዚህ መዘግየት የተነሣም ብዙ የፈጠራ ታሪኮች ተፈጠሩ፡፡

አንዳንድ የማኅበራዊ ሚዲያ አቀንቃኞች በላኩልኝ የውስጥ መልእክት የጀማልን ሙስሊምነት መካድ ሙስሊሞች ለክርስቲያኖች ያላቸውን ድጋፍና ፍቅር መካድ ነው ሲሉ ገልጠዋል፡፡ ለእኔ ግን ከተፈጠረውጀማልይልቅ እዚሁ አዲስ አበባ ያለው መሐመድ ካሣ ይህንን ልዩ ፍቅር ከንጋት ኮከብ በላይ አጉልቶ አሳይቶኛል፡፡ ልቡ እስኪደክም ኀዘንተኞቹን ለማጽናናትና ለመርዳት የሚደክመው፤ ለምን ጉባኤ አይደረግም፣ መዘምራን ለምን አይመጡም፣ መምህራን ለምን አያስተምሩም እያለ ልቅሶ ቤቶቹን ከክርስቲያኖቹ በላይ ሲያገለግል የነበረው፤ ተዝካራቸው መውጣት አለበት ብሎ ከካህናቱ ጋር የሚሟገተው፣ ድንበር ተሻጋሪውና ድልድይ ገንቢው መሐመድ ካሣ ለኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች ፍቅር ከበቂ በላይ ማሳያዬ ነው፡፡

ያየሁት፣ የነካሁት፣ የበለጠኝ ማስረጃዬ፤ ፈጠራ አያስፈልገኝም።

ኤፍሬም ሆይ በረከትህ ይደርብን።

 ------------------------------------------- / / / --------------------------------------------


በተጨማሪም፦ እንደ እኔ፣ እንደ እኔ እምነት ሠውን በሠውነቱ እናክብረው፤ ሃይማኖት የሠማያዊ መንገድ ጉዞ ነው። ይኼ ጉዞም፥ ፍቅር፣ ቅንነትና ቸርነት፣ የዋህነት፣ ገርነት፤ በራስህ ላይ ሊደርስ የማትፈልገውን ነገር በሠዎች ላይ አለማድረግ ነው።
 
ለዚህም ነው መልካምነትን ስለተመኙ አንዳንድ ሙስሊምና ክርስቲያን ወንድሞቹና ህኅቶች ባልታወቀ መረጃና ማስረጃ ስለ "ጀማል" ሙስሊምነቱ፣ ስለ ሰማዕታት ጓደኞቹ የሃይማኖት ጽናት ሲል እራሱን አሳልፎ የሰጠ የሙስሊም ጀግና ተብሎ፥ ስለ "ጀማል" ጽናቱና ስለ ጀግንነቱ ብዙ ብዙ ተብሎለታል፣ ሥነ ግጥሞ ተገጥሞለት፣ ሥነ ጹሑፍ ተጽፎልት፣ አጠቃላይ ታላቅ ውዳሴ ተወድሶለታል።

በእርግጥ ስለ "ጀማል" የተወራው፥ ሙስሊም ኾኖ ስለ ጓደኞቹ የሃይማኖት ጽናት የከፈለው ውድ ዋጋ ተብሎ የተነገረው ነገር እውነት ቢኾን ኖሮ ምኞቴ ነበር። ለምን ቢሉኝ፦

አንድም ስለ ተሰውቱ ሰማዕታት የሃይማኖታቸው ጽናት መመስከሩ፤

አንድም፦ የሰማዕታት ደም የቤተ ክርስቲያን [ምርጥ] ዘር ነውና እንዲህ ብሎ ጠርጠሉስ እንደተናገረ፦ “…. የበለጠ በገደላችሁን መጠን የበለጠ እንኖራለን (አለን) የሰማዕታት ደም የቤተ ክርስቲያን [ምርጥ] ዘር ነው።ጭካኔያችሁ የሚያሳየው እኛን ከምትከሱበት ወንጀል ነጻ መሆናችንን ነው።እናም ዓላማችሁን ከንቱ ታደርጋላችሁ። ምክንያቱም ስንገደል/ ስንሞት የሚመለከቱ ሰዎች ለምን እንደምንገደል ይገረማሉ። እንደ ወንጀለኛ እና እንደ ተናቀ ሰው ሳይሆን እናንተ እንደምታከብሯቸው ሰዎች በክብር እንሞታለንና። [ስንገደል/ ስንሞት የሚመለከቱ ሰዎች] እውነቱን ሲረዱ ደግሞ እኛን ይመስሉናል/ ከእኛ ጋር አንድ ይሆናሉ (ይቀላቀሉናል)እንዳለን በመገንዘብ፤

አንድም የመገደላቸው ምስጢርና እስከ መጨረሻው ሠዓት ድረስ ስለ ሃይማኖት የነበራቸውን ጥልቅ ጥንካሬያቸውን "ጀማል" ስላየና ስለሰማ፣ እውነቱን ስለተረዳከእነርሱ ጋር አንድነቱን ደም እንዳጸና እንረዳ ነበር፤

አንድምበጽንፈኞች አክራሪ ሙስሊሞች ግድያ መንገሽገሹ ይመሰክር ነበር።

ቢኾንም ግን ስለ "ጀማል" ማንነት "ጀማል፣ ጀማል" እንዳልኾ ከተረዳን (የኤፍሬምን የፌስ ቡክ ክታቡን ይመልከቱ) እውነቱ ለምን ተገለጠ ተብሎ አጉል ንትርክ ተገቢ አይመስለኝም፤ ከዚህ ይልቅ አሁን ስለ ሁሉ ነገር በፍቅር አድርገን ስንነጋገር፦ እውነቱን እውነት ሐሰቱን በሐሰት እንበል፤ ይኼውም፥ "ጀማል" ሳይኾን ኤፍሬም ነው እንበል።

ስለምን ቢባል፥ ሠውን በሠውነቱ እናክብረው የምትሉ፣ መልካምነትን "ጀማል" ለተመኛችሁ ሁሉ "ጀማል" ጀማል ባይኾንም ሙስሊምና ክርስቲያን ወንድሞቹና ህኅቶች ሆይ፦ ስለ "ጀማል" ባልታወቀ መረጃና ማስረጃ ሙስሊም እንደኾነ ስለተነገረለት፤ የተገጠመለት ግጥምና ጀግንነትም ምንም ሳይቀነስና ሳይዛነፍ እንደ ሠውነቱ ተቀኙለት።

          እኛም እንደ ሃይማኖታችን ቀኖና እንዲህ እንላለን፥ ኤፍሬም ሆይ፦ በረከትህ ይደርብን!

No comments:

Post a Comment