Monday, February 16, 2015

ስለ መካ ከተማ መያዝ (መሸነፍ)፦


(ከአስራ  ስምንት ዓመት በታች ማንበብ አይፈቀድም!)

            ሙሐመድም . . . ከዚህም ሌላ መካን በጦር ኃይል ለመያዝ ያደረገው ሃሳብ የተቀደሰ ስፍራ ነው፤ ስለ ሃይማኖት ግዴታ መካን መያዝ አለብን ብሎ ለተከታዮቹ አስረዳ። «መካውያን መካ ገብተን እንሰግድ ዘንድ ያልፈቀዱልን እንደኾነ ምን ማድረግ ይገባናል» ብለው ተከታዮቹ ቢጠይቁት፤ «እኔ የመጨረሻው ነቢይ፥ ሰይፌን ጨብጬ ተላክሁ፣ ሰይፉም፥ የመንግሥተ  ሠማያና የገሃነም መክፈቻ ነው። ስለ ሃይማኖት ሲሊ የሚመዝዙት ሰይፍ ዋጋ ያገኙበታል።» ሲል ሙሐመድ መለሰላቸው።

           . . . ሙሐመድ በዕድሜው እያረጀ ሄደ፣ እንደ ልቡ ለመራመድ አልደፈረም። የደም ሥሮቹም ደክመው ነበር። በአረብ ሃገር፥ ነቢይነቱንና መሪነቱ በመታወቁ መጠን፣ ዓለም በመላ የእስላም ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ግዛት ትኾን ዘንድ አለመ። መዲና ላይ የጦር ኃይሉን እንደ አደራጀና እንዳጎለመሰ ሁሉ በሌሎች ሃገሮችም የእስላምን ሃይማኖት የሚዘረጉትንና የሚያስፋፉትን የክብር መልክተኞችን ማደራጀት ጀመረ። እንዲህ ሲልም ለውጭ ሃገር መንግሥታት መሪዎች ጻፈ፤ ለሮም ቄሣር የጻፈው ደብዳቤ ከዚህ በታች የሚገኘው (የሚነበበው) ነው። ለሌሎችም ነገሥታት ሁሉ የጻፋቸው ደብዳቤዎች እንዲሁ ያሉ ነበሩ፦

Sunday, February 8, 2015

ንግሥት ሳባ፦

ንግሥት አዜብ፥ የንጉሥ ሠለሞንን ጥበብን ለማየትና ለመስማት እንደተገናኘችና ከሃገራችን የሚገኘውን አልማዝና ወርቅ እጅ መንሻ ሥጦታ እንዳበረከተችለት፤ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ "ለንጉሡም መቶ ሃያ መክሊት ወርቅ፣ እጅግም ብዙ ሽቱ፣ የከበረም ዕንቍ ሰጠችው፤ የሳባ ንግሥት፥ ለንጉሡ ለሠሎሞን እንደ ሰጠችው ያለየሽቱ ብዛት ከዚያ ወዲያ አልመጣም ነበር።" (፩ኛ ነገ ፲፥፩-፲፫፤ ፪ኛ ዜና ፱፥፩-፲፪፤ ማቴ ፲፪፥፵፪፤ ሉቃ ፲፩፥፴፩)

Friday, January 23, 2015

"በርታ ሠውም ሁን"፦ (፩ኛ መጽ ነገ ፪፥፫) አስራ ኹለቱ ምክረ ዘ መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ


በርቱ፥ ሠውም ሁኑ! ሠው ለመኾን የሚከተሉትን መንገዶች እንኺድ

፩፤ አምልኮታችንን፦ እናክብር።

፪፤ እግዚአብሔር ቃል፦ ምግባችንን እናድርግ።

፫፤ የአሕዛብን መንፈስ፦ ከኅሊናችን ውስጥ እናውጣ።

፬፤ የሎጂክ ኑሮዎቻችንና የሎጂክ የእውቀት ጠባዮቻችንን፦ እግዚአብሔር አምላክ መንገድ ላይ እንጣለው።

፭፤ የአባቶቻችንን መንፈሳዊ ታሪክ፦ እንደገና ለመገመትና ለማንሳት እንሞክር።

፮፤ የቤተ-እግዚአብሔር መንፈስን፦ በፍቅርና በጸጋ የምንመላለስበትን ጉልበት እንድናገኝ፥ እንበርታ፤ እንጸልይ።

፯፤ በንስሐና በቅዱስ ቁርባን፦ የተባረከ ትውልድ፣ ጊዜ፣ ዘመን እንዲኖረን፤ ዕቅድ (ፕሮግራም) እናውጣ።

፰፤ የዘወትር ዕቅዶቻችን፦ እግዚአብሔር መንፈስ የተመራ እንዲኾን፥ በጸሎት እግዚአብሔር መንገዳችንን አደራ እንስጥ።

፱፤ የዕውቀታችንን ግማሽ፦ እግዚአብሔር መንፈስ ያለበት እንዲኾን ለማድረ፥ እንደገና አዕምሮዎቻችን ወደ አምላክ እንመልስ፤ የነፍስ ትምህርት እንዲኖረን፥ እንዘጋጅ።

፲፤ የዚህን ዓለም ሃብት፦ እንደ ዕለት እንጀራ እንጂ እንደ ዘላለማዊነት አስበን፣ በክፉ ምትአታዊ አኗኗርና ዲያብሎሳዊ ስሜትና ሐሳብ ውስጥ ገብተን የሟርት ኑሮን አንያዝ።

፲፩፤ እግዚአብሔር ክብርና ጸጋ የተሞላ ኑሮ እንዲኖረን፦ ዕለት ዕለት ሠማያዊ ምስክነት ይኑረን።

፲፪፤ መንፈስ ቅዱስ መግለጫ እንድንኾን፦ ዘወትር በአካኼዳችን፥ እግዚአብሔር ግርማ ሞገስ የተላበስን፣ በእምነቱና በቅዱስ ቁርባን ፊታችን የተባረከና የተሻሸ፣ ሠማያዊ ወዝ ያላቸው ልጆች እንዲፈጠሩና እንዲወለዱ፤ እግዚአብሔር አምላክን፥ እንማጸን።


እነዚህ ሂደቶች በሕይወታችን ውስጥ ካሉ፦ ሠው የመኾን ብርታትና እድላችን ሠፊ ነው።

 -----------------------------------------------------------------------------------------------
(ምንጭ፦ ሬዲዮ አቢሲኒያ፥  መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ መንፈሳዊ ትምህርት፤ ክፍል ፳፫)
 ----------------------------------------------------------------------------