Monday, February 16, 2015

ስለ መካ ከተማ መያዝ (መሸነፍ)፦


(ከአስራ  ስምንት ዓመት በታች ማንበብ አይፈቀድም!)

            ሙሐመድም . . . ከዚህም ሌላ መካን በጦር ኃይል ለመያዝ ያደረገው ሃሳብ የተቀደሰ ስፍራ ነው፤ ስለ ሃይማኖት ግዴታ መካን መያዝ አለብን ብሎ ለተከታዮቹ አስረዳ። «መካውያን መካ ገብተን እንሰግድ ዘንድ ያልፈቀዱልን እንደኾነ ምን ማድረግ ይገባናል» ብለው ተከታዮቹ ቢጠይቁት፤ «እኔ የመጨረሻው ነቢይ፥ ሰይፌን ጨብጬ ተላክሁ፣ ሰይፉም፥ የመንግሥተ  ሠማያና የገሃነም መክፈቻ ነው። ስለ ሃይማኖት ሲሊ የሚመዝዙት ሰይፍ ዋጋ ያገኙበታል።» ሲል ሙሐመድ መለሰላቸው።

           . . . ሙሐመድ በዕድሜው እያረጀ ሄደ፣ እንደ ልቡ ለመራመድ አልደፈረም። የደም ሥሮቹም ደክመው ነበር። በአረብ ሃገር፥ ነቢይነቱንና መሪነቱ በመታወቁ መጠን፣ ዓለም በመላ የእስላም ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ግዛት ትኾን ዘንድ አለመ። መዲና ላይ የጦር ኃይሉን እንደ አደራጀና እንዳጎለመሰ ሁሉ በሌሎች ሃገሮችም የእስላምን ሃይማኖት የሚዘረጉትንና የሚያስፋፉትን የክብር መልክተኞችን ማደራጀት ጀመረ። እንዲህ ሲልም ለውጭ ሃገር መንግሥታት መሪዎች ጻፈ፤ ለሮም ቄሣር የጻፈው ደብዳቤ ከዚህ በታች የሚገኘው (የሚነበበው) ነው። ለሌሎችም ነገሥታት ሁሉ የጻፋቸው ደብዳቤዎች እንዲሁ ያሉ ነበሩ፦

            «በእግዚአብሔር ስም በምሕረተኛውና በርኅሩህ፤ ለሄራቅሊጦስ ለሮም ንጉሠ ነገሥት፥ በትክክለኛው መንገድ ለሄደ ሁሉ ሰላም ይሁንለት፣ ከዚህ በኋላ እላለሁ፤ በእውነት ወደ እስልምማ እጠራዎታለሁ፣ እስልምናን ይቀፉ (ይቀበሉ)፤ እግዚአብሔር፥ እጥፍ ይከፍሎታል። አልቀበልም ያሉ እንደኾነ ግን እላንተ የመጽሐፍት ሠዎች ተጠንቀቁ!፤ እኛ እስላሞች ነን! ሃይማኖታችንም እስልምና ነው።»

      በሰላም እስልምናን ለተቀበሉት ሁሉ ቡራኬውን ላከላቸው፤ ለናቁት (ያልተቀበሉትን) ግን ሙሐመድ እንዲህ ሲል የዛቻ ቃል ላከባቸው፦ «እኔ የነቢያት መጨረሻ የኾንሁ፣ ሰይፍ ጨብጬ ተልኬሃለሁ፤ ሰይፉም የምንግሥተ ሠማያና የገሃነም መክፈቻ ነው። በእስልምና ስም የሚመዙት ሁሉ ዋጋ ያገኙበታል።» የጦር ሠራዊቱም የአረብ ጎረቤት ሃገሮችን ሁሉ አጥለቀለቁ፣ ሙሐመድ በሦስት ዓመታት ውስጥ የአረብ ሃገር በመላና የጎረቤቶቿንም ነገዶች ሁሉ ከጫማው ሥር አደረ።

[ምንጭ፦  እስልምናና አፍሪቃ፤ ገጽ ፳፫-፳፬፤ ደራሲ ጐድሬይ ዴይል፤ ተርጓሚ ጐበዜ ጣፈጠ ፲፱፻፵፱ ዓ/ም]  እስልምናና አፍሪቃ መጽሐፉን በPDF ያንብቡ።
 -----------------------------------------------------------------------------------------------
            በተጨማሪም፦ «ስለ መካ ከተማ መያዝና (መሸነፍ)» እንዲሁም በወቅቱ የቆሬሾች የከዓባ ቤተ መቅደስ ተቆጣጥሮ በጎረቤት አረብ ሃገሮች ላይ ያዘመተውን የእስልምናን ሰይፍ እስከ አውሮፓ ሮም ለማዝመት ወደ ኋላ አላለም፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬም ድረስ ይኼ የእስልምናን ሰይፍ እያፍገመገመ ነው። ከሶርያ እስከ ኢራቅ፣ ከየመን እስከ ሊቢያ፣ ከሱማሌ እስከ ሊቢያ፤ ከናይጄርያ እስከ ቻድ፣ የአክራሪዎች የእስልምና ሰይፍ እየተምዘገዘገ የሠዎችን ደም እየጠጣ ነው። በሃገራችን በኢትዮጵያም በተለያዩ ክልሎች የእነዚህ የአክራሪዎች የእስልምና ሰይፍ የብዙ የንጹሐን ሠዎችን ደም አጨማልቆ፣ ሕብረተሰቡን በዕንባ አራጭተዋል።

        የእስልምና ተከታዮች፥ እስልምናን ከጦር እንቅስቃሴ ይልቅ ሃይማኖታዊነቱን ብቻ ካልተመለከቱት፤ ይኼም፦ የማይዳሰስና የማይታይ ሠማያዊ ተስፋ አለ ብለው ለይተው እስካላዩት ድረስ፤ እስልምና ከመካ የጀመረው የእስልምና ሰይፍ እየተምዘገዘገ ዛሬም ድረስ በተለያየ ጊዜያቶችና ዓመታቶች፣ ምዕተ ዓመት መልኩን እየቀያየረ ዓለሙን ሁሉ በእስልምና እቅፍ በማድረግ፦  ነፃነትና ገለልተኛ አመለካከት ፈጽሞ እንዳይኖር ማድረግና ጨርሶኑ እንዳይኖርና እንዳይሰብ ማድረግ፤ እንዲሁም ደግሞ እጅግ አሰቃቂ ስቃይና መከራ፣ እንግልትና ግርፋት ማድረስ፤ የአራዊትነት ጸባይ ተላብሰብ፥ ለቃላትም ይሁን ለማሰብ እጅግ የሚሰቀጥጥ፣ ፍጹም ኢ-ሰብአዊነት የተሞላበት ጭፍጨፋ ማካኼድና መግደል ከብዙ በጥቂቱ ያካኼዱትና ለወደፊትም የሚያካኼዱት መለያቸው እየኾነ ነው! ልዩ አርማቸውም ነው።



          የየትኛውም ቤተ-እምነት ይሁን፣ የትኛውም የሃይማኖት ሠው፤ ኢየሱስ ክርስቶስን በየትኛውም መንገድ ቢቀበለው እንደዚህ ያለ̕ የወረደና ተልካሻ ተግባር፣ ከእንስሳት ያነሰ ምግባር አይዝም!። ኢየሱስ ክርስቶስ ተወልዶ፣ አድጎና ፍቅሩን በመስቀል ላይ ለዓለም አትረፍርፎ ለግሶ፣ ወደነበረበት ወደ ቀድሞ ክብሩ ከተመለሰ በኋላ፤  ከአስት መቶ ዓመት በኋላ የተነሳ ሙሐመድ ለዓለማችን ምንድ `ነው እያስተማረ ያለው? ሰላም? ፍቅር? ገርነት? ቸርነት? ቅንነት? እነዚህማ የአንድነት ምሶሶዎችንማ አያውቋቸውም!። ከዚህ ይልቅ፦ ጦርነት፣ ሽብር፣ ሰቀቀን፣ ፍርሃት፣ ጭንቀት፣ ሁከት፣ ክቡር የኾነውን የሠውን ሠውነት እየበላለቱ ማረድና ሠዎችን መግደል (ነፍስን ማጥፋት አይቻላቸውም) እኮ ምንድ `ነው፤ ሥራቸውና የሙሐመድ አስተምህሮ!።

        እኛስ በክርስቶስ ክርስቲያን የተባልን፣ ንኡድ ክቡር የኾነ፤ ክብርና ምስጋና ይግባውና አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ ብሎናል፦ “ሥጋንም የሚገድሉትን፣ ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ" (ማቴ ፲፥፳፰)።

----------------------------------------------------------------------------
(ለግንዛቤ፦ ሃይማኖታዊ የሚመስሉ፥ ኢ-ሃይማኖታዊ፤ ጽንሰ-ሐሳቦችን ማርቀቅ፤ ለምን? በሚል በክፍል  እና የቀረበ ጹሑፍ ይመልከቱ)
---------------------------------------------------------------------

No comments:

Post a Comment