Saturday, May 25, 2013

የዶ/ር እጓለ ገብረ ዩሐንስ አጭር የሕይወት ታሪክ

ደራሲ / እጓለ ገብረ ዩሐንስ ከጻፉት መፅሐፍ ስለ ሞራል ድቀት ብፁዓን ንጹሐነ ልበ ስለ ክርስቲያን ምግባር መሠረት በሚል ለንባብ ካበቁት የተወሰደ። 

      ሀገር፣ መንደር፣ ቤት ንብረቱን ትቶ ወደ ሩቅ የሄደ ሰው ባይተዋር ይባላል። ይህ ስያሜ በኑሮ አድራሻ መለወጥ ብቻ ምክንያቱን የሚያገኝ አይደለም።   የመንፈስ ባይተዋርነትም አለ። ሰው ከነበረበት ቦታ ወደ ሌላ ሳይዘዋወርም ለአዲስ አስተሳሰብ፣ ፈሊጥና የኑሮ መልክ ሊጋለጥ ይችላል። አንደኛው እስኪያይል ወይም ሁለቱም እስኪዋሐዱ ድረስ የወትሮው እና የአሁኑ በሕሊና ውስጥ የባላንጣዎች ተቃርኖ ይፈትራሉ።

       እንዲህ ያለ ሰውነት ሲታገል ይቆይና ሲሰለቸው፦ የቸልተኘነት፣ የግዴለሽነት ኢንዲፈረንቲዝም መንፈስ ይሰፍንበታል። ይህ በተለይ የሚገለጸው በሥነ ምግባር መስክ ነው። ሥለታም የነበረው ሥነ ምግባራዊ በሕሊናው ይሰንፋል። የሚመቹ፣ የማይቆረቁሩ፣ የማይጋጩ እንደ ዘዴኝነት፣ ጮሌነት፣ ብልሃተኝነት፤ ያሉ የማይጨበጡ የቀልጣፋ ሰውነት ጠባዮች ያይላል።አስመሳይ፣ አድር ባይ፣ እንደ እምነቱ የማያምን፣ እንደ ኑሮው የማይኖር፣ የሕሊናውን ብኵርና ለምስር ንፍሮ የለወጠሌላም ሌላም። እንደ አለንጋ የሚጋረፉ ተግሣጾች ወቅታዊነታቸውን የሚያገኙት በዚህ ሳቢያ ይመስለናል።የሞራል ድቀትየሚባለው ይህ ሳይሆን ይቀራል? የመነሳቱ፣ የመቆሙ፣ ከራሱ ጋር ተስማምቶ ሚዛን ጠበቆ የመራከመዱ፤ ነገርስ እንዴት ይሆን? ቅን ሕሊና የማያልፈው ጥያቄ ነው።
                           +++++++++++++++++              +++++++++++++++++
      Dedicated in Loving Memory of Our Dear Dr. Eguale Guebre Yohannes (1932- 1991). A Great Ethiopian Scholar, Philosopher, Author, Theologian, Diplomat and Lecturer. An Amazing, Wonderful, Loving Husband and Father.
We are very proud of you and very blessed to have you in our lives.
We love you and miss you so much.
Etaferahou Tesfaye, Orit Eguale, Gada Eguale, Kelemsis Eguale.


የዶ/ እጓለ ገብረ ዩሐንስ አጭር የሕይወት ታሪክ - በዶ/ ሥርግው ሐብለ ሥላሴ 1983 / የተጻፈ

 / እጓለ ገብረ ዮሐንስ የካቲት 6 ቀን 1924 / ከአባቱ ከመምሬ ገብረ ዩሐንስ ተሰማና ከእናቱ ከወ/ አመለወርቅ ሀብተ ወልድ አዲሰ አበባ ደብረ ሰላም ቅዱስ እሰጢፋኖስ አጥቡያ ተወለደ:: ዕድሜዉ ለትምህርት ሲደርስ በዚሁ ደብር ፈደል ቆጥሮ ዳዊት ደግሟል:: ዳዊቱን: በቃሉ ጭምር ያውቀው ሰለነበረ የዳዊት መጽሐፍ ባላገኘ ጊዜ በዓቢይ ጾም ዳዊት በሚተዛዘልበት ወቅት በቃሉ ያስተዛዝል ነበረ::

        
ቀጥሎም የዜማ ትምህርት ክመሪጌታ ኃይለ ጊዮርጊስ መንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ወንበር ዘርግተው ከሚያስተምሩት ዘንድ ገብቶ ጾመ ድጓን ዘልቆአል:: በዚያን ጊዜ ከእየደብሩ 2:2 ልጀች እየተመረጡ ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት እንዲገቡ ጥሪ ሰለደረሰ ከሁለቱ ተመራጮች አንዱ ሆኖ ቅድስት ሥላሴ ትምህርት ቤት ገብቶ በዘመናዊ ትምህርት ስምንተኛን ክፍል አጠናቅቆ ሁለተኛ ደረጃ እንዳለ ወደ ግሪክ አገር እንዲሄድ ስለተመረጠ 1943 / ወደ ግሪክ አገር ሄዶ ቆሮንጦስ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን አጠናቅቋል:: እዚያ በነበረ ጊዜ ዝንባሌው ግልጽ እየሆነ ሄደ:: ፍልስፍና ትምህርት ላይ ትኩረት ስለአደረገ የፍልስፍናን መጽሐፍት በብዛት እየገዛ ያነብ ነበር:: የጋለ ፍቅር እስክ መጨረሻ ሕይወቱ አልከሰመም:: የመጽሐፍ ሱስኛ ቀበኛ እንደነበር በዚህ አደባባይ ሳልገልጠው አላልፍም:: ብዙዎቹን መጽሐፍቱን ለተመለክታቸው በእርሳስ ተዥጐርጉረው ገጾቻቸው ተበሳስክው ነው የሚገኙት:: አመለኛ ጎብኝቶአችዋል ማለት ነው::

           
ወደ: ነገሬ ልመለስና የቆሮንጦስን ትምህርት ቤት ሲጨርስ ንግግር እንዲያደርግ የተወሰነው እርሱ ነበር:: ንግግሩ ቅደም ተክተሉ የሠመረ ብቻ ሳይሆን ለለጋ ዕድሜዉ ጥልቅ የፍልስፍና ሐሳብን ያዘለ ነበር:: በዚያን ጊዜ በወቅቱ የአቴን ዩኒቨርስቲ መንፈሳዊ መምህራን እንዲገኙ ተጋብዘው ነበር:: እጓለ ንግግሩን ሲጨርስ አንድ የዩኒቨርስቲ መምህር ክመቀመጫው ተነሥቶ ሒዶ ስሞ አመስግኖታል::

           
አቴን ዩኒቨርስቲ መንፈሳዊ ትምህርትን ከፍልስፍና ጋር አዛምዶ አእምሮውን ያንጽ ጀመር:: ለትምህርት የነበረው ፍቅር በአርእያነት የሚጠቀሰ ነበር:: የተወሰነውን የአራት ዓመታት ትምህርት ካጠናቀቀ በኋላ ወደ ጀርመን ሀገር ሄዶ ቦን ዩኒቨርስቲ ከፍልስፍና ፉከልቲ ተመዝግቦ የሚጓጓለትን ፍልስፍና ይዋኝበት ጀመር:: በዘመኑ ክቦን ዩኒቨርስቲ በዓለም መድረክ የታወቁ መምህራን ያስተምሩ ነበር:: የእነርሱን ትምህርት ሳያስታጉል በጥንቃቄ ያዳምጥ ነበር:: በግልም እያነጋገረ ስለ ፍልስፍና ትምህርት አጠናንና አቀራረብ መመሪያ ይቀበል ነበር:: ይህም አልበቃ ብሎ በሌላ ዩኒቨርስቲ አንቱ የተባሉና በዓለም መድረክ ያንጸባረቁ ለምሳሌ ፍራይቡርግ ዩኒቨርስቲ Martin Heidegger ሀይደልበርግ ዩኒቨርስቲ Karl Jaspers ያስተምሩ ስለነበር እዚያ ያሉበት ድረስ እየሄደ ትምህርታቸውን አዳምጧል:: ሁለቱም እንደሚታወቀው Existentalist Philosophers ናቸው:: Martin Heidegger የታወቀው ሥራጊዜና መሆን” (Time and Being) የሚለው ምን ያህሉንም እጓለን ያረካ አልመሰለኝም Jaspers እውነት” Von der Wahrheit የሚለውን ግን ከአንደበቱ የማይለየው ነበር;: ሁሉንም ባይሆንም እንኳ አብዛኛዎቹን የዚህን ፈላሰፋ ድርሰቶች ገዝቶ ክግል ቤተ መጻሕፍቱ አክማችቶአል:: ምናልባት ወደዚህ ፈላሰፋ መንፈሱ ያጋደለው ሚዛናዊና ኅላፊነት የተሞላ አስተሳሰብ ስላለው ሳይሆን አልቀረም::

            
ቀደመ ካሉት ፈላሰፋዎች የሚያደንቃቸው አፍላጦንን (ፕሌቶንና) ኢማኑኤል ካንትን ነበር:: የአፍላጦንሪፑብሊክየካንትንየንጹሕ አእምሮ ሒስ” (Critique of Pure Reason) የሚባሉት አዘውትሮ ደጋግሞ የሚያነባቸው መጽሕፍት ነበሩ:: ምናልባት ክመጽሕፍ ቅድስ ለጥቆ በሁለተኛ ደረጃ የሚመደቡ ሳይሆኑ አልቀረም::

          
የእጓለ አስተሳሰብ የተመሠረተው በሶቅራጥሰ ጥያቈና ምላሽ ዘዴ ላይ ነበረ:: ስለ: እውነት ሲባል የአንድን ሐሳብ ደካማና ጠንካራ ጐን እየገመገሙ እስከ መጨረሻዉ ሂደት ማድረስ ነበር:: በምንም ዓይነት በሚከራከርበት ወቅት አይቆጣም:: የሚቆጣ ሰው እንኳን ቢያጋጥመው አለሳልሶ ወደ ጤናማ ክርክር ይመልሰዋል:: በምዕራብ አስተሳሰብ ገጸ ባሕርይና ሐሳብ የተለያዩ ናቸው ምንም እንኳን አንዱ ከሌላው ጋር የተያያዘ ቢሆንም:: ሕሳቡን መንቀፍ ሰውየውን ማዋረድ አይደለም::

           
ከባለ ቅኔዎች ደግሞ አሊጌሪ ዳንቴን ፍሪድሪክ ዊልሔም: ጆሴፍ ቮን ሽለርንና ዮሐንቮልፍጋንግ ቮንጌቴን በተለይ ይወዳል:: እንደ ባለቅኔዎቹ ቅደም ተከተል በዚያኑ መጠን ፍቅሩ እያየለ ይሄዳል:: ጌቴ ላይ ሲደርስ ፍቅሩ ይጠናል:: ከፊተኞቹ ሁለቱ ላይ ቀንጨብ እያደረገ በስንኝ ወደ አማርኛ ተርጉሟል:: ከዳንቴ መካነ ንስሐ ከመግቢያው ተርጉሞ ከመጽሐፉ ውስጥ ጨምሮ አሳትሞታል:: እንዲሁም ከሽለርዋስትናየሚለውን ተርጉሟል:: ይበልጥ ያተኮረው ግን ጌቴ ላይ ነበር:: “ፋውስትን በሙሉ በሰንኝ ለመተርጐም አቅዶ ጀምሮ አካሂዶታል:: ነገር ግን ዳር ሳያደርሰው በሞት ተቀደመ:: እንደዚሁ በጅምር የቀሩከተረት ወደ ኅሊናየሚል የፍልስፍና ድርሰትናመዝሙረ ኢትዮጵያዊየሚል የግጥም ሰብስብ ይገኝበታል:: ቀደም ሲል የካንትን ሥነ ምግባር ለማስተማሪያ እንዲያገለግል ገና ከትምህርት ቤት እንዳለ ተርጉሞታል:: እጓለ የግጥም ተሰጥዎ በተጨማሪ ነበረው:: የግጥሙ ስልት የሚክተለው ከፍ ብለው በተጠሩት ባለቅኔዎች ፈር ነበር:: ሌላው ተዘጋጅቶ አልቆለት ሳይታተም የቀረ በአንቀጸ ብጹዓን ላይ የተመሰረተ የአባቱን ምግባረ ሠናይ የሚገልጽ በመንፈሳዊና በፍልስፍና ሐሳብ የተጠናከረ ሰፋ ያለ ጽሑፍ ነው:: የዚህን መጽሐፍ ታትሞ መውጣት ለማየት በጣሙን ይጓጓ ነበር::

         
ቦን ዩኒቨርስቲ የዶክተር ማዕረግ ካገኘ በኋላ ምኞቱ በክፍተኛ ተቅዋም ለማስተማር ስለነበረ የማስተማርን ዘዴ ለማጠናከርና የእንግሊዝኛ ዕውቀቱን ለማጎልበት እንግሊዝ አገር በርሚንግሃም ዩኒቨርስቲ ቆይቶ 1953 / ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ:: ወዲያው ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተመድቦ ፍልስፍናን ማስተማር ጀመረ:: በዚያን ጊዜ ነው ፍልስፍና ለበስ ንግግሮችን በተከታታይ በራዲዮ ለሕዝብ ያሰማ የነበረው:: እነዚህንም ኋላ አሰባሰቦየከፍተኛ ትምሀርት ዘይቤበሚል ርእስ አዲሰ አበባ 1956 / መጽሐፍ አሳትሟል:: በዚህም በኢትዮጵያ አስተሳሰብና በምዕራብ አስተሳሰብ መካከል ድልድይ ሠርቷል:: ስለዚህ በዚህ አገር በዘመናዊ ዐዋቂዎች ታሪክ ግንባር ቀደም እንዲሆን አስችሎታል :: ከዚሁ ጋር መጥቀስ የሚገባው በአስተማሪነቱ ለረጅም ጊዜ በኢትዮጵያ ራዲዮ የታወቀውን መምህር አብራራው በመባል የሚታወቀውን ፕሮግራም ሰያሜውንም የሰጠ ፕሮግራሙንም የጀመረ / እጓለ መሆኑን ነው::

          1956 / ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተዛዉሮ በቦን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አንደኛ ጸሐፊ ሆኖ ሠርቷል:: እዚያም 6 ዓመታት ያህል ካገለገለ በኋላ ወደ ዋናው መሥሪያ ቤት ተዛውሮ በአማካሪነት ማዕረግ የክፍል ኃላፊ በመሆን አገልግሏል:: 1965 / የመምሪያ ኃላፊ ሆኗል:: ከኅዳር ወር እስከ ስኔ ወር 1970 / በበርሊን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አማካሪ ሆኖ ሠርቷል:: ከጥር 1 ቀን 1972 / ጀምሮ ወደ ጡረታ ክልል ገብቷል:: ከዚያን ጊዜ እስከ ዕለተ ሞቱ ባለው ዕድሜ ከፈጸማቸዉ ሥራዎች በኢትዮጵያ የመጽሐፍ ቅዱሰ ማኅበር አማካይነት የግዕዙን ሐዲስ ኪዳን ለማሻሻል በተቋቋመው ቡድን ያደረገው አስተዋፅኦ ጎላ ብሎ የሚታየ ነው:: ሐዲስ ኪዳንን በተለይ ጳዉሎስን በእናቱ በግሪኩ ዘር በቃሉ ጭምር የሚያውቀው በመሆኑ የእርሱ ድርሻ የላቀ እንደነበር ይገመታል::

      1983
/ እንደሚባለው ለእጓለ ጎደሎ ዓመት ነው:: ይህ ዓመት ከገባ አንሥቶ ፈጽሞ ጤና አልነበረውም:: ዓመቱ ሲጋመስ እንዲሁ ጤንነቱ ተጋመሰ:: እዚሁ አዲስ አበባ ሐኪም ቤት ገባ ግን ሕመሙ አልተሻለውም:: ለተሻለ ሕክምና ናይሮቢ ኬንያ ተላከ:: ሕክምናው አሁንም ውጤት አላሳየም:: መጋቢት 23 ቀን 1983 / ናይሮቢ ኬንያ ዐረፈ:: አሰከሬኑ በአይሮፕላን ወደ አዲስ አበባ ተጓጉዞ መጋቢት 26 ቀን 1983 / ሥርዓተ ቀብሩ በቀራንዮ መድኃኔ ዓለም ቤተክርስቲያን ተፈጸመ:: ወሩ ይለያይ እንጂ ወር በገባ 23 አባቱ ያረፉበቱ ዕለት ነው:: አባት ልጃቸውን ጠሩ ልጅም ለአባቱ ታዘዘ::

/ እጓለ ሚያዝያ 8 ቀን 1964 / ከወይዘሮ እሀትአፈራሁ ተስፋዬ ጋር በቁርባን ታጋብቶ 3 ልጆችን አፍርቷል::

                     ቸሩ አምላክ ነፍሱን ክአብርሃም ፣ይስሐቅና ያዕቅብ እቅፍ ያኑርልን::

No comments:

Post a Comment