Saturday, June 15, 2013

በመጽሐፍ ቅዱስ እይታ "ባርያ" ማለት ምን ማለት ነው?


ወዳጆች ሆይ ቅድስት ድንግል ማርያም ልጅ  በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሠላምና ፍቅር ይሁንላቹ!

* በመጽሐፍ ቅዱስ ያ ማለት በብዙ መንገድ የየራሱ ታሪክና ጥልቅ የሆነ ሐተታን ቢጠይቅም እኔ ግን እግዚአብሔር እንደ ፍቃድ በሦስት አበይት የሥአገልግ እይታ እንመለከተው ዘንድ እነሆ፦

1ኛ፦ በፊት በነበረው እርዮተ ዓለም ለምድ የሥአገልግዎቹን በቅጥር መልክ ሳይሆን በአስገባሪዎች አማካኝነት የባርነትን ስራ እንደ ህጋዊነት ይሸጡ ይለውጡ እንደነበር  መጽሐፍ ቅዱስ እንዲ ብሎ ይገልጽልናል “በብር የተገዛ ባያ” /ዘ 1244/ እንዲል!  

2ኛ፦ በባርነት ሳይፈልጉና ሳይፈቅዱ በግዳጅ ያለምንም ክፍያ እንዲያውም እየተደበደቡ፣ ስቃይና መከራ እየተቀበሉ፣ እየተገደሉ፣በሚወልዷቸውም ልጆች ጭምር ዓይናቸ እያየ፣ በመሪር ልቅሶና እሪታ አንጀታቸው እየተላወሰ ወንድ ልጆቻቸው ለሞት፥ ሴት ልጆቻቸውን ደግሞ፤ በጽኑ ሥራ፥ በጭቃ፥ በጡብም በእርሻም ሥራ ሁሉ፥ በመከራም በሚያሠሩአቸው ሥራ ሁሉ፥ ሕይወታቸውን ያስመርሩአቸው እንደነበር፥ እንዲሁም ግብፃውያን የእስራኤልን ልጆች በመከራ እንደገዙአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ በሰፊው ያትትልናል። /ዘጸ 1፥ 13-14/

3ኛ፦ ሦስተኛው ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የእግዚአብሔር መልአክቶች፣ለሟቹ፣ አገልጋዮቹ፣ ነቢያቶች፣ አጠቃላ ለመንፈሳ አገልግ ሲሉ ራሳቸውን በተጋጋ ይጠሉ። መሆ እንደ እግዚአብሔር ቃል ለመንፈሳዊ አገልግሎት ይህን ቃል የተጠቀሙትን በአጭሩ እንይ፦


ሊቀ ነበያት ሙሴ፦ “የእግዚአብሔርም ባሪያ ሙሴ” /ኢያ 11፥2/

ሎሌው ኢያሱ፦ “የእግዚአብሔር ባሪያ የነዌ ልጅ ኢያሱ” /መሣ 2፥8/

ንጉሥ ዳዊት፦ “እግዚአብሔር ባሪያ ዳዊት” /መዝ 36/

ነብየ ኢሳያስ፦ “ባሪያ እሆነው ዘንድ ከማኅፀን ጀምሮ የሠራኝ እግዚአብሔር” /ኢሳ 49፥5/

የ ዳንኤል “የሕያው አምላክ ባያ ዳንኤል” /ዳ 620/

ነብየ ዘካርያስ፦ “ከታናሽነቴ ጀምሮ ባሪያ ሆኜ ነበርሁና” /ዘካ 13፥5/

ስለ አገልጋዮቹ፦ “በቤተ ሰዎች ላይ የሾመው ታማኝና ልባም ባሪያ ማን ነው?” /ማቴ 24፥45/

ስለ ሐቶቹ፦ “ከእናንተም ማንም ፊተኛ ሊሆን የሚወድ የሁሉ ባሪያ ይሁን” /ማር 10፥44/

ስለ መልአክቶቹ፦ “የጌታ ባሪያ” /ሉቃ 1፥38/

ቅ/ ጳውሎስ፦ “የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ጳውሎስ፤ እንደ ባሪያ ራሴን ለሁሉ አስገዛለሁ።” /ሮሜ 1፥2፣ 1ኛ ቆሮ 9፥19/

ቅ/ ያዕቆብ፦ “የእግዚአብሔርና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ያዕቆብ /ያዕ 1፥1/

ቅ/ ይሁዳ፦ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ የያዕቆብም ወንድም የሆነ ይሁዳ” /ይሁ 1፥1/

ቅ/ ሚካኤል፦ “የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ” /ራእ 19፥10/

እንግዲህ ምን እላለሁ? ስለ ጌዴዎንና ስለ ባርቅ ስለ ሶምሶንም ስለ ዮፍታሔምና ስለ ሳሙኤልም ስለ ነቢያትም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛልና። እንዲል ሐዋርያው ቅ/ ጳውሎስ።

ከላይ በጥቂቱ ያየናቸውና ያላየናቸው  ስለ እነዚህ ሁሉ አገልጋይ ባርያዎቹ እግዚአብሔርስ ምን ይላል? “ከባሪያዬ በቀር ዕውር ማን ነው? እንደምልከው መልእክተኛዬስ በቀር ደንቆሮ የሆነ ማን ነው? እንደ ፍጹሙ ወይስ እንደ እግዚአብሔር ባሪያ ዕውር የሆነ ማን ነው?” /ኢሳ 42፥9/ እውነት ነው! እንደ እግዚአብሔር ባሪያ ዕውር የሆነ ኧረ ማን ነው? ሲሰድቧቸው፣ ሲገርፏቸው፣ሲያስሯቸው፣ ለግዞት ሲዳርጓቸው፣ ሲገድሏቸው፤ ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ልጅ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ሲል ሱን ያ ያደረገ ኧረ ማን ነው?

 ይህን ካደረጉ ብጹአኖች ንጹአኖች፣ ታጋሾች፣ የዋሆዎች፣ ገርሮች፣ ቅኖች፤ የመንፈስ ቅዱስ ባርያ አገልጋዮቹ ማለት እነዚህ ናቸው!!!

እንደ ሰውኛ አስተሳሰብ “ባርያ” የሚለውን ቃል በመምዝ ወደ ተሳሳተ የስህተት ተምህሮ ወደ ማስተማር እንዳንሄድ እውነተኛና ሕያው የሆነው የእግዚአበሔር መንፈስ ያለበት የመጽሐፍ ቅዱስ መልስ ይሄ ነው!


                                  ወ ስብሐት ለእግዚአብሐር!!!

No comments:

Post a Comment