
ለዚህ ደግሞ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንጦስ ክርስቲያኖች ባስረዳቸው እውነተኛ አስተምህሮ ድንግል ማርያም ንጽሕት፣ ድንግል መሆኗን፤ መስክሯል። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ለክርስቶስ አገልግሎት በተጠራበት ግዜ "እንደ ንጽሕት ድንግል እናንተን
ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና" /2ኛ ቆሮ 11፥ 2/ ይላል። ታዲያ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በትንቢተ ሕዝቅኤል /44፥ 2/ የተነገረውን የእግዚአብሔር ቃል ደግሞ ሲናገር እመቤታችን ድንግል ማርያም ንጽሕት፣ ድንግል፣ ለክርስቶስ
በክርስቶስ እንደሆነች አስረግጦ አስረድቶናል።


ታዲያ አባቶቻችንና ወንድሞቻችን የሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስን ቃል አብነት አድርገው ስለ ጌዴዎንና ስለ ባርቅ፣ ስለ ሶምሶንም ስለ ዮፍታሔም፣ ስለ ዳዊትና ስለ ሳሙኤልም፣ ስለ ነቢያትና ስሌሎች ቅዱሳን አባቶች እንዲሁም ቅዱሳት እንስት ሲነግሩን ፣ ሲያስተምሩን፣ ሲመሰክሩን ለምን ይሆን የሚነቅፏቸው!
ሐዋርያው ቅዱስ ሉቃስም አረጋዊው ቅዱስን ስምዖን እመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማርያም ስለ መባረኩ እንዲህ ሲል ገልፆልናል! "ስምዖንም ባረካቸው እናቱን ማርያምን" /ሉቃ 2፥ 34/ በማስከተልም ደግሞ ስለ ቅድስት ሐና በቅድስናዋ፣ በጾም፣ በጸሎት፤ በእግዚአብሔር መቅደስ በሌሊትና ቀን እያገለገለች አትለይም ነበር ብሎ አስተምሮና። /ሉቃ 2፥ 36-37/ ስለዚህም ነው አባቶቻችንና ወንድሞቻችን "የድንግል ማህጸን ፍሬ ክርስቶስ በቤተክርስቲያን ተሞሸረ፣ የክርስቶስ ምእመናን ከቤተክርስቲያን ተጸነሱ። ክርስቶስም፥ ለመታረድ የማያቋርጥ፣ እርዱ የማያልቅ ንጹሕ ላህም፣ በግ ነው። ቅድስት ድንግል ማርያም ከርኩሰትም ሁሉ ንጽሕት፣ ከኃጢአትም ሁሉ የጸራች እንደሆነች የማያምን እርጉም ነው። ሰይጣን በድንግል ማርያም ታመመ፣ በልጇ ተጨነቀ፣ በልጇ መስቀል ስቃይ አገኘው። ስለዚህም ከፍጡራን ወገኖች ሁሉ ሰይጣን ቅድስት ማርያምን ይጠላል።" /ጻዲቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፥ መጽሐፈ አርጋኖን/
በሃይማኖት አባቶቻችን ዘንድ "ፊቱ በጨለማ የተሸፈነ ዲያብሎስ በልደት ሥልጣን ያለውን ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም ሥጋን ተዋሕዶ ወደ ሲኦል ወርዶ ባየው ጊዜ ፈራ፥ ደነገጠ።" ይሉናል። ግን ለመሆኑ ይህን ከየት አመጡት ተብለው ቢጠይቁ የሐዋርቱን የቅዱሳን ነቢያትቱ ትምህርት በሚገባ ስለተረዱት ስለ ቅዱሳት እንስት እና ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የሚያስተምሩን በሚገባ እንደተረዱት ያስገነዝቡናል። /ሕዝ 28፥ 13-18። 1ኛ ጴጥ 3፥19። ሃይማኖተ አበው ምዕ 2፥ 8/
አሁንም ወዳጆች ሆይ፦ ስለ ጌዴዎንና ስለ ባርቅ ስለ ሶምሶንም ስለ ዮፍታሔም ስለ ዳዊትና ስለ ሳሙኤልም ስለ ነቢያትና ስሌሎች ቅዱሳን አባቶች እንዲሁም ቅዱሳት እንስት እንደ እግዚአብሔር ቃል መሰረት እግዚአብሔርን በመፍራት፣ አገልጋዮቹን በማክበር፤ ስለ ሁሉ እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛል ይባላል እንጂ! አይ እነዚህን መተረክና ማስተማር ጊዜ ማባከን ነው የሚሉ ካሉ ከሁሉ የከፋ የስህተት ስህተት ነው።
ወ ስብሐት ለእግዚአብሐር!!!
አሁንም ወዳጆች ሆይ፦ ስለ ጌዴዎንና ስለ ባርቅ ስለ ሶምሶንም ስለ ዮፍታሔም ስለ ዳዊትና ስለ ሳሙኤልም ስለ ነቢያትና ስሌሎች ቅዱሳን አባቶች እንዲሁም ቅዱሳት እንስት እንደ እግዚአብሔር ቃል መሰረት እግዚአብሔርን በመፍራት፣ አገልጋዮቹን በማክበር፤ ስለ ሁሉ እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛል ይባላል እንጂ! አይ እነዚህን መተረክና ማስተማር ጊዜ ማባከን ነው የሚሉ ካሉ ከሁሉ የከፋ የስህተት ስህተት ነው።
ወ ስብሐት ለእግዚአብሐር!!!
No comments:
Post a Comment