Thursday, March 20, 2014

በመልአከ መንክራት ግርማ ወንዱሙ ላይ ማጉረምረም ለምን?


አንዳንድ ወንድሞችና እኅቶች በመልአከ መንክራት ግርማ ወንዱሙ ትምህርት ቢመሰጡም፤ የተስጧቸው፥ ያህል ግን አጥጋቢ መንፈሳዊ ስንቅ ያለመያዛቸው ጉዳይ በተጠይቅና በፍልስፍና ጥያቄዎች ሲዳክሩ ማየት የተለመደ ነው።

እንዚህ ሠዎች የዲያቢሎስ መንፈስ ስልትና ውጊያ አለማገናዘባቸው፣ በመንፈሳዊ ትምህርታቸው ውስጥ የሚያስተላልፉት መንፈሳዊ ትምህርቶች ወደጐን በመተው፤ ከአምላክ የተቸራቸውን የጸጋ ሃብተ-ፈውስን በመንተራስና በመለጠጥ፣ አጉልተው፥ ለማጣመምና ሃብተ-ፈውስን "በአጋንት አለቃ አጋንትን የሚያወጣ ሠው ናቸው" በማሰኘት፣ ከመንፈሳዊ ዕይታ ይልቅ በኢ-መንፈሳዊ ዕይታዎች በማቀናጀት፣ ለማጣጣልና ከእግዚአብሔር ጸጋ-በረከት ህዝቡ እንዲርቁ በአሳቻ ምክር በመምከርና በክፉ ዕይታ እንዲታዩ በማሳየት፤ ትልቁን፥ የማጥመቅ አገልግሎት ማለትም፦ ከቤተ-ክርስቲያን ምስጢራት አንዱ "ምስጢረ ጥምቀት" የወጣ ነው፤ ብለው፥ ሲያወሩና ሲፅፉ እያየን ነው።

ቢሆንም ምስጢረ ጥምቀት ከቤተ-ክርስቲያን ምስጢራት አንዱና ዋነኛው ሲሆን፤ እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ ሆነና ስለ ምስጢረ ጥምቀትን (-አማናዊ የሆኑ ሠዎች፦ ወደ ክርስትና ሊመጡ ቢወዱ ንስሐንና ክርስትና እንዲነሱ ሲፈቅዱ የሚያደርጉትን የቀኖና ስርዓት ከምስለ ወድምፅ VCD 1-27 እንዲሁም መፅሐፋቸው፣ በተጨማሪም በአቢሲኒያ የሚተላለፈው በመንፈሳዊ ትምህርታቸው የተካተተ ነው!) በተለይም እንዴት እንደሚፈጸም በ፪፯ኛው በምስለ ወድምፅ በየረር ቅድስት ሥላሴ ቤተ-ክርስቲያን በአውደ ምዕረት ላይ በተካሄደው ንስሐ ክርስትና እንዴት በቤተ-ክርስቲያን ምስጢራት እንደሚከናወን፤ የተገለጸና የታመነ በቂ ምስክር ነው!

እግዚአብሔር፥ ጸጋ በረከታቸውን ያብዛልን፤ እርሳቸውንም ከሠዎች ከንቱ ውዳሴና ከንቱ ማጉረምረም በተጋድሎና በጽናት ያቆይልን፤ አሜን!

3 comments:

  1. amen....le abatchine hedmena tena yestline tigahun yabzalachu !!!!

    ReplyDelete
  2. አሜን! አንተንም ልኡል እግዚያብሔር ያበርታህ ይባርክህ
    መቼም በክፋት ለቆሙ የክርስቶስን ጥሪና ድምፅ ስራ ለማስተዋል ከባድ ነው ነገር ግን ልኡል እግዚያብሔር ያንቃቸው ማስተዋል እንዲችሉ እና መንፈሳዊ ክብርና ስጦታ እንዲገባቸው።
    ልኡል እግዚአብሔር ፀጋውን አብዝቶ በእውነት ለቆሙ ለመምህር ግርማ እና አባቶቻችን እናቶቻችን ወንድሞቻችን እህቶቻችን ይስጥልኝ/ ይስጥልን!!! እኛንም ይባርከን!!

    ReplyDelete
  3. Aw wendmachin Sintayehu beteley Gubae tekftolachew yih awekn temeramern milut tiraz netek ewketachewn ena yemyhon hasabachewn yekinat menfes yetetnawetachewn Mahbere Kidusan wstem yalu gn mahberu ewnet mn aynet sewochin ena astemariwechin new yeyazew mnm neger sayredu abatchin Hara Zetewahido bemilew page lay yemyhon sem setetuachewal abatachinin Aba Girman ena mn yishalal endih yalewn ewnetun kehaset meleyet yakatewn tewld ebakih betelelyaye medrek endineger ena endenastawel be face bookm hone share eyederaregen endenastawk abatachin nistuh sew nachewna Adera alebn ewnet ewnet ewnet beteley lemygeba sem setetobenal zenegna minlchew yebetekrstyanachin lij nachew mnlachew sewoch sem alteksem Even Diakon Daniel Kibret bewananet semachewn bayteksem berasu entenet lay ye zemenu Hasawyan atemakiowch bloawtetual lemn megemerya benawk ayshalm wey endew zmmmmmmmmm blo kemefred beza lay tsere Orthodox (tehadisso)eyebezubn new sentun enwaga errrr mn aynet zemen nw ena anten Egziabher yisteh bereketachew yiderben amen!

    ReplyDelete