Thursday, April 17, 2014

ታትመናል፥ በደሙ በክርስቶስ!


ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ፥ የዓለም መድኃኒት፣
ተወልዶ፥ ከድንግ ማርያም ቅድስት፣
ፍቅሩን ሲገልፅላት፥ እነሆ፦ እናቴ አላት፣
እኛም እንበላት፥ በክርስቶስ ፍቅር እናታችን ናት።

ክርስትና፥ ኦርቶዶክ ዘ ተዋሕዶ ነች፣
የቅዱሳኑን ስማቸው፥ ታከብራለች፣
ከክርስቶስ ስርዓት፥ ያልበረዘች፣
ሁሉን ነገሯን፥  ስለ እርሱ ያደረገች።

መጥምቁ ዮሐንስ፥ ክርስቶስን ሲሰብከው፣
የዓለም በግ፥ መድኅነ ኢየሱስ ነው ሲለው፣
አይሁድ ፈሪሳዊያን፥ ለካስ ሞኞች ናቸው፣
አፍጥነው ለመስቀል፥ እቅድ አዘጋጅተው።

በተና በ ተመካ ሉ፣
ሁከት እንዳይነሣ በበዓል አይሁን አሉ።

ዕረቡ፥ የከንቱ ከንቱ ምክር ተፀነሰ፣
ቀኑ ጸጥ ብላ ዋለች ዕት ሐሙስ፣
በዚች ሌሊት ተያዘ የዓለም ንጉስ፣
ዓለሙን በደሙ ሊያነፃ ክርስቶስ።


         ዕለት ዕለት ከቃሉ የተማሩው፣
ጴጥሮስም ሰይፍ ቢመዝው፣
የመፅሐፍት ቃል እንዲፈፅመው፣
ሰይፍፉን እንዲመልስ አመላከተው።

ወደ ይሁዳ የፍቅር ዓይኖቹን፣
ለካህናት አለቆች ውብ እጆቹን።

ራሱን አሳልፎ ሰጠ ስለ ፍቅሩ፣
እንዲፈፀም የቃሉ ምስጢሩ።

እንስቀለው አሉ፥ ወንበዴውን ሊያስፈቱ፣
ጮኦትና እሪታ እያሰሙ፥ እስከ ለሊቱ፣
ከንጉሳቸው ዘንድ ቀረቡና  ፊቱ፣
ይለቀቅ፥ ይለቅቅ! እያሉ በርባን ከእስራቱ።

ተሳካና፥ አሉ የታለ ያ የዓለም በግነቱ፣
ምግብ የሚሆነው፥ ብለው ሲዘባበቱ፣
አላስተዋሉምና ሥጋውን ሊበሉ፥ ተዘባበቱ፣
ጌታን ለመስቀል፥ እርስ በርሳቸው እየዶለቱ።

ይሁዳ ልቦና፥ ተንኮል ተፀነሰሰና፣
በምክረ ሠይጣን፥ ልቦና ሸፈተና፣
ክርስቶስ ሞተ፥ ለዓለም ተሰቀለና፣
ትን ድል ነሳው፥ ጌታ ነውና።

ክርስትና፥ በብዙ መስቀለና እንግልት እያለፈች፣
በመከራ አፋፍ ብትሆን እንኳን፥ እየጸናች፣
ኑ ከበጉ ማዕድ፥ ተመገቡ  ጠጡ እያለች፣
የክርስቶስን፥ ሥጋ ወደሙ ትመግባለች።

ክርስትና፥ ኦርቶዶክ ዘ ተዋሕዶ ነች፣
የቅዱሳኑን፥ ስማቸው ታከብራለች፣
ለጴጥሮስ ቃል የገባለትን፥ ታስታውሳለች፣
በስማቸውም፥ ቤተ-ክርሰቲያን ትመሰርታለች።

የዓለም በግ፥ መድኅነ ኢየሱስ
እንድንጠ ውኃና ከመስ፣ ʼ
ልጁ እንድን በመ ቅዱስ፣
መናበደ ክርስቶስ!።
 ------------------------------------------------------------------
(ማሳሰቢያ ሥነ-ግጥሙን፥ ገንዘብ ለማግኛ እንዳይጠቀሙበት በእግዚአበሔር ስም አደራ እላለሁ፣ ይህን ሥነ-ግጥሙን ከወደዳችሁት በማንኛውም መንገድ ለሕዝበ ክርስቲያንን ሊጠቅም በሚችል መንገድ ማንሸራሸር፤ ትችላላቹ። እግዚአበሔር ይስጥልኝ አመሰግናለሁ! በከንቱ የተቀበላችሁ፥ በከንቱ ስጡ። /ማቴ 108/ ይላልና ወንጌሉ!)
 -----------------------------------------------------------------

No comments:

Post a Comment