Sunday, April 20, 2014

ክርስቶስ፥ በከርሰ መቃብር፤ ሦስት መአልት ሦስት ሌሊት እንዴት ሊሞላው ቻለ? በቀሲስ ብርሃኑ ጎበና

        ክርስቶስ ሦስት መአልት ሦስት ሌሊት፣ በከርሰ መቃብር አደረ፤ የሚባለው፥ እንዴት ሆኖ ነው? (ለሚለው ጥያቄ፥ ምላሹ በሁለት ዓይነት አረዳድ እንገነዘባለን)

        
፩፤ ለዚህ ምላሽ የዕብራውያንን አቆጣጠር ማወቅ ያስፈልጋል:: የመጽሐፍ ቅዱስን ምስጢር ለማወቅ መጽሐፍ ቅዱስን የጻፉት የዕብራውያንን ሥርዓት ወግና ጂኦግራፊያዊ (መልክአ ምድራዊ) አቀማመጥ ያስፈልጋል።

        
ምክያቱም፥ ጸሐፊዎቹ ባህላቸውንና ሥርዓታቸውን ጠብቀው የጻፉት ስለሆነ ነው። ጌታ ዓርብ ተሰቅሎ ቅዳሜ ለእሑድ አጥቢያ ከተነሳሣ እንዴት ብሎ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት ይሞላል ሊያሰኝ ይችላል።

        
ዕብራውያንን አቆጣጠር ሌሊት የሚቆጠርው በዋዜማው ካለው አሥራ አንድ ሰዓት ጀምሮ ነው። ከአሥራ አንዱ ሰዓት በፊት ያሉት ሰዓቶች ግን አንድ ሰዓትም ቢሆን እንደ አንድ መዓልትና ሌሊት ይቆጠራል። ጌታ የተቀበረው ዓርብ ከአሥራ አንድ ሰዓት በፊት ስለሆነ የተቀበረበት ሰዓት የዓርብን መዓልትና ሌሊት ያጠቃልላል።

        
አርብ ከሠርክ አሥራ አንድ ሰዓት ጀምሮ እስከ ቅዳሜ አሥራ አንድ ሰዓት ከሰዓት በዋላ ድረስ ያለው የቅዳሜ መዓልትና ሌሊት ነው። ቅዳሜ ከአሥራ አንድ ሰዓት ጀምሮ ያለው እሑድ ነው። አንዱም ሰዓት ቢሆን ከላይ እንደ ተገለጠው የዕለቱን ሰዓቶችን ያሟላል። ጌታም የተነሣው እሑድ በመንፈቀ ሌሊት ስለሆነ ሦስት መዓልት ሶስት ሌሊት ይሆናል።

        
፪፤ ሁለተኛው ደግሞ የተሰቀልው በዕለተ አርብ ሰለሆነና የሞተውም በዕለት አርብ በመሆኑ አቆጣጠሩ ከአርብ ጠዋት ይጀምራል። አርብ ጠዋት ከ፲፪ ሰዓት እስከ ሰዓት ድረስ በምድር ላይ ብርሃን ነበር፤ አንድ ቀን።

        
ከ፮ እስከ ሰዓት በምድር ላይ ጨለማ ሆነ ይላል መጽሐፍ ቅዱስ፤ ያም፥ ጨለማ እውነተኛ ጨለማ እንጂ በምትሐት የሆነ ስላልሆነ እንደ ሌሊት ይቆጠራል። አንድ ቀን አንድ ሌሊት ይኖረናል። አርብ ከ፱ ሰዓት እስከ ምሽቱ ፲፪ ሰዓት እንደገና ቀን ሆኖአል፤ አርብ ሌሊት ለቅዳሜ አጥቢያ ያለውን ጨለማ ወይም ሌሊት ስንቆጥር ሁለት ቀን ሁለት ሌሊት ይሆናል።

        
ቅዳሜ ሙሉ ቀንና ሌሊት ለእሁድ አጥቢያ ጌታ እሁድ ሌሊት ተነስቷል፤ አንድ ላይ ሲደመር ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት ይሆናል። እንግዲህ በሁለቱም ዓይነት የሚቆጥሩ ስላሉ ሁለቱም ዓይነቶች ቀርበዋል እኛም የገባንና የተረዳንን አቆጣጠር መርጠን ማስረዳትም መረዳትም እንችላለን።

                     
<<<<<<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!! >>>>>>>>

ምንጭ፦ ዓምደ ሃይማኖት /ገፅ ፹፱/ ሲስ ብርሃኑ በና

No comments:

Post a Comment