Tuesday, August 19, 2014

ከፕሮፌሰራችን ዕይታ፦ የማልስማማበት



ፕሮፌሰራችን መስፍን ወልደ ማርያም ለሃገራችን፣ ለሕዝባችን፣ ለሀሕጉራችን፤ ትልቅ አስተዋጽዎ ካበረከቱ አንዱ ምርጥ ኢትዮጵያዊ ናቸው። ስለ ፕሮፍ አጠቃላይ ስለሰሩት መልካም ስራዎች፣ ስላበረከቱት ታላቅ አስተዋጽዎ በዚች አነስተኛ ጹሑፍ ለመዘከር አይደለም፤ ይልቅ የፕሮፋችን ዕይታ፣ ተመክሮ፣ ልምድ፣ ሕይወት፤ በዚህ ባሳለፍነው ተከታታይ አምስት ሳምንታት ከምንወዳትና ከምናከብራት፥ ከመዓዛ ብሩ ጋር እያደረጉት ያለውን ቃለ-መጠይቅ እያዳመጥናቸው ነው።

ሦስት ነገስታንን በሕይዎታች የተመለከቱ እኚህ ፕሮፋችን፥ በንግግራቸውም ረጋ ያሉና አንደበተ ርዕቱ ናቸው፣ እጅግ ማራኪ በኾነ አገላለጽ ታሪኮችን ያማክላሉ፣ የራቀውን አቅርበው እያጣጣሙ እያስቃኙን ነው። ቢኾንም ከፕሮፌሰራችን ዕይታዎቻና ቅኝቶች፦ የማልስማማበት ነገሮች ቢኖሩም፤ ከማልስማማበት አንዱ ደግሞ “የመንፈሳዊ ልዕልና” ብለው በዘረዘሩት ውስጥ “የቱ ጳጳስ፣ የቱ ቄስ ነው? ድኾች ተጠቅተዋል፣ ፍትሕ ጎደለ፣ ሠው ተበደለ ብሎ የጮ። የለም!። ካሉ በኋላ በእርሶ ጊዜ፦ አቡነ ባስልዮስ፥ ከንጉስ እጅ እርስዎና ከእርስዎ ጋር ሊገረፉ የነበሩትን ሠዎች ስለታደጉ ብቻ “ከአቡነ ባስልዮስ በኋላ ማንም!” የለም ማለትዎን ስለማልቀበለው ከአቡነ ባስልዮስ በኋላ፦ ድኾች ተጠቅተዋል፣ ፍትሕ ጎደለ፣ ሠው ተበደለ ብው የጮኹ አሉ!፤  ለዚህም  ከታች ያለውን አነስተኛ ጹሑፍ ላዘጋጅ ወደድሁኝ። እንደ መረጃና እንደ-ማስረጃ ይኾነን ዘንድ እንሆ ኹለቱን፦


በአብዮቱ ዘመነ-ደርግ ጊዜ (መረጃና ማስረጃ፤ አንድ)

ለአብነት ያህል በመጨረሻው ሸንጎ ላይ ከተገኙት የሃይማኖት መሪ (ስማቸውን በውል ባላውቀውም፥ እኚህ አባት መንፈሳዊ አባት ወይም ቄስ መኾናቸውን ልብ በሉ) እንግዲህ ፕሮፍ “አንድ ጳጳስ፣ አንድ ቄስ የለም” ማለታቸው ምን ማለታቸው ነው? የመፈሳባቶችንሪክ ይሆን ወይ? ወይስ  ለጠል? ግራ-ቀኙን ሳይመለከቱ፣ ነገሩን ከስሩ ሳይረዱ እንዲሁ በደፈናው መናገር ይቁም!። አልሰማኹም፣ አላየኹም፣ አላነበብኩም፤ ማለት እያለ “አንድ ጳጳስ፣ አንድ ቄስ የለም” ብሎ መናገር ታሪክን የኋሊት ሄዶ ያለ-ማንበብ፣ ያለ- መስማት፣ ያለ- ማየት፣ ያለማሰስ እንዲሁም ጥናትና ምርምር ሳያደርጉ እንደው በደፈናው የተናገሩ ቃል ከመኾን አያልፍም! ይኼ ቃላቸው እንከን እንደኾነ ያስረዳል እንጂ እውነታ የለውም! ፕሮፋችን፥ ልብን በሚነካና በለሰለሰ ቃላት አሳጅበው፣ እውነታው፥ ለመሸፈንና ለማድብዘዝ፤ “አንድ ጳጳስ፣ አንድ ቄስ የለም” ስላሉን ብቻ እውነት እንዳይመስለን!።

ለምን? ተብዬ ብጠየቅ፤ ፕሮፌሰራችን፥ ያልሰሙት፣ ያላዩት፣ ያላነበቡት፣ ያልተገነዘቡት፤ እውነታ እንዳለ አምናለሁ። ፕሮፌሰራችን፥ የሰሙት፣ ያዩት፣ ያነበቡት፣ የተገነዘቡ እውነታ ቢኾን ኖሮ እንዲህ፦ “እንደ ቀድሞዎቹ ጳጳስ፣ እንደ ቀድሞዎቹ ቄስ በአሁኑ ጊዜ የለም” ባሉ ነበር፤ ፕሮፍ፥ ግን ያሉት የተገላቢጦሽ ኾነ ነገሩ።  

በመጨረሻው ሸንጎ ላይ፦ ድምፃቸውን ለማሰማት ከታደሙት መካከል፤ በጓድ መንግስቱ ኃይለ ማርያም፥ ጋባዥነት ለታደሙ ሠዎች ድምፃቸውን እንዲያሰሙ ዕድል ይሰጡ ነበር። በዚህ ሸንጎ መሐል እንዲናገሩ ዕድል እንዲያገኙ ጓድ መንግስቱ ኃይለ ማርያም፥ አንድን አባት “እሺ እዚህ አባቴ” ብሎ እንዲናገሩ ዕድሉን ለእኚህ ቆራጥ መንፈሳዊ አባት ሰጥቷቸዋል።

በጓድ መንግስቱ ኃይለ ማርያም፥ በአብዮቱ ዘመነ-ደርግ ጊዜ፦ በመጨረሻው ሸንጎ ላይ ከተገኙት የሃይማኖት መሪ ከኾኑት አንድ አባት የተሰማው፤ ሸን ያልተጠበቀው እጹብ ድንቅ ነገር ልዩ ነው። የመንግስቱን አስተዳደር፥ በመንቀፍ፣ የሥልጣኑ ኃያልነትና አስፈሪነት ሳይበግራቸው፣ በቆራጥ አነጋገር ወደ ኋላ ሳይሉና ሳያጎበድዱ የተናገሩት ህያው የኾነ ቃል በመናገር ታሪክ ሁሌም ሊያስታውሳቸውና ሊዘክራቸው የተገቡ ታላቅ አባት ናቸው። እኚህ ታላቅ መንፈሳዊ አባት በሸንጎ ላይ፥  ለወታደራዊ መሪው  ለጓድ መንግስቱ ኃይለ ማርያም  ለአብዮቱ ዘመነ-ደርግና ለኢትዮጵያ ሕዝብ በአጽዕኖት እንዲህ ሲሉ ተናግረው ነበር፦  

“ ,,, ምናልባት በእርሶ አስተዳደር፣ ምናልባት በእኛ አስተዳደር የኢትዮጵያ ሕዝብ፥ የማያምንበት ኾኖ ከተገኘ፣ ከኢትዮጵያ አንድነት በኋላ ተወያይተን እርሶም እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ በወታደራዊ ደረጃ ያድራሉ ወይም ደግሞ የአገልግሎትዎ ዘመንዎ ተቆጥሮ ጡረታ ይወጣሉ (እንወጣለን)። ምንድነው የምንፈራው! ከሃገር አንድነት አይበልጡም! እርሶ!።

ነገር ግን በአሁኑ ሠዓት ላይ፦ የኢትዮጵያ ሕዝብን፥ ፶ (አምሳ) ሚሊዮን ሕዝብን በጦርነት ባሕር ማግደው፣ ቆስቁሰው፣ በእርስዎ ኃላፊነት፥ ፲፰ (አስራ ስምንት) ዓመት ሙሉ መርተው፣ ሳያደራድሩ  (ሳያደላድሉ)፣ ሳያረጋጉ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብን እሳት ላይ ዳርገው፣ በአሁኑ ሠዓት ላይ ከመሞት በስተቀር፣ የቴዎድሮስን ጽዋ ከመጠጣት በስተቀር፤ ሌላ እድል የለዎትም!።

ይኼንንም፥ እንደማያበላሹ አምናለሁ!። እዚቺው እንደሚሞቱ እንጂ እንደ-ሌሎች መሪዎች በኤውሮፕ ውስጥ ላይ ይፈረጥጣሉ ብዬ እምነት የለኝም! እግዚአብሔር ምስክሬ ይኹን!። ይኼንን፥ ሕዝብ አጋልጠው ይሞታሉ (ይሄዳሉ) አልልም፤ መንጌ፥ ከርሷ ወንበር ላይ ደርቀው እንደ-ቋንጣ እንደሚቀሩ፣ ለታሪክ እንደሚቀሩ ምንብዎታለሁ!። ኼንን፥ ባያደርጉ ግን ታሪክ ይፋረድዎታል! ያለዎት ዕድል ይኼ ብቻ ነው፤ አሁን እኛ ያለን ዕድለ ሦስት ቀን ብቻ ነው።

      ይኼም ታሪካዊ መስክ ኹለተኛ የምንገናኝበት ጊዜ ያለ አይመስለኝም፣ እኔ፥ እየጠበበኝ መጥቷል፣ እየጨነቀኝ መጥቷል፣ እናንተ አግገባችሁም! ለሞት የተዳረገ ሕዝብ ዳምኗል! ሞት ያደነዘዘው በልዩ ልዩ ሥራ ነው።” /፩/ (ድምጽ-ወምስሉን ይመልከቱ)


ከዘመነ ደርግ እስከ ኢሕአዴግ ዘመን አለቃ አያሌው ታምሩ (መረጃና ማስረጃ፤ ኹለት)

ሊቀ ሊቃውንት አያሌው ታምሩ፦ ከጎጃም ክፍለ ሀገር ተልዕኮ እስከ አብዮት ዐደባባይ (መስቀል ዐደባባይ)፣ ከደርግ ውድቀት ዋዜማና እስከ ሚያዝያ ጊዮርጊስ፣ ከቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን እስከ የኢሕአዴግ ዘመን መግቢያና አጠቃላይ በሕይወት ዘመን እስከ-ነበሩበት ጊዜያት፤ ያላለሰለሰ ጥረት አድርገዋል!። ይኼንንም ለመቃኘት ካስፈለገን፦ በድምጽ የተሰጠ ትምህርታቸው፣ የተናገሯቸው ንግሮች፣ ቢሰሙና ቢያዳምጡ፤ እንዲሁም ደግሞ፦ የሃገር ያለህ፣ የእግዜር ያለህ፣ የሠው ያለህ፣ እያሉ፤ በወቅቱ የታተሙትን ጋዜጦችና መጽሔቶች ተናግረዋለ፣ አሳትመዋል። እነኚን ጋዜጦችና መጽሔቶች ስናነብና ስንቃኝ ደግሞ የሊቀ ሊቃውንት አያሌው ታምሩን ቆራጥነት እንመለከታለን።

በቆራጥነት መቆማቸውን ለመመልከት ደግሞ፦ መንግስት፥ ሕዝብን ሲበደልና ግፍ ሲፈጸም፤ በዝምታ ማዕቀብ የማያልፉ፣ ስለ-እውነትና ስለ-ተገፉ ሠዎች የሚገዳቸው፣ ከትንጋቸው ጋር ሲቃ እየተናነቃቸው፦  የሃገር ፍቅርንና የሕዝብን አንድነት በቆራጥነት የተናገሩ፣ የጉልበተኞች መንግስታት ኃያልነት ያልፈሩ፣ የመሳሪያ ብዛትና እስከ-አፍንጫቸው ቢታጠቁም በአለቃ አያሌው ዘንድ ግን “ከራስ በላይ ንፋስ” የሚባለውን ተረት ወዲያ አስወግደው፣ መንግስታትን፦ “በእውነት ሕዝብን በደላችሁ፣ ሕዝብን ገፋችሁ፣ ሕዝብን አሰቃያችሁ፣ ሕዝብን ገደላችሁ እያሉ”፤ ለማንንም ሳያጎበድዱና በተናገሩበት የጸኑ፣ ባመኑበት ነገር ወደ ኋላ ያላሉ፣ በእውነትና ስለ-እውነት እየመሰከሩ ፊለ-ለፊ የገሰጹና የተናገሩ ድንቅና ታላቅ አባት ናቸው።

አለቃ አያሌው ታምሩኅዳር ቁስቋም ላ ለትግራይ ተወላጆች ያቀረቡት መንፈሳዊ ጥሪ

“ ,,, አሁን በደረስንበት ወቅትም ሥጋዊና መንፈሳዊ ሥልጣን በሙሉ ለትግራይ ሕዝብ ተሰጥቷል። ይህ ታላቅ ሕዝብ የተሰጠውን መንፈሳዊና ሥጋዊ ሥልጣን ገሪቱንና ቤተ-ክርስቲያንን ከውድቀት ለማንሣት ሊሠራበት ይገባል። ይህ ሳይሆን ቀርቶ ሕዝብና እግዚአብሔርን የሚያሳዝን ሥራ ቢሠራ ግን ትዝብትንና የታሪክ ተወቃሽነትን ያተርፋል”፤ የሚል ሐሳብ ያለው ሰፊ ትምህርት ሰጥተዋል።

አለቃ አያሌው፦ ለሰብዓዊ መብት ቀናዒ ነበሩ! ለሕዝቡ ማጽናኛ ቃሎችና ምክሮችን በመለገስ፣ ለመንግስታቶች ደግሞ ግልጽና ጠንካራ ተቃውሞችን በማሰማት፣ እንዲሁም እየገሰጹ፤ እስከ-ዕለተ እረፍታቸው ድረስ በቆራጥንት የታገሉ ታላቅ መንፈሳዊ አባት ናቸው!።/፪/ 
                                                                               
ለማጠቃለያ፦ ፕሮፋችን፥ ያልጠቀስኳቸው ብዙ መንፈሳዊ አባቶች አሉ! እናም ፕሮፋችን ከላይ በጥቂቱ ከተገነዘቡልኝ እንግዲህ፦ “እንደ ቀድሞዎቹ መንፈሳዊ አባቶች በአሁኑ ጊዜ ለምን አይታዩም” እንደሚሉ ተስፋ አለኝ፤ ሠላምን ሁሉ እመኝሎታለሁ!!! አክባሪዎ።
------------------------- /// -----------------------


ምንጭ፦   /፩/ ከድምጽ-ወምስል  ከቃል ወደ ጹሑፍ የተገለበጠ፤
            /፪/  ከሊቀ ሊቃውንት አያሌው ታምሩየሕይወት ታሪክ፤


No comments:

Post a Comment