Wednesday, September 30, 2015

በመልአከ መንክራት ግርማ ወንዱሙ ላይ ማጉረምረም ለምን? ክፍል ፪



እኔ ታናሽ ብላቴና ይህንን ጹሑፍ እንዳዘጋጅ ያነሳሳኝ ነገር ስለ  ሦስት ዓበይት ነገር ነው።

አንደኛ፦ ከአንድ ዓመት አምስት ወር በፊት የምንወድው ውዱ ወንድማችንና መምህራችን ቀሲስ ሕብረት የሺጥላ «አጋንንትን ከሰዎች የማስወጣት ሥርዓት» በሚል ባስተማረው ትምህርት በዚህ ትምህርትህ ላይ መምህራችን ስም ሳይጠቅስ (ስለ መልአከ መንክራት ግርማ ወንዱ ያስተማረው ትምህርት እንደሆነ ነው በቀጥታ የተመለከትኩት።)

ኹለተኛ፦ በፕሮቴስታንታዊ ተሀድሶ የሚመራው መለከት የተባለ ሬድዮ ያሰራጨው የሐሰት ዶሴና ክስ፤ ጲላጦስና ሄሮድስ የማይስማሙ ኾነው ሳለ ክርስቶስን አሳልፈው ለመሰጣጠት ለጊዜያዊ ጥቅማቸው ሲሉ አንድነታቸውን አበረቱ፤ እንዲሁም ደግሞ መልአከ መንክራት ግርማ ወንዱሙ ለማሳደድ አንዳንድ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ጉያ ከተሰገሰጉ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ጋር በማበር ለጊዜያዊ ጥቅማቸው ሲሉ አንድነታቸውን አበረቱ፤ ሲያብሩ አየን፤ ሰማን።

እነዚህ አንዳንድ ዘለባብዳን /ዘለባጆች "መለከት ሬድዮ" በተባለ በድምፅ ማሠራጫ ባስተላለፉት የድምፅ ማዕደር የወንጌል ሥራ ከእኛ ጋር የሚሰሩ የተባሉ፤ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ጉያ ከተሰገሰጉ ፕሮቴስታንት ተሐድሶ ከኾኑት ከእነ አቶ ጽጌ ስጦታው፣ ከእነ አቶ ሙሴ መንበሩ ጋር (እነዚህ በይፋ የተወገዙና የተለዩ ቢኾኑም ሌሎች ያልተወገዙና ያልተለዩ አሉ) መረቡን የዘረጋው ፕሮቴስታንታዊው ተሀድሶ ቡድን ነው፤ ይሄ ቡድን የተለመደውን መዘለባበጃቸውን ለይስሙላ በመልአከ መንክራት ግርማ ወንዱሙን በማነጣጠር፣ የመምህር ግርማ ወንዱሙን መንፈሳዊ አገልግሎታቸውንም እንነቅፋለን ቢሉም ቅሉ ግን አጠቃላይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ዶግማንና ቀኖናን ያነጣጠረ ነበር። ይሄም፥ የቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ አባቶችን፣ ቅዱሳት መላእክትን፣ ጻድቃንን፣ ቅድስት ድንግል ማርያምን በማንቋሸሽና በማጥልሸት፤ የተለመደው የኑፋቄ መርዛቸውን ሲረጩ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው።

ጠቢቡ ሠለሞን በምሳሌው፦ "በቃል ብዛት ውስጥ ኃጢአት ሳይኖር አይቀርም፤ ከንፈሩን የሚገታ ግን አስተዋይ ነው።" /ምሳ 1019/ ብሎ እንዳዘዘን፤ እኛም ከንፈራችን የተባለው፥ አንደበታችን ሰብስበን፤ ይሄንን የድምፅ ማዕደርን በመስማት እውነቱን እንወቅ!።

 ሦስተኛ፦ የምናከብረውና የምንወደው ውድ የቤተ ክርስቲያል ልጅ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በጻፈው «የዘመናችን አጥማቂ ነን ባዮች፡- የሐሳዊው መሲሕ መንገድ ጠራጊዎች» በሚለው ከመጣጥፉ በመነሳት ነው።  ቢሆንም ግን ይህንን   ጹሑፍ ሳዘጋጅ እጅግ በጣም ልቤን ኃዘን እየተሰማኝ ነው። ምክንያቱ ደግሞ በአንዳንድ ታላላቅ መንፈሳዊ መምህራኖቻችን ፊት ለፊ ሊኖር የሚገባው፦ ተቀራርቦ መወያየት፣ መተሳሰብ፣ መግባባት እና መናበብ ያለመኖር እረፍት ይነሳኛል። እንዲሁም ደግሞ፦ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ምዕመናን በከተበው ክታቡ ላይ፦ «የጸጋም ስጦታ ልዩ ልዩ ነው መንፈስ ግን አንድ ነው» የተባለውን የመንፈስ ቅዱስ ሥጦታን ታላላቅ መንፈሳዊ መምህራኖቻችን፥ አንድ ሆነው በአፅንኦትና በቅንጅት ያለመረዳት ችግራቸው እየሆነና እየተለመደ እየመጣ ነው። ለወደፊቱ ይህ ችግር ይቀረፋል የሚል እምነት አለኝ።

የዚህ ጹሑፍ አቅራቢ፥ ወንድማችን ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በጻፈው ጹሑፍ አርዕስት በመነሳት «የዘመናችን አጥማቂ ነን ባዮች፡- የሐሳዊው መሲሕ መንገድ ጠራጊዎች» የተባሉት እነማን እንደሆኑ ይመረምራል። እንዲሁም የምንወድው ውዱ ወንድማችንና መምህራችን ቀሲስ ሕብረት የሺጥላ «አጋንንትን ከሰዎች የማስወጣት ሥርዓት» በሚል ባስተማረው ትምህርት ላይም በመልአከ መንክራት ግርማ ወንዱሙ ላይ የተሰነዘረ የድምፅ እና ጹሑፍ ፍላፃ ባይሆን ይመርጣል፤ ከሆነም ደግሞ በመልአከ መንክራት ግርማ ወንዱሙ ላይ ማጉረምረም ለምን? ብሎ ይጠይቃል!።

ወደ ፍሬ ሐሳቡ ስገባ «የዘመናችን አጥማቂ ነን ባዮች፡- የሐሳዊው መሲሕ መንገድ ጠራጊዎች» መግቢያ ላይ የተጻፈው «ክብራቸውን የሚገልጥ ማስታወቂያ ያስነግራሉ» ተብሎ መጻፉ በራሱ ስህተት ነው፤ ምክንያቱ፥ አንደኛ ማስታወቂያ ማስነገር ኃጢአት አይደለም፤ ቀጥሎ ደግሞ በቤተ ክርስቲያናችን አንደ መንፈሳዊ አስተማሪ ሀገር ቤትም ውስጥ ይሁን በውጭ ዓለም ተጋባዥ ኾኖ ሲመጣ፦ አቡነ እገሌ፣ መጋቤ እገሌ፣ ቀሲስ እገሌ፣ መምህር እገሌ፣ ሊቀ ሊቃውንት እገሌ፣ ዲያቆን እገሌ፣ ሊቀ ዘማሪ እገሌ፤ ዘማሪት እገሌ እያሉ ማስታወቂያ ማስነገሩ ምዕመናን በሕብረት ቃለ እግዚአብሔርን እንዲሰሙ፣ ከጠፉበት እንዲመለሱ፣ ከራቁበት እንዲቀሩ፣ ከተበተኑበት እንዲሰበሰቡ፣ ዕዝነ ልቦናቸውን ወደ ንስሐ እንዲመልሱ ለማድረግ ነው፤ በአሁኑ ጊዜ አንዱ መንፈሳዊ ደውል ቢኖር ማስታወቂያ ማስነገር ነው።

ወንድማችን ዲያቆን ዳንኤል በተራ ቁጥር 1 ላይ የጻፈው ነገር ቢሆንም መምህር ግርማን ይወክላችዋልን? ብዬ እንድጠይቅ ያስገድደኛል፤ በእርግጥ ይህንን እንድጠይቅ የሚያስገድደኝ ነገር ደግሞ፦ «ሰው ያለ ተጋድሎ እንዴት ጸጋ ያገኛል። በአሁኑ ዘመን ግን ከተራ ሰዎች የተለየ መንፈሳዊ ሕይወት የሌላቸው ሁሉ እየተነሡ አጥማቂ ሊሆኑ የቻሉበት አሳማኝ ምክንያት የለም።» ተብሎ  ስለተጻፈ  ነው። እዚህ ጋ የመምህር ግርማ ወንዱም ተጋድሎ እንዴት ነው? በጸሎትስ የበረቱ ናቸውን? ወይስ ሐፍተ ፈውስ ብቻ ነው የሚፈጽሙት? መንፈሳዊ ትምህርታቸውስ እንዴት ነው? የሚሉትን ለመመለስ መምህር ግርማ፥ በሬድዮ አቢሲኒያ ቀርበው ስለ እነዚህ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተውባቸዋል። ለምሳሌ ያህል ይህንን እንመልከት፦

የሬድዮ አቢሲኒያ አዘጋጅ አያልቅበት እንዲህ ብሎ ጠይቋቸው ነበር፦ «መምህር የአስተዳደጎ ሕይዎትዎ ምን ይመስላ?»  መምህር ግርማም ለተጠየቁት ምላሽ ሲመልሱ፦ ከልጅነት ጊዜ ቤተ ክርስቲያን በማገልገል አብዛኛውን ጊዜ ያሳለፉት እንደኾነ፤ ስለ ቤተሰባቸው ታሪክ ካወጉ በኋላ እንዴ መንፈሳዊ ሕይወት ውስጥ ሱታፌውን ለመካፈል እንዴት እንዳተኮሩ፤ ወደ መንፈሳዊ ሕይወት ከገቡ በኋላ ደግሞ ሰይጣን እንዴት እንደፈተናቸው፤ በፈተና ውስጥ ደግሞ በመውደቅና በመነሳት ከሰይጣን ጋር ያደረጉት ትንቅንቅ፣ «የሰይጣንን ጥልቅ ጥበብና ምስጢር» የሚያውቁበትን መንፈሳዊ ጸጋ እንዴት እንዳገኙ ተናግረዋል፤ ለማዳመጥ በሬድዮ አቢሲኒያ በክፍል አንድ ላይ በ24ኛው ደቂቃ ላይ ልታረጋግጡ ትችላላችሁ።

በተራ ቁጥር 2 ላይ ደግሞ «ስለ ከንቱ ውዳሴ እና ከከንቱ ውዳሴ ስለ ለማምለጥ የተፃፈ ነው» ይሄም ቢሆንምኮ መምህር ግርማ በቃል ትምህርታቸው ውስጥ፦ «እኔ አዳኝ አይደለሁም፥ ነኝ ብዬ ተናግሬ፣ ተመፃድቄም አላውቅም፤ አገልግሎት እየሰጠሁ እንጂ! የሚፈስና የሚያድው እግዚአብሔር አምልክ ነው!።» ብለው ነው እያስተማሩ ያሉት፤ ሌላው ደግሞ ስለ ውዳሴ ከንቱነት በድጋሚም ባሳተሙት መጽሐፋቸው ውስጥም ቢሁን ይህንኑን የሚያጠናክር ኃይለ ቃል እናገኛለን። እንዲህ ይላሉ፦ «ይህ ሁሉ ሲሆን ግን፤ እኔ ለክርስቶስና ለክርስቶስ ቤተ-ክርስቲያን ኃጢያተኛ ባሪያው እንጂ፤ ከራሴ ሕይወት ምንም የለኝም። የሚያስገርማቹ ነገር ቢኖር ግን "በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊ እንበልጣለን!»  (ሮሜ 87) ለዚህም ዋቢ መጽሐፍ፦ "በማለዳ መያዝ" ገፅ 9 መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ ያሳተሙት።

በተራ ቁጥር 2 ላይ ደግሞ «ስለ ከንቱ ውዳሴ እና ከከንቱ ውዳሴ ስለ ለማምለጥ» የተፃፈ ነው። እኔን ድንቅ የሚለኝ ወንድማችን ዲያቆን ዳንኤል «መንፈሳዊ አገልግሎት» «መንፈሳዊ አገልግሎት» / ለመስማት ይሄንን ይጫኑ/ በሚለው ባስተማረው መንፈሳዊ ትምህሩቱ ውስጥ ይሄንን ሳስብ ድንቅ ይለኛል፤ «መንፈሳዊ አገልግሎት» በትህትና ከሆነ ነው፤ ከትእቢት፣ ከሥልጣን፣ ከክብር፤ እንዚህ ከመሳሰሉት ነገር ነገሮች የራቀ ከሆነና በትህትና እና እራስ ዝቅ በማድረግ የሚደረግ ከሆነ ነው «መንፈሳዊ አገልግሎት» ማለት የሚቻለው። ያ «መንፈሳዊ አገልግሎት» ምድራዊ ክብርን የሚያመጣ፣ ምድራዊ ሥልጣንን የሚያመጣና በምድር ሠዎቹን በጣም ከፍ የያደርጋቸው ከሆነ «መንፈሳዊ አገልግሎት» መሆን አይችልም።  «መንፈሳዊ አገልግሎት» ሆኖ ቢጀመር እንኳ «መንፈሳዊ አገልግሎት» ሆኖ አያልቅም። በዚሁ ትምህር ላይ «ስለ ከንቱ ውዳሴ እና ከከንቱ ውዳሴ ስለ ለማምለጥ» ብዙ አገልጋዮች በሠዎች በከንቱ ውዳሴ እንደወደቁ ሲገልጽ የቀድሞው ባሕታዊ አባ ገብረ መስቀል አጀማመራቸውንና አፈፃጸማቸውን፣ እንዴት እንደወደቁ አስተምሯል፤ ጥሩ፥ እሰየው የሚያሰኝ ነው በማስተማሩ። በዚሁ ትምህርቱ በመምህርነት አንድ ዓመት ባስተማረበት ነዋሪ በምትባል ከተማ ላይ አንዳንድ ሕዝብና አንዳንድ ካህናት ጠንቋይና ወደ ቃልቻ ቤት እየሄዱ እንደሚያስቸግሩ፣ ሆኖም ዲያቆን ዳንኤል፦ «ወደ ጠንቋይና ወደ ቃልቻ ቤት የሚሄዱት ካህናትን ተዉ! አትሂዱ እያለ መንፈሳዊ ግሳፄ እንደሚገስፃቸው፤ ሆኖም እርሱን እንዳልሰሙትና የቀድሞው ባሕታዊ አባ ገብረ መስቀል መጥተው ወደ ጠንቋይና ወደ ቃልቻ ቤት የሚሄዱት አንዳንድ ሕዝቡና አንዳንድ ካህናትን ሰብስበው፦ እናንተ ሕዝቡ ከቃልቻ ቤት እንዳይሄድ ለምንድን ነው የማታስቀሩ? ሕዝቡ ከጠንቋይ ቤት እንዳይሄድ ለምንድን ነው የማታስቀሩ? እናንተ ለምንድን ነው ጠንቋይ ቤት የምትሄዱት? እኔ እዚህ የማያችሁ ካህናት በሙሉ፥ ፊታችሁ የገረጣ፣ ሰውነታችሁ የከሳ፣ እንደው እዚህ ግባ የሚባል ሠውነትና መልክ የሌላችሁ ናችሁ፤ ለምን እንደሆን ታውቃላችሁ? እናንተ መብላት ያለባችሁ ፍትፍት ጠንቋዩ  በላው፣ እናንተ መብላት ያለባችሁ ቅልጥም ጠንቋዩ በላው፣ እናንተ መጠጣት የነበረባችሁ ጠጅ ጠንቋዩ  ጠጣው፤ ለምን ሕዝቡን ሰብካችሁ ብታስቀሩ’ኮ ሠዉ ፍትፍቱን ወደ ጠንቋይ ቤትመውሰዱን ይቀርና ወደ ካህኑ ስለሚያመጣው መልካችሁ ያምራል፣ ሠውነታችሁ ይወፍራል።» ሄይ በእውነት ለዚህ ሀገር ሕዝብ ተስማሚ የሆነ ትምህርት ነው!። እኔ አልረሳሁም ይሄንን ትምህርታቸው፤ ይሄን የመሰሉትን ሠው፥ ሠው ነው ጠልፎ . . . ጠልፎ . . . ጠልፎ . . . የላቸውን ራዕይ ሳያዩ ለምን አያዩም ብሎ ያስጨንቃቸዋል ማየት አለብዎት፣ የሌላቸውን ነገር ከእግዚአብሔር ጋር ተገናኘን እንዲሉ፣ ክንፍ አወጡ፣ በአንድ እግራቸው ቆመው ሲጸልዩ አየናቸው፣ እንዲህ ሲያደርጉ አየናቸው፣ መሬት ተሰንጥቆ ሲሄዱ፣ ሠማይ ላይ ሲወጡ አየናቸው ብሎ የሌለ ታሪክ ሰራና እሳቸውም ልክ ሠው እንደሚላቸውን ለመሆን ሲጥሩ ወደቁ፤ ሕዝብ ጥሩ ጥሩ አገልጋዮችን ነው ያበላሸው። ብሎ ያስተማረው መንፈሳዊ ትምህርት ሳዳምጠው እጅግ እጹብ ድንቅ ነው። ግን ወንድማችን ዲያቆን ዳንኤል ይህንን አንዳንድ ሕዝብና አንዳንድ ካህናትን ወደ ጠንቋይና ወደ ቃልቻ ቤት የሚሄዱትን ለምን አልወቀሳቸውም?

እንደ እኔ እንደ እኔ አሁን ያሉትን አገልጋዮች ከመውደቃቸው በፊት ውዳሴ ከንቱነትን በጥልቀት እንዲረዱት እሻለሁ። መምህር ግርማም ከላይ የተገለጸውን የውዳሴ ከንቱነት ተረድተውታል፤ አንዳንድ ሕዝብና አንዳንድ ካህናት ወደ ጠንቋይና ወደ ቃልቻ ቤት እየይሄዱ በተግሳጽም፣ በምክርም፣ በትምርታቸው፣ እያስተላለፉ ነው። ይሄም ቢሆንም’ኮ መምህር ግርማ በቃል ትምህርታቸው ውስጥ፦ «እኔ አዳኝ አይደለሁም፥ ነኝ ብዬ ተናግሬ፣ ተመፃድቄም አላውቅም፤ አገልግሎት እየሰጠሁ እንጂ! የሚፈስና የሚያድው እግዚአብሔር አምልክ ነው!።» ብለው ነው እያስተማሩ ያሉት፤ ሌላው ደግሞ ስለ ውዳሴ ከንቱነት በድጋሚም ባሳተሙት መጽሐፋቸው ውስጥም ቢሁን ይህንኑን የሚያጠናክር ኃይለ ቃል እናገኛለን። እንዲህ ይላሉ፦ «ይህ ሁሉ ሲሆን ግን፤ እኔ ለክርስቶስና ለክርስቶስ ቤተ-ክርስቲያን ኃጢያተኛ ባሪያው እንጂ፤ ከራሴ ሕይወት ምንም የለኝም። የሚያስገርማቹ ነገር ቢኖር ግን "በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊ እንበልጣለን!»  (ሮሜ 8፥7) ለዚህም ዋቢ መጽሐፍ፦ "በማለዳ መያዝ" ገፅ 9 መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ ያሳተሙት። (እግዚአብሔር አምላክ፥ መምህር ግርማን ወንድሙን ከከንቱ ውዳሴ ይጠብቃቸው)

ይቆየን፤ ይቀጥላል . . .  

5 comments:

  1. የታላቁ አባት ዲዮስቆሮስ በ451 ዓም የኬልቄዶን ጉባኤ የልዮንን የሁለት ባሕርይ ትምህርት አልቀበል ሲል የሮም ባለ ሥልጣናት ‹‹እርሱኮ በቅዱስ ጴጥሮስ መንበር የተቀመጠ የሮም ፖፕ ነውና አለቃህ ነው›› ባሉት ጊዜ ‹‹ሰይጣንም ለቅዱስ ሚካኤል አለቃው ነበረ›› ብሎ ነው የመለሰላቸው፡፡
    ሳንድያጎ፣ ካሊፎርንያ

    ReplyDelete
  2. አሁን በገደምዳሜ ያነሳኸውን የ‹‹አባ›› ግርማ ጉዳይ በሚመለከት ብፁዕ አቡነ ገሪማ በቤተክርስቲያኗ ስም ድርጊቱ ሕገ-ወጥ መሆኑን ከ3 ዓመታት በፊት ለሁሉም አሳውቀዋል፡፡እገዳውን የማኅበረቅዱሳንና የመንበረ ፓትርያርክን ኦፊሴላዊ ዌብሳይቶች ጨምሮ ስለ ኢኦተቤክ እንጦምራለን የሚሉ ብሎጎች ሁሉ--ቀሳጥያኑ ተሐድሶዎች ሳይቀ--ለወረት ያህል ዘግበውታል፡፡ብቻ ግን የቤተክሕነት መዋቅር የሠራውን ሁሉ አጠልሽቶ ድክመቱን ብቻ ማጮኽ ላይ የተጠመደው በቡድንተኝነት የተቃኘው ማኅበራዊ ሚዲያችን እምብዛም አልሄደበት፡፡ያንተ ጽሑፍ ቢዘገይም በኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ የታሸና የኢኦተቤክ በጉዳዩ ያላትን አቋም በደንብ ያንጸባረቀ ስለሆነ እሰጥ አገባውን በቅጡ ጠቅልሎ ለማሳረግ ይረዳል፡፡ቢዘገይም እንኳን ጻፍክ!ጠቅላይ ቤተክሕነት አስተላልፎት የነበረውን ሰርኩላር ማየት ለፈለገ ግን ያውለት፡-


    ቁጥር፡-9474/756/2005 ዓ.ም
    ቀን፡- 8/9/2005 ዓ.ም
    የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
    መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
    ለደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤ/ክ ሰ/ጉ/ጽ/ቤት
    አዲስ አበባ፤
    ጉዳዩ፡- በአስቸኳይ አጥማቂ መምህር ግርማ ወንድሙ በደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ሰ/ጉ/ጽ/ቤት በቁጥር 339/ቀ/አ/ቤ/ክ በ28/8/2005 ዓ.ም የተሰጠው እገዳ መ/ፓ/ጠ/ጽ/ቤት ያጸናው ስለመኾኑ ይመለከታል፤
    መ/ር ግርማ ወንድሙ ሰባኬ ወንጌልና አጥማቂ ነኝ፤ የማዳን ፈውስ አለኝ በማለት በሕገ ወጥ መንገድ እስከ አሁን ድረስ በደብሩ እያጠመቁ ይገኛሉ፡፡
    ይኹንና በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ከ1993 ዓ.ም እስከ 2002 ዓ.ም ድረስ በየወቅቱ በሕገ ወጥ መንገድ የማዳን ፈውስ አለኝ በማለት ሕዝበ ክርስቲያኑን በየደብሩ ቅጽር ግቢ በማሰባሰብ የሚያጠምቁትን በተመለከተ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
    1. ከቤተ ክርስቲያኗ ቀኖና ሥርዐት ውጭ በሚፈጸም ስብከትና ጥምቀት፤
    2. የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ሳይፈቅዱ የሚሰጥ የወንጌልና ጥምቀት አገልግሎት መስጠትን በተመለከተ ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነ ቢኾንም በሥርዐተ አልበኝነት በተለያዩ ቦታዎች የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ሲጣስ ይታያል፡፡
    በመኾኑም መምህር ግርማ ወንድሙ በደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ በሕገ ወጥ መንገድ የሚፈጽሙት ሕገ ወጥ የማጥመቅ ሥርዐትና የወንጌል አገልግሎት መኾኑን እየገለጽን የእምነታችን ተከታይ ሕዝበ ክርስቲያኑ ከዚህ እግድ ጋራ በተያያዘ የጸጥታ ችግር እንዳይገጥመው የሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ጥብቅ ክትትል በማድረግ ውሳኔውን ተግባራዊ እንዲያደርግ እያሳሰብን የሚመለከታቸው የመንግሥት የጸጥታ አካላትም የቤተ ክርስቲያኒቱን ውሳኔ ተግባራዊ በማድረግ ረገድ አስፈላጊው ትብብር እንዲያደርጉልን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
    ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን
    ግልባጭ፤
    • ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት
    • ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪክ ልዩ ጽ/ቤት
    • ለአስተዳደር መምሪያ
    • ለሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
    • ለምሥራቅ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት
    • ለፌዴራል ጉዳዮች ጽ/ቤት
    • ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን
    • ለብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት
    • ለአ/አ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን
    • ለቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ
    • ለአ/አ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ
    • ለቂርቆስ ክ/ከ ፍትሕ ጽ/ቤት
    አዲስ አበባ፤

    ReplyDelete
  3. Memher Girma wondimu keep going God bless ..
    Other guys only lube. ..
    In my life and my family big big change and also Radio Absinia I love you keep going ..you're write
    Ways.

    ReplyDelete
  4. Memher Girma wondimu keep going God bless ..
    Other guys only lube. ..
    In my life and my family big big change and also Radio Absinia I love you keep going ..you're write
    Ways.

    ReplyDelete
  5. THE FIRST THING I LOVE MY PARENT IS BEING ORTHODOX!THE TRUE ROAD THAT WE MUST FOLLOW!

    ReplyDelete