Saturday, December 21, 2013

“ልጃገረዷን በግድ ቢይዛት አፍንጫውን ይፎንኑት (ይቆረጥ)”

                  ለግብረሰዶማውያን ግን ቅጣታቸው ሰይፍ ነው!” አዲስ አድማስ የተወሰደ 

ልጃገረዷን በግድ ቢይዛት አፍንጫውን ይፎንኑት፡፡ ለእርሷም ከገንዘቡ ሲሶውን ይስጧት። አስራ ሶስት ዓመት ሳይሆናት አስቀድሞ ልጃገረዲቱን የያዛትን ሰው አፍንጫውን ይፎንኑት፡፡ ከገንዘቡም እኩሌታውን ለእርሷ ይስጧት፡፡

ይህ ሕግ ነው፤ ሴቶችን ከእንስሳዊ ጥቃት ለመታደግ 570 ዓመት በፊት የተደነገገ፡፡ ዘመኑ የአገራችን ሥነ ጽሑፍ አብቦበት እንደነበረ የሚነገርለት ነው - የአፄ ዘርዓ ያዕቆብ (1434-1468) ዘመነ መንግስት፡፡ ለሥነ ጽሑፉ መዳበር ትልቁን ድርሻ የሚይዙት ከጉንዳንጉዶ ገዳም የተነሱት የአባ እስጢፋኖስና ደቀመዛሙርታቸው አዲስ ሃሳብ ማቀንቀን ነው፡፡ መነኮሳቱ ለሚያነሱት አዲስ ነገረ መለኮት መልስ ለመስጠት ሲባል በርካታ መጻሕፍት በንጉሱ እና በተቃራኒው ወይም በነባሩ አስተሳሰብ መመራትን በሚሹ መነኮሳት ይጻፉ ነበር፡፡

ፍትሐ ነገሥትየተባለው የሕግ መጽሐፍ ሥራ ላይ የዋለውም ከዚያ የፍትጊያ ዘመን ጀምሮ ነው፡፡ 1923 . በወጣው ሕገ መንግሥት እስከተተካ ድረስም ለአራት መቶ ሰማንያ ዘጠኝ ዓመታት መንግሥትና ሃይማኖት/በተለይ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት/ በተግባር ሲያውሉት ቆይተዋል፡፡

ዛሬየሕግ ትምህርት ቤትእንደሚባለው ድሮ ፍትሐ ነገሥት ራሱን ችሎ ወይም ከትርጓሜ መጻሕፍት ጋር በአንድ ጉባኤ ትምህርቱ ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ ፍትሐ ነገሥት የተማሩት ሊቃውንትም ከነገሥታቱ የፍርድ አደባባይ ላይ በመገኘት ነገሥታቱ በፍትሐ ነገሥቱ ህግጋት መሠረት የፍርድ ሥራቸውን እንዲያከናውኑ ያግዙ ነበር፡፡

Friday, December 20, 2013

ሥራህን ሥራ፦ በብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ



ሥራህን ሥራ፦ ጌታ ለእያንዳንዱ ሰው ሥራ ሰቶታል፤ ያንን መስራት የእሱ ፈንታ ነው። ቢቻለው እሱን ማገድ የዲያብሎስ ሥራ ነው። በርግጥ ሥራውን እግዚአብሔር እንደሰጠህ ያህል ሰይጣን ሊያግድህ ይጥራል። ሌላ ነገር በበለጠ ደስ የሚያሰኝ ሊያቀርብልህ ይጥራል፤ በዓለማዊ ተስፋዎች ያባብልሃል። የሃሜት ጎርፍ ያስወርድብሃል። ደራሲያን እንዲጠይቁህ፣ እጅግ ስመጥር ሰዎችም በክፉ እንዲናገርብህ ይጠቀምባቸዋል።

ጲላጦስ፤ ሔሮድስ፤ ሐናንያ፤ ቀያፋ ሁሉም በአንተ ላይ ያድማሉ። ይሁዳም በአጠገብህ ቆሞ በሰላሳ ብር ሊሸጥህ ይከጅላል። ይሄ ሁሉ የደረሰብህ ሰይጣን በዚህ ከስራህ ሊስብህና እግዚአብሔርን ከመታዘዝ ሊያሰናክልህ መሆኑን ልትገነዝብ አትችልምን?
ሥራህን ሥራ፦ አላማህ እንደ ኮከብ የጸና ይሁን ተወው አለም እንደፈለገው ይነታረክ ይጨቃጨቅ፡፡ አንበሳው ሲያጋራ ፍንክች አትበል የሰይጣንን ውሻዎችን ለመውገር አትቁም፡፡ ጥንቸሎችን በማባረር ጊዜህን አታጥፋ

ሥራህን ሥራ፦ ዋሾች ይዋሹ፣ ጠበኞች ይጣሉ፣ ማህበሮችም ይወስኑ፣ ደራሲዎችም ይድረሱ፤ ሰይጣንም የፈለገውን ያድርግ። አንተ ግን ምንም ነገር እግዚአብሔር የሰጠህን ሥራ ከመፈፀም እንዳያግድህ ተጠንቀቅ።

ሥራህን ሥራ፦ ገንዘብ እንድታተርፍ አልተላክህም፣ እንድትበለጽግም አልታዘዝክም፣ ለክብርህ ተከላከል ብሎ አልተነገረህም፤ ሰይጣን አገልጋዮቹ የሚነዙትን የሐሰት ወሬ እንድታስተባብል አልተጠየቅህም እነኚህን ሁሉ ነገሮች ብታደርግ ሌላ ሥራ ልትሰራ አትችልም፤ ይህም ብቻ ሳይሆን ለራስህ እንጂ ለጌታ አልሰራህም።

ሥራህን ሥራ፦ አላማህ እንደ አለት የፀና ይሁን፣ ጥቃት ይደርስብህ፣ ትበደል፣ ትሰደብ፣ ትታማ፤ ትቆስልና ትናቅ ይሆናል። አንተ ግን በፀና ውሳኔ የማያወላውል ቅናት በመጨረሻ ላይ ፀንተህየሰጠኽኝን ሥራ ፈፀምኩ ሃይማኖትንም ጠበቅሁ” ለማለት እስክትችል ድረስ የሕይወትህን አላማና የተፈጠርክበትን ግብ ተከትል።

  --------------------------------------------------------------------------------
        (ምንም ብታደርጉ ሠዎች *በአራቱም አቅጣጫ* ከማውራት ስለማይመለሱ ዝም ብላቹ ሥራችሁ ላይ ትኩረት አድርጉ!!!)
   ---------------------------------------------------------------------------------

Wednesday, December 11, 2013

አንደበተ ርቱዕ፥ አባ ፍስሐ



       ከደብረ ሊባኖስ ወደ አብተ ማርያም ገዳም ለመድረስ በእግር ጉዞ መሄድ ግድ ይላል። የመድረሻ ሰዓት፥ እንደ እግር ተገዦች (እንደሰዎች) ፍጥነት ይለያያል። እኛ ግን ወደ አንድ ሰዓት ከአርባ ደቂቃ አካባቢ ፈጅቶብን ደረስን።

በዛም፥ በአብተ ማርያም ገዳም አካባቢ ከሚኖሩ አበው ዘንድ ጎራ በማለት አባ ፍስሐ አገኘናቸው። እርሳቸው በመንፈሳዊ ሕይወታቸው የበቁ አባት ናቸው። አባ ፍስሐ፥ ምክራቸው፣ ተግሳፃቸው፣ ትምህርታቸው፤ እጅግ እጹብ ድንቅ ነው።

ከአንደበታቸው በሚወጣው ፍጹም መንፈሳዊ ምግብ፦ ነፍስህ ሐሴት ስታደርግ ታስተውላለህ፣ ሕይወት ትማረካለች፤ ተመስጧቸው፥ ህሊናን ወደ መንፈሳዊ ተመስጦ ውስጥ ይመራዋል፣ በመንፈሳዊ ተጋድሎዋቸው የሕይወታቸው ምርኮኛ እንድትሆን አንዳች የመንፈስ ቅዱስ ምሪት ያነሳሳሃል። እድሜያቸውን በሙሉ ለእግዚአብሔር አገልግሎት የገበሩ አባት ናቸው።


ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ፥ መጽሐፍ ቅዱስን፣ በቅዱሳት ሥእላት ትሰብካለች!

      ህንደኬ፥ የተባለች፣ የኢትዮጵያ ንግሥት አዛዥና ጃንደረባ የነበረ፣ በገንዘብዋም ሁሉ የሠለጠነ፣ ኢትዮጵያዊ ሰው፤ በነብየ ኢሳያስ የተተነበየውን የመድኃኒታችንና የአምላካችን፣ የኢየሱስ ክርስቶስን፤ የትንቢት ቃሉ ሲያነብ፥ በቅዱስ ፊልጶስም አማካኝነት፣ የቃሉን የትንቢት ምስጢር ከነ-ትርጓሜው የተተረጎመለት፤ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ (አገልጋይ)


    በሙሉ ልቡ፥ ያመነና የተቀበለ፣ የተጠመቀና በእግዚአብሔር ጃንደረቦች (አገልጋዮች) በነብያትና በሐዋርያት ቃል የታነጸ፤ በተመስጦ ባነበበው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ልቡ ደስ ያለው፤ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ (አገልጋይ) /ኢሳ 534-9 ሐዋ 826-40/


Sunday, December 1, 2013

ከጽጌ ስጦታው እና ከመሰሎቹ ተጠበቁ!!!


[ቅ/ሲኖዶስ በተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅነት ካወገዛቸው፤] ከግለሰቦቹ ከአስራ ስድስቱ አንዱ ጽጌ ስጦታው ነው።

 "ሰውን ማስታመም የሚቻለው በምግባር ድክመቱ እንጂ በሃይማኖት ክሕደት አይደለምና!” /ብፁዕ አቡነ አብርሃም የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ ለሀ/ስብከታቸው ሰባክያነ ወንጌል እና ምእመናን ይፋ ሲያደርጉ ከተናገሩት/ (ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 9/2004 .ም፤ ጁን 16/ 2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF) የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ለቤተ ክርስቲያንና ለሃይማኖት ጉዳይ በተለይም ለምእመናን አንድነት ቅድሚያ በመስጠት፣ በጉዳዩ ላይ በስፋት በመነጋገር፣ ግንቦት 15 ቀን 2004 .ም፣ በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅ ድርጅቶች፣ ግለሰቦች እና መጽሐፎቻቸው ላይ በአንድ ድምፅ ያስተላለፈውን የውግዘት ውሳኔ የያዘው ቃለ ጉባኤ ለመላው አህጉረ ስብከት ተሰራጨ፡፡ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት /ቤት ሰኔ 7 ቀን 2004 .ምሰ ጀምሮ በሀገር ውስጥና በውጭ ለሚገኙ 48 አህጉረ ስብከት ባሰራጨው ቃለ ውግዘት የተካተቱት መናፍቃን ድርጅቶች ሰባት ሲኾኑ የግለሰቦቹ ብዛት ደግሞ 16 ነው፡፡ ከግለሰቦቹ ከአስራ ስድስቱ አንዱ ጽጌ ስጦታው ነው።
 
"ልጆች ሆይ፥ መጨረሻው ሰዓት ነው፥ የክርስቶስም ተቃዋሚ ይመጣ ዘንድ እንደ ሰማችሁ አሁን እንኳ ብዙዎች የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ተነሥተዋል፤ ስለዚህም መጨረሻው ሰዓት እንደ ሆነ እናውቃለን። ከእኛ ዘንድ ወጡ፥ ዳሩ ግን ከእኛ ወገን አልነበሩም፤ ከእኛ ወገንስ ቢሆኑ ከእኛ ጋር ጸንተው በኖሩ ነበር፤ ነገር ግን ሁሉ ከእኛ ወገን እንዳልሆኑ ይገለጡ ዘንድ ወጡ።" /1 ዮሐ 218-19/

እነ ጽጌ ስጦታው እና መሰሎቹ፤ የጥበበኞችን ጥበብንከንቱ የሚያድርግ ጌታ፤ ለነብዩ ሲራክ የገለጠለት፦ "ገንዘብህን በከንቱ አትበትን፤ በቃኝም አትበል" /ሲራክ 51/ የሚለውን በመምዘዝና ላልተገባ ትርጎሜ ጠቀሙበት መጽሐፍ ቅዱስን ልብ አለማለታቸ አያስደንቀንም፤ ምክንያቱም ቀድሞኑን "ሐሰተኛ ወንድሞች" ስለሆ ነውና።