Wednesday, June 4, 2014

ለእምነት የሚከፈል ዋጋ!!!

(ሪፖርተር፥ ግንት ፳፯/፳፻፮ ዓ/ም 04 June 2014)

‹‹እምነትን ማዛባት፤ ጭካኔ ተሞልቶበታል የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮን

‹‹ጉዳዩ ውስብስብ ነው፣ ጎሳንና ማኅበራዊ ሕይወትን ይነካካል፤ በመሆኑም የሞት ፍርዱ ተፈጻሚ አይሆንም›› የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትሩ አብዱላህ አል አዝራቅ

ከእስልምና ወደ ሌላ ዕምነት መቀየር ፍፁም የተከለከለ ነው፡፡ ዕምነት የሚፀናውም በአባት ነው፡፡ ልጆች ከሙስሊም አባት ከተወለዱ የእናታቸው ዕምነት እስልምና ካልሆነ በስተቀር የፍላጎታቸውን ዕምነት መከተል አይችሉም፡፡

ለዕምነት የሚከፈል 70 በመቶ በላይ ሕዝቧ የእስልምና ዕምነት ተከታይ በሆነባት ሱዳን የሌላ ዕምነት ተከታይም ቢሆን ትዳሩን ሲመሠርት የሚዳኘው በእስልምና ሕግ ነው፡፡ ክርስቲያን ሆኖ ሙስሊሟን ቢያገባ ልጁን የማሳደግ መብት አይኖረውም፡፡ ሚስቲቱም ሃይማኖቱ የሚያዛትን እንደጣሰችና ዕምነት እንደቀየረች ተቆጥራ በወንጀል ሕግ ትዳኛለች፡፡

በሱዳን የእስልምና ሃይማኖትን በሌላ ዕምነት የቀየረ የሚፈረድበት ሞት ነው፡፡ በአፍጋኒስታንና በሌሎችም የእስልምና መንግሥት ያላቸው አገሮች እስልምናን ከመቀየር ጋር በተያያዘ የሚወስኑት የሞት ፍርድ ከሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ በሙስሊም አስተምርሆ ውስጥ ሆነው ባህላዊ አካሄድ ነው በማለት ቅጣቱ ሞት መሆን እንደሌለበት ከሚናገሩ፣ እንዲሁም ከሌሎች ዕምነት ተቋማት ጋር ሁሌም እንዳወዛገባቸው ነው፡፡

በመንግሥት ተቋማት ደረጃ ብቻም ሳይሆን የእስልምና እምነቱን የቀየረ ወይም የቀየረች ሲገኝ ወይም ስትገኝ በመደበኛ ፍርድ ቤት ደረጃ ሳይደርሱ በአካባቢያቸው ነዋሪዎች ፍርዱ የሚፈጸምባቸውም ቀላል አይደሉም፡፡ በተለይ ደግሞ ሴቶች የብትሩ ሰለባዎች ናቸው፡፡

ሰሞኑን በሱዳን ካርቱም አከራካሪና አነጋጋሪ ሆኖ የከረመው አጀንዳም ይኼው ነው፡፡ ከኢትዮጵያዊት ክርስቲያን እናትና ከሱዳናዊ ሙስሊም አባት የተወለደችው ማርያም ያህያ ኢብራሂም ክርስቲያን ማግባቷ ከስህተት ተቆጥሮባት እስር ቤት እንድትገባ፣ 100 ጅራፍ እንድትገረፍና በሞት እንድትቀጣ እንዲወሰን ምክንያት ሆኖባታል፡፡

Sunday, June 1, 2014

"ጠንቋይና አስጠንቋይ" በመልአከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ ሺፈራው


,,, እንዲህ የሚያስጨክን፥ የማይገባ ሥራ የሚያሰራ ሰይጣን ነው። በየ-አንዳንዱ ጎጆ (መኖርያ ቤት) ውስጥ ቢገባ ብዙ ጉድ አለ! ተስፋውን በጥንቆላ ላይ አድርጎ የሚኖር፣ ጠንቋዩ፥ በመከረው ምክር የሚመላለስ፣ ያንን በይፈጽም እንደው ዕለቱን መሬት-ተከፍታ የምትውጠው የሚመስለው አለ። በጥንቆላ፣ በመተት፣ በአስማት፤ ወገኖቻቸውን የሚያሳብዱ፣ ወገኖቻቸውን የሚገድሉ፣ ወገኖቻቸውን የሚያፈዙ፤ ጥቂት አይደሉም።

እገሌ እኮ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ነበረ፤ አሁን ግን ጨርቁን ጥሎ የሚኼደው። ምን ነካው? "ጓደኛው ነው ያቀመሰው አሉ" ይባላል። እገሌ እኮ ጥሩ ደሞዝ ነበረ፣ እንዲህ ዐይነት ቦታ ይሠራ ነበር፤ አሁን እንዲህ ከንቱ ኾኖ ቀረ። ምን ኾነ? "ጓደኛው ነው እንዲህ ያደረገው" ይባላል። እገሌ እኮ እንዴት ያለ ነጋዴ ነበረ፣ ቢጠሩት የማይሰማ፤ አሁን ግን ከንቱ ኾኖ ቀረ። ምን ኾነ ታዲያ? "አይ፥ በንግዱ የቀኑበት ሠዎች ናቸው እንዲህ ያደረጉበት" ይኼንን ነው የምንሰማው።

በአካባቢው፥ በመንደሩ፤ የሚነገረው ይኼ ነው። ጠንቋይ፥ ቤት የሚያድረው ሕዝብ፣ ቃልቻ፥ ቤት የሚያድረው ሕዝብ፤ ብዛቱ፥ ቁጥር-ስፍር የለውም። ምንድነ ነው የሚሻለን ታዲያ? የእግዚአብሔርን ቃል፥ አልሰማንም እንዳንል፤ ሰምተናል! ተአምራቱን፥ አላየንም እንዳንል ዐይተናል! ግን ሰምተን እንዳልሰማን ኾንን፣ ዐይተን እንዳላየን ኾንን! የአንዳችንም ሕይወት ሲለወጥ ዐይታይም።

ተማሪው፥ "ትምህርት እምቢ አለኝ" ሲል፤ እንደው፦ "ጠንቋይ ቤት ሂድ ጠንቋዩ ይነግርሃል፤ እቃልቻው ቤት ብትሄድ ይነግርሃል" ይባላል፤ እውነት መስሎት ይሄዳል። ነጋዴውም፥ "ንግድ እምቢ አለኝ ምን ማድረግ ይሻለኛል" ሲል፤ "እጠንቋዩ ጋር ብትሄድ፤ እቃልቻው ቤት ብትሄድ" ይባላል። መሪ፥ መካሪ አለው እርሱም (ርኩስ የሰይጣኑን መንፈስ) ሥራ፥ ፈልጌ፣ ፈልጌ አጣኹ፤ ምን ይሻለኛል? ሲል፤ "እጠንቋዩ ጋር ብትሄድ፣ እቃልቻው ቤት ብትሄድ፤ ሥራ ታገኛለህ" ይኼ ደካማ ሕዝብ ሥጋዊ ፍላጎቱን ለሟሟላት ሲል፥ ሃይማኖቱን ሽጦ፣ ለውጦ፤ ከአምልኮተ እግዚአብሔር ሲንሸራተት፣ ሲያፈገፍግ ይታያል።

እንደው፥ ዘመኑ ዓመተ ምዕረት ኾኖ፤ እግዚአብሔር፥ ኃጢያት፣ በደላችንን ሸፍኖልን ነው እንጂ! የእየ-አንዳንዳችን ኃጢያት በየግንባራችን የሚፃፍ፣ የሚገለጥ ቢኾን ኖሮ ከእኔ ጀምሮ ኹላችንንም ብንኾን ከዚህ ቦታ ባልተገኘንም ነበር! እንደውም፥ ጥንቆላ የተስፋፋበት ዘመን ነው። በየ-ጋዜጦች ላይ የምናነበው፤ ጥንቆላ አይደለ? ወይስ የእግዚአብሔር ነቢያት ነው የፃፉልን? ትንቢተ ማን እንበለው? ግራ-የሚገባ (የሚያጭበረብር) ነገር እኮ ነው።

Monday, May 19, 2014

ቅን ትችት፥ ለሚቀበለው ሠው፦


      ቅን ትችት እንዴት ደስ ይላል፣ ቅን ተቃውሞም ልብን ያረሰርሳል በንዴት ለጦፈውም፣ በኃይል ለተነሳው በቃ፥ ብሎ ቁርጥ-ውሳኔ ለቆረጠው ኅሊናው፥ እንዲሟገተውና ወደ ራሱ እንዲመለከት ያግዘዋልከቀየሰ ት ጐዳናም ይታደገዋል!።

 
 

 

Wednesday, May 14, 2014

የሠው፥ ልዩ ዘር ኧረ ወዴት አለ?


ገበሬው አውድማው እህል ማረስ፤
አፈሩ ተኰተዋ እንዲለስለስ፤
ሩን ይዘራዋል በስብሶ እንዲፈርስ፤
ቃያሲያፈራ ማሳው ሲደርስ።

በዘራው የእህል በዓይነት
እዪ ሐሴት ያደርግ ገበሬው ሲደሰት

አንዳችን ስለ አንዳችን፣ በፍቅር ዓለም ከተዋደድን፤
ልዩነት ከየት ይመጣል፣ በሕይወት ሥር ከሰደድን፤
ዘር ቆጠራ፥ ለእህል እንጂ! ለእኛ ለሠዎች አይኹን፤
በፍቅርና በአንድነት መኖር፣ ቆየን ከተለማመደን።

ገበሬው በዘራው የእህል ዘር ፍሬ መደሰት፤
ያለʼውን፥ አንድነትና ልዩነቱን እንመልከት።

እንዳንኾን፥ ታሪካን ለማፍረስ፤
በልባችን፥ የፍቅር ዘርን እንረስ፤
ኅሊናችን፥ ለሌላው ሲለሰልስ፤
እንደሰታለን ፍሬው ሲደርስ።

የእህል ዘር፥ ዓይነቱ ብዙ
የሠው ዘሩ፥ ኧረ ወዴት ?

አፋልጉልኝ፥ የእከሌ ዘር ነኝ ያላለ፤
ይኼ ነው! ልዩ ሠው ለፍቅር የዋለ፤
ፍቅር፥ መተሳሰብና አንድነት ካለ፤
የሠው፥ ልዩ ዘር ኧረ ወዴት አለ?

ለሃገ አንድነት፥ ኹሌ የሚናፍቀው፤
ባንዲራዋን፥ በፍቅር የሚመለከተው። 
                 
ራሱን ጥቅም ይልቅ ለአንዲት እምዬ ኢትችን፤                                                    
የወንዙና የሸንተረሩን ጐጥ ብቻ ያልተመለከተውን፤
ሳዩኝ ይኼን ሠው፥ኢት ዋጋ የከፈለውን፤
ይኼ! ለ ሃገ አንድነትን የሚሻውን።      

በህብረ-ቀለማት ፍቅሩ የረሰረሰና ለሃገ
ለኢትዮጵያችን፥ ይኼ ሠው ታላ

ወዳጄ ሆይ፦ ራስህን በመውደድህ፤
ትኖራለህ፥ ሌላውንም ታከብራለህ፤
ለሃገርህም ሠላምና ፍቅርን ትሻለህ፤
ግርማና ክብርበነቷንም ትናፍቃለህ።

ክብርን ለማግኘት ተቀይሶ የዋለ
የሠው፥ ልዩ ዘር ኧረ ወዴት አለ?

እኔ፥ ከዚህ ዘር ነኝ እንዳንባባል፤
ኹላችን ከአዳም ዘር ተወልደናል፤
ከማይጠፋው ዘር ተገኝተናል፤
ክርስቶስ ፍቅርን አስተምሮናል።

(//፳፻፮ /)

Friday, May 9, 2014

ዝክረ ቅዱሳን፦ ማርያምን!!!



በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን!

ወዳጄ ሆይ፦ አንተ አመልከዋለሁ የምትለው አምላክ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ከኾነ፦ ትንቢት የተነበየለት፣ "የዘመኑ ፍፃሜ" ከሴት ብሎ ከእናቱን ከቅድስት ድንግል ማርያምን በሥጋው እንደተወለደ፣ በጌታ ዘንድ ጻድቅና ትጉህም የነበሩ፣ ኢየሱስ ክርስቶስን ከእናቱ ጋር አብረው እንደባረኳት፤ እናነባለን እንጂ ክርስቶስን ብቻ እንባርክ አላሉም! /ሉቃ ፪፥፳፭፤ ገላ ፬፥፬/ ማርያምን!!!

በጌታ ዘንድ ጻድቅና ትጉህም የነበሩ ከባረኳት፣ ለጌታችን፣ ለመድኃኒታች፣ ለኢየሱስ ክርስቶስ ለሥም አጠራሩ ክብርና ልዕልና፣ ውዳሴና ምስጋና፤ ይገባውና አንድ ጊዜ የመረጣቸውን ሐዋርያት እንዲኾኑ ወስኗል። ለዚኽ ነው፥ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ፤ በሮሜ መልዕክቱ፦ "ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤ አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው፤ የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው፤ ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው። እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?" /ሮሜ ፰፥፳፱-፴፩/ ሲል አንድ ጊዜ የመረጣቸውን እስከመጨረሻው እንዳከበራቸው ይገልጽልናል። ማርያምን!!!

እራሱ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ "እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ።" ያለበት ያለ ምክንያት አይደለም! ክርስትና መምሰልና መኾኑ እንዳለብን ሲያስገነዝበን ይህን ተናገረ። /፩ኛ ቆሮ ፲፩፥፩/ አንድ ክርስቲያን፥ ክርስቶስን አምላኬ ነው ካልን፤ መምሰል ደግሞ ግድ ይላል! ያውም፥ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ መምሰልና ኾኖ መገኘት! ማርያምን!!!

እንደዚህ ዓይነቱ መምሰል ደግሞ  የቅዱሳንና የፃድቃንን መትጋትና ተጋድሎ አይቃወምም! ቅዱሳንን ማክበር ከዚኽ ይጀምራል። ዓይነ-ሥውራኖች (ዓይነ-ለሞች) እኮ መዳን ቢፈልጉ "የዳዊት ልጅ ማረን" እንዳሉ ልብ ማለት ይገባል! /ማቴ ፱፥፳፯፤ ፲፭፥፳፪/ "የዳዊት ልጅ" የሚለው የመጠሪያ ሥም በመንፈሳዊ ዕይታ እንዴት እንደቀደመ ማገናዘብ ይጠይቃል። ለዚኽም ነበር ቅዱስ ማቴዎስ የቅዱሳንን ተጋድሎ ከመናገሩና ከመፃፉ በፊት፤ የወገናቸውንና የአባታቸውን ሥም በማስቀደም በመጥራት ይጀምራል። ለዚኽም አንድ ማሳያ እንዲኾነን፦ "ከአሴር ወገንም የምትሆን የፋኑኤል ልጅ ሐና የምትባል አንዲት ነቢይት ነበረች፤ እርስዋም ከድንግልናዋ ጀምራ ከባልዋ ጋር ሰባት ዓመት ኖረች" ይላል። /ሉቃ ፪፥፴፮/ ማርያምን!!!

እንዲኹ ደግሞ፦ በቅዱሳን መንፈስና ክርስቶስን በመምሰል፤ የእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን እናትና አባቷ የነበራቸው መንፈሳዊ ተጋድሎና ሕይወት፣ ስለ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፥ ፅንሰትና ውልደት፣ ሕይወቷና አጠቃላይ መንፈሳዊ ተጋድሎዋ ቢሰበክና ቢፃፍ፤ የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፦ እግዚአብሔር፥ የጠራቸውን፣ ያጸደቃቸውን፣ ቅዱሳንን ማክበርና ተገቢ መኾኑን ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ አስረግጦ ገልፆ አስተምሮናል። (በነገራችን ላይ፥ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያናችን ለሌሎችም ቅዱሳን በዓላቸውን ታከብራለች) ስለዚኽ፦ እግዚአብሔር፥ የጠራቸውን፣ ያጸደቃቸውን፣ ቅዱሳንን አለመቃወማች አስረግጠን እንገልጽለን እንጂ! አንቃወምም! ማርያምን!!!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወድንግል ማርያም ክብር፤ አሜን! (//፳፻፮ /)