Monday, October 14, 2013

ምርጥና እጹብ ድንቅ አስር የአብው ብሂላዊ ምክር፦



1. ትግል፣ ተናና መከራ ከሌሉ የድል አክሊል፤ ጠላት ከሌለ ድል ማድረግ አይቻልም። /ታላቁ ባስልዮስ/

2. በመንፈሳዊ መንገድ ውስጥ ዝግ ብለህ አትጓዝ። በጎዳና ላይ በምትመለከታችው ትዕይንቶች አማካይነት አትማረክ፤ አትቁምም ጠላቶችህም ሆኑ ወዳጆችህም ያሰናክሉህ ዘንድ አትፍቀድላቸው። /አቡነ ሺኖዳ/

3. የከበሩ አባቶቻችን ልጆች ልትሆኑ ከወደዳቹሁ እነርሱ የጻፉትን (ያስተማሩት) እንጂ ምንም ሌላ አትመኑ። /ቅዱስ አትናቴዎሰ/

4. ጠላት በበዛበት ቦታ የምኖር ከሆነ ብርቱ ወታድር እሆናለሁ። /አባ ጴሜን/

5. ፍቅር፦ በእውነት ሰማያዊ ኀብስትና የአእምሮ ምግብ ነው። /ቀለሜንጦስ ዘእስክንደርያ/

6. ከሰው ተለይቶ ወንድሙን የሚመክር ሰው እነሆ የፍቅሩን ጽናት ብዛት ያስረዳል፤ ባልንጀሮቹ ፊት የሚነቅፈው ግን የቅናቱን ጽናት ያስረዳል፣ የምቀኝነቱን ጽናት ያስረዳል። /ማር ይስሐቅ/

7. ፍቅር፦ መያዣ የሌለውን የሰው ልብ አስሮ ለመሳብ የሚያገለገል የሠላም መንገድ ነው። /አንገረ ፈላስፋ፤ ሊቀ መዘምራን ሞገስ ዕቁበ ጊዮርጊስ/

8. አሁን የምንኖራት ሕይወት ምን ያህል ውድ እንደሆነች ልታውቅ ትወዳለህን? ይህች ሕይወት ለዘለዓለማዊ ሕይወታችን መሠረት የትግል ዐውድማ፣ እንዲሆም በገነት ያለችውን አክሊል የምትሰጥ ናት። /ዮሐንስ አፈወረቅ/

9. ልማት ማለት መሬትን መቆፈር ብቻ አይደለም። የሰውን ልቦና በትምህርተ ወንጌል ቆፍሮ ማለምለም፣ በሰው አእምሮ ፍቅርና ስምምነት መዝራትና መትክል፣ ሰውን ከስህተት መመለስና ማስተማር፤ ከልማቶች ሁሉ የበለጠ ነው። /ብፁዕ አቡነ ጳውሎስ/

10. የትሕትና ከፍታ እጅግ ታላቅ ነው፤ የመታበይ ጥልቀት ደግሞ እጅግ ጥልቅ ነው፤ የመጀመረያውን እንድትከተል፥ ወደዚህኛው ደግሞ እንዳትወድቅ እመክርሃለሁ። /አባ ኤስድሮስ/


ዋቢ መፅሐፍ ብሂለ አበው 2005 @ማኅበረ ቀዱሳን

No comments:

Post a Comment