Tuesday, May 6, 2014

ሂሰ-ሐሳብ


ሰማነው ገና ከተራራው ከዱሩ ከጫካው፤
ያኔ ያኔ በወቅቱ የነፃነት ታጋይ አርበኛው፤
በጩኸትና በብሶት ዓላማውን ያሰማው፤
ጭቆና በዛ፣ ደም ፈሰሰ፣ ብሎ የነዛው።

ፍላጎቱ ሠመረ ሃገረ ኢትዮጵያን ተረከባት፤
በብሔረሰቦች የደመቀች የህብረ-ቀለማት፤
ታላቋ ኢትዮጵያ የሠላምና ፍቅር ሃገር ናት፤
ለኹሉም የምትመች ናት ያላት ልዩ ውበት።

የእውነት ናት ሠላማዊት ሃገረ ኢትዮጵያ፤
ብዙዎችን ያስጠጋች የዕረፍት መጠለያ።

ውሎ አድሮ ነገር-ተጐንጉኖ ተሸበረ፤
ከኢትዮጵያዊነት ይልቅ ፓርቲ ከበረ።


አብዮት ተገርስሷል፣ ነፃነት፥ አለ ተብሎ ፖለ ተነዛ፤
ከባለፉት ዘመናት ይልቅ፣ አኹን ስቃይና እንግልት በዛ፤
የሕዝብን ነፃነት መብት በሌላ ስም መለወጥ እጅግ በዛ፤
ምን አጥፍተን ይኾን የምንቀጣው ያለጥፋት እንደዋዛ።

ከእርሷ ፓርቲ የሌሉ ሠዎችን በዓይነ-ጎጥና በቅስፈት፤
ዓይኗን አፍጥጣ ትመለከታቸዋለች ልክ እንደ ጠላት።

መቼ እጠላ ነበር የነፃነት ሕግ ኾና ብትሰላ፤
ሕጓ ብልጥ ኾናለች የበላይ በዘዴና በመላ።

መንግሥት በዳይ ሕዝብ ተበዳይ ኾኖ ሲመጣ፤
የሃይማኖት መከበርና ግርማ-ሞገሷን እንድታጣ፤
ከመንግሥት የተለየች ናት ተብላ በሕግ ተቀምጣ፤
ሃይማኖት እንዳትተነፍስ ተከልክላለች ወይ ጣጣ።

እጁን በየቤተ-እምነትና ሃይማኖት፤
አሰማሩ የራሳቸውን ሼኪና ካህናት።

አንተ ወዳጄ በወኅኒ እስር ቤት ያለኸው፤
እንደው ኅሊናህን ሊያስሩት አይቻላቸው፤
በዓይነ-ኅሊናህ እነ-ማንዴላን አስታውሳቸው፤
እውነቱን ተመልከት ያሰሩኽ ሥጋህን ብቻ ነው።

ወዳጄ ሆይ እስትህ ፈታለህ፤
አለች፥ አንድ ን፣ ህ፤
ኹሌም አስባት፥ ስትይዝ በስልጣንህ፤
ያሳለፍኸው የወኅኒ ቤት ቆይታህ።

ሐሳብህን አፍልቅ ምልከታ ተናገር ለኢትዮጵያችን፤
ኹሉም ሂሰ-ሐሳብ ይጠቅማል በመከባበር ለሃገራችን።

በኅሊናህ የሚብሰለሰለው፤
በአዕምሮህ የሚመላለሰው፤
በአንደበትህ ልሳን ተናገረው፤
ቢቻልኽ በብራና ክተበው።

ሪክ በረዝ፣ ነ ያለው ክፉ እንግልታችን፤
በዘመናችን የሚከናወነውን፣ ሥቃይና መከራችን፤
ለመጪው ትውልድ፦ እውነተ ሪክ እንዲኾን፤
እንዘግበው፥ ዓይችን ናየውን ሰቆቃችንን።

መቼ እጠላ ነበር የነፃነት ሕግ ኾና ብትሰላ፤
ሕጓ ብልጥ ኾናለች የበላይ በዘዴና በመላ።

(መታሰያነቱ፦ አኹኑ ሥርወ-መንግሥት *በሥልጣነ-ኢአህዴግ ዘመነ መንግሥት* በፖለቲካ ሂሰ-ሐሳብ ምክንያትና በተለያየ ምክንያት፤ ከሚወዷትና ከሚያከብሯት ውዷና ኹልጊዜ ተናፋቂዋ ሃገራችን ኢትዮጵያ፤ በሂሰ-ሐሳባቸው ምክንያት፦ በስደት፣ በወኅኒ ቤት፣ በቁም እስርና በተለያየዩ እንግልትና ስቃይ ለሚደርስባቸው ውድ ወገኖቼ፤ በስደትም ያሉትም ይኹን በሃገር ቤት ላሉት፤ ማስታዎሻ ይኹንልኝ።)

No comments:

Post a Comment