Tuesday, June 24, 2014

ሆ ማርያም ጽናትሽ፦



ተወልደሽ ከአባት ከእናትሽ፤
ከኹለት ቤተ እምነት ኾንሽ።

ከፍትሕ ፊት ቢያቆሙኝ፣
የክስ ፋይል ቢከፍቱብኝ፣
አንገቴን አቀርቅሬ አዳመጥኹኝ፤
ዳኛው ተናገሩ በቃ ትገደል አሉኝ።

በሕይወት ለመኖር፥ እድል ቢሰጠኝ፣
ለውሳኔ፥ ሦስት ቀን ብቻ ቢታወጅብኝ፣
በሃይማኖቴ አልግደረደርም ክርስቲያን ነኝ፤
አዋጁን ሰምቼ በአርምሞ ልቤን አጸናሁኝ።

ልቤ አይደነግጥም እጸናለሁ በአማላጁ፤
የማይተወኝ ገብርኤል ይቆማል ከደጁ።

ከትንታግ እሳት፥ የሚታደገኝ፣
ገብርኤል ነው ስሙ እወቁልኝ፣
የኢየሱስ ልጁ ነኝ የማይተወኝ፤
አለ የድንግል ልጅ ምንም አይነካኝ።

ምን እኾናለው ብኖርም ብሞትም፤
እኔ የኢየሱስ ነኝ አልደነገጥኹኝም።

ሆ ማርያም፦ ጽናትሽ ሃያልና ድንቅ ነው፣
የሃይማኖት ጽናትሽን እንዴት ተማርሽው፣
ሆ ማርያም ከወዴትና እንዴት አገኘሽው፣
እንደሚታረድ በግ አንገትሽን የሰጠሽው።

በሞሪያም ምድር የሄደውን፣
ምዕራፍና ጥቅስ ያላለውን፣
ዳግም ይስሐቅን አሳየሽን፤
ከሞት አፋፍ የነበረውን።

እኔማ፥ እኔማ አንብቤ ነበር፣
ያለያቸው ከክርስቶስ ፍቅር፣
ከቅዱሱ ቃል የቅዱሳኑን ክብር፤
በዘመኔ ዐየሁሽ የጽናትሽን ፍቅር።

በእጸ ሳቤቅ፥ ይስሐቅን ታድጎታልና፣
የማርያም ጽናት፥ ልዩና ድንቅ ነውና፣
ኅህቴ ማርያም፥ ጽናትሽ ይደርብኝና፤
ለታደገሽ አምላክ ይድረሰው ምስጋና።

(እንደ ሠልስቱ ደቂቅ፥ ማርያም ያህያ ኢብራሂምን በተስፋው ቃል ጎብኝቷት ከአንበሳ መንጋጋ ለታደጋት፤ ውዳሴና ክብር ምስጋና ለወልደ እግዚኣብሔር ለወልደ ማርያም ልጅ ለኢየሱስ ክርስቶስ ይሁን አሜን!!!)


[፲፯//፳፻፮ /]

No comments:

Post a Comment