Wednesday, June 4, 2014

“እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ።” /ዮሐ ፰፥፵፬/



የእግዚአብሔር ቃል ክብር ለሚገባው ክብር መስጠት እዳለብን ያስተምረና፤ /ሮሜ ፲፫፥፯/ ቢኾንም ግን አንዳንድ የፕሮቴስታንቶች ፓስተሮች (የተቃዋሚ አገልጋዮች) ይኼንን አምላካዊ ቃል ወደ ጎን በመተው የራሳቸውን ሥጋዊ ምኞቶቻቸው እንዳዛዘቸው እየፈጸሙና እያስፈጸሙ ነው። አባታችሁ ዲያብሎስ ከመፈሳ ይልቅ ምኞት ላሳወራቸው፤ ምኞታቸውን የተከተልጉትንና የኙትን ነገሮ ሁሉተ-ክርስቲኒቷ ላይ እጃቸውን በኃይል በመጫን ያሻቸውን ማድረ ጀምረዋል።

ቢኾንም ግን ከመጀመርያው ጀምሮ ፕሮቴስታንቶች፥ ከካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ሲያፈነግጡ፤ የነበራቸው እምነትና ሃይማኖት ከካቶሊካውያን የወረሱትን መሠረታዊ የካቶሊካውያንን ሥርዓት በመያዝ ነበር። ሉተር፥ ከካቶሊካውያን ያፈነገጠበት ዋናው ምክንያት፦ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን በወቅቱ ለአንዳንድ ነገሮች የገንዘብ ማሰባሰቢያ ስለፈለገች ስለነበር  ያዘጋጀችውን ትኬት “የመንግሥተ ሠማያት የመግቢያ ትኬት” ነው፤ ትኬቱን ግዙ እያለችና እያስባለች በነበረበት ወቅት በሉተር አማካኝነት ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ተቃውሞ  ገጠማት። ይኼም ተቃውሞ እየበረታና እያየለ ኼዶ፤ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን የራሷን ልጆች የነበሩትን እነ ሉተርን በማግለልና እነ ሉተርም የራሳቸውን ተቃውሞ በሀገሩ ላይ በተለያዩ  ከተሞች የሚገኙ የቀድሞ የካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን በሮች ላይ የተቃውሞውን ሐሳቦቹን ጽፎ ለጥፎ ነበር።

ይኹን እንጂ፥ የፕሮቴስታንቶች እምነትና ሃይማኖት እንደዚህ ከመቀየሩ በፊት፦ ለመድኃኒታችንና ለአምላካችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ያላቸውን ጥልቅ ፍቅር፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱሳንና ለሰማህታት ባዘዛቸው መንገድ፥ ለእናቱ ለቅድስት ድንግል ማርያም፣ ለቅዱሳኑ፣ በአጠቃላይ ከካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን የወረሱትን ሃይማኖታና ባህላዊ፣ ትውፊትና ቅዱሳት መጽሐፍቶቻቸውን እስከተወሰነ  ጊዜያት ድረስ ይጠቀሙበት ነበር።

ከዛ በኋላ የተነሱ ልዩ ልዩ የፕሮቴስታንቶች መሪዎችና ፓስተሮች የተዛባ አስተሳሰባቸውን በመርጨት፦ ለድንግል ማርያምና ለቅዱሳን፣ ለሰማህታትና ለፃድቃን፣ ለደናግልና ለአባቶች፤ እንዲሁም ደግሞ ለቅዱሳት መጽሐፍትና ለቅዱሳት ሥዕላት፤ ማንቋሸሽ፣ ማብጠልጠል፤ ጥቅም አልባ ማድረግ፤ ከምዕመናኑ፥ ልቦናና ኅሊና ፍቆ ማውጣት፤ የነደፉት ንድፈ-ሐሳባቸውን በመጫን ያላቸውን ጥላቻ ቀስ በቀስ ቀጠሉበት።
ዛሬ፥ ዛሬ አንዳንድ ፕሮቴስታንቶች፥ ለድንግል ማርያም፣ ለቅዱሳን፣ ለሰማህታት፤ አጠቃላይ ክርስቶስ የመረጣቸውን አንቃወምም በማለት በቃልና በጹሑፍ ብቻ የእናምናለን ነገር ሲያደርጉ ይታያሉ ይኼም መልካም ጅምር ነው። አንዳንድ ፕሮቴስታንቶች ደግሞ፥ ክርስቶስን ያገለገሉና የወደዱ እየመሰላቸው፦ እናቱን ቅድስት ድንግል ማርያምን፣ ቅዱሳኑን፣ ሰማህታቱን አጠቃላይ ክርስቶስ የመረጣቸውን፤ በቃል፣ በጹሑፍ፣ በድርጊትታቸው፤ ያላቻውን ጥላቸው  ይገልፃሉ፤ ይኼንን እያነበብንና እየተመከትን ነው።

የፕሮቴስታንቶች መሪዎች፦ ከ፲፱፺፭ (1995) እአአ ጀምሮ፤ ስለ ቅዱሳንም ኾነ ስለ ሰማህታት፥ ተጋድሎ፣ ክብር፣ ልዕልና፤ አናስተምርም ካሉ በኋላ፥ የሃይማኖትና የአምልኮ ኃይላቸው ወርዷል። በብዙ የአጥቢ ቤተ-ክርስቲያናቸው ዘንድ፤ የፕሮቴስታንቶች መሪዎቻቸውና ፓስተሮች ዘንድ እየተካኼደ ያለው የእምነት ኃይላቸው መቀዘቀዝ፣ ወደ ሥጋዊ ምኞታቸውና የኃጢያት ፍላጎቶቻቸው እየተሳቡ እየተሳቡ መጥተዋል። የመንፈስ ቅዱስ ማደርያ የነበረው ቅዱስ ሠውነትታቸው ላልተገባ ነገር አዋሉት። መንፈስ ቅዱስ ሲለያቸው፤ ርኩስ መንፈስ ቀርቦ እያደረባች ሲሄድ የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻን እስከ-መፍቀድና ራሳቸውም በዚህ የዋረደ ተግባር በመግባት፣ በገልጽ ማንነታቸውን በማሳወቅ፣ የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻን ሲፈጽሙና ሲያስፈጽሙ ይታያሉ።

‹‹ . . . የግብረ ሰዶማዊነት መነጋገርያ ጉዳይ ሊሆን የሚገባው ባይሆንም ይህን ጉዳይ መነጋገርያ አድርጌ በማንሳቴ እጅግ እያዘንኩ በአገልግሎቴ ተገድጄ ልመክር ግን እወዳለሁ፡፡›› እንዳሉት አባታች አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ፤ እኔም ይኼን ጹሑፍ ለመፃፍ ባልፈልግም፤ ግን የዲያብሎስ ባሮች የፈጸሙትና ያደረጉት ነገር ነውና ተግባራቸውን ይብለጥ እንድናውቃቸው ይረዳን ዘንድ ነው።

በዚህም ብቻ አላበቁም፤ የዲያብሎስ ባሮች ሲኾኑ፥ ለአባታቸውም ለአውሬው የተሰጠው፦ “ታላቅንም ነገርና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው” /ዮሐ ፲፫፥፭/ እንደተባለው፤ ከአባታቸውም ከአውሬው  የተማሩትን ትምህርት፤ እንኳን ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ይቅርና ስለ አምላካችንና ስለ መድኃኒታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የተሳደቡበት አፍ አለ። ይኼውም፦ ከፕሮቴስታንቶች እምነትና ሃይማኖት ተገንጣዯ የ‹‹ኢቪኒገግ ካልቸር›› የኾነችው ይህቺ ቤተ-ክርስቲያን በመሪዎቿና በፓስተሮቿ የመንፈስ ቅዱስ መለየት ያስከተለው መዘዝ ቀላል አይደለም። እነዚህ መሪዎቿና ፓስተሮቿ፥ በመጀመርያ ቅዱሳንን ያቃለሉ መስሏቸው ነበር፤ ቀስ ቀስ እያሉ የቅዱሳንን መንፈስን ሲያሳዝኑ ምንም ስላልመሰላቸው፤ የቤተ-ክርስቲያን ራስ የተባለውን ክርስቶስን ማሳዘን ጀመሩ። የቤተ-ክርስቲያንን ሥርዓት ናቁ፣ ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባራትን አቃለሉ፣ የፖለቲካ ሠዎች በመጠጋት በራስ መተማመንን ጀመሩ፣ መጨረሻቸው ክርስቶስን ተዳደቡ!።

ዛሬም ቢሆን በስዊድን አገር ባሉ የከፍተኛ የመንግሥት የሥልጣን ማዕከላትና የቅርንጫፍ ማዕከላት ላይ ያሉ ባለሥልጣናት ሁሉ በግብረ ሰዶማዊነት አቀንቃኞች አጀንዳ ተጽዕኖ ሥር ገብተዋል፡፡ ከስዊድን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጀምሮ አስከ ታች ድረስ፡፡ በፖለቲካው ካሉት ባለሥልጣናት ብቻ አይደለም፡፡ ከረጅም ዘመናት ጀምሮ በሕዝብ የግብር ገንዘብ ድጎማ ተዳዳሪ የሆነችው የስዊድን ቤተ ክርስቲያንም ብትሆን በነዚሁ በግብረ ሰዶማውያን ደጋፊዎች ፍላጎት ተጽዕኖ ሥር ወድቃች፡፡ ይሁን እንጂ በዚህችው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሊደነቅ የሚችል ቁጠር ያላቸው ምእመናንና እንዲሁም አገልጋዮች ከመሪዎቻቸው በየጊዜው ከሚወጡ ፖሊሲዎች ጋር የማይስማሙ ናቸው፡፡ 

እንዴት ክርስቶስን ተሳደቡ? በቃል? አዎን ከቃልም በላይ ቃል!!! ምን ዓይነት ቃል? ቅዱሳንን ባቃለሉት ቃል አይደለም፤ ከዛ በላይ እንጂ!!! እኮ ምን ዓይነት ነዋ ቃሉ? ሥዕላዊ ቃል!

የሊቀ ጳጳሱ ሀመር (“ጳጳሱ ሀመር  ግብረ-ሰዶማዊያን እና ግብረ-ሰዶማዊያት ጋብቻ እንዲፋጽሙ የፈቀደ፣ ራሱም ግብረ-ሰዶማዊ የነበረ ነው) እና በኡፕስላ የሰበካ ቄስ የሆነችው ግብረ-ሰዶማዊት (ሌዝቢያን) እህቱ ቪካር አና ካሪን በስዊድን ሉተራዊት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለውን ረጅም የመሠረተ እምነት ወግ በመለወጡ ረገድ ግንባር ቀደም ሰዎች ናቸው፡፡ (ግብረ-ሰዶማውያን የሚደርጉትን እንዲህ መሰሉን አሳፋሪ ድርጊት በዝርዝር ለማወቅ ከፈለጉ የታችኛውን የደረ-ገጽ  በማስፈንጠር ሄደው ይመልከቱ።[፩])

በ፲፱/፱/፲፱፺፰ (19/9/1998) ... (የዛሬ አስራ ስድስት ዓመት በፊት) ኡፕሳላ ተደርጎ በነበረው ‹‹ኢቪኒገግ ካልቸር›› በኡፕሳላ ካቴድራል የቅዳሴ አገልግሎት አዘጋጅተው በነበረ ጊዜ ኤክ ሆሞ ተብሎ የሚጠራውን ኤግዚቢሽን አሳይተው ነበር፡፡ ኤግዚቢሽኑ ኢየሱስን ሆሞሴክሹዋል ሁኔታዎች ውስጥ እንዳለ ሳይሆን ራሱ ግብረ ሰዶማዊ እንደሆነ አድርጎ ያሳየ ነበር፡፡ በቅዱሱ ኡፕሳላ ካቴድራል የቅዳሴ አገልግሎት ወቅት ኢየሱስን በዚህ መንገድ ማስተዋወቁ ባለፉት 30 ዓመታትና ከዚያ ወዲህ በስዊድን አገር የሆነውንና የተደረገውን ነገር ከፍተኛ መገለጫ ይመሰላል፡፡ (ሎ ስብሐት ለእግዚአብሔር!)


የፕሮቴስታንቶች መሪዎችና ፓስተሮች የጀመሩት፤ አህዛቦችም የነዚህም የስድብ አፍ በመስማት ዛሬም ቀጥለውበታል። እነዚህስ በማን ቀጠሉ? በንጉሡ እናት፣ በጌታ እናት፣ በክርስቶስ እናት፣ በኢየሱስ እናት፣ በአማኑኤል እናት፣ ኢየሱስ ብርሃን ነውና በብርሃን እናት፣ ክርስቶስ እግዚአብሔር ነውና በእግዚአብሔር እናት፣ በድንግል ማርያም ላይ የስድብ አፋቸውን ከፍተዋልና “ታላቅንም ነገርና ስድብን የሚናገሩበት አፍ ተሰጣቸው” /ዮሐ ፲፫፥፭/

ብራዘር ናትናኤል፥ አህዛቦች ያቀረቡትን ድምጽ በጥሞና ተከታትለው ምን ዓይነት ትውልድ ላይ እንደደረስ ይነግሩናል። አህዛቦች ያቀረቡትን ወምስል ተመልከቱና ታዘቧቸው።[፪]

 ጌታ ሆይ የሚሉትንና የሚያደርጉትን አያቁምና ይቅር በላቸው! ሎ ስብሐት ለእግዚአብሔር፤ ወድንግል ማርያም ክብር!

 ----------------------------------------
ዋቢ፦
[፩] የግብረ-ሰዶማዊያን አሳፋሪ ድርጊት በዝርዝር ለማወቅ ከፈለጉ፦ ኤማሶ ድረ-ገጽ
[፪] አህዛቦች ያቀረቡትን ድምጽ ወምስል ተመልከቱና ታዘቧቸው፦ ብራዘር ናትናኤል

No comments:

Post a Comment