ራሱን የሶርያና ኢራቅ እስላማዊ መንግሥት ብሎ የሚጠራው (ISIS) በዓለም ላይ ከሱኒ እስልምና ውጭ ያሉትን፤ እንዲኹም ደግሞ የሱኒ ሙስሊም ተከታይ ቢሆን እንኳን ዘግናኝና አስጸያፊውን ድርጊቱን የሚቃወሙትን የሱኒ ሙስሊም ተከታዮችን፤ አጠቃላይ ሃይማኖት ባለውም በሌለውም በማንኛውም የሠው ልጅ ፍጥረት ላይ ደም የሚጠጣበት ካራውን ካነሳ ቆይቷል።

ነገር ግን ልበ አምላክ እንዲህ ይላል፦ «ደምን ለማፍሰስ እግራቸው ፈጣን ነው፣ ጥፋትና ጕስቍልና በመንገዳቸው አለ፤ የሰላምን መንገድ አላወቁአትምና እግዚአብሔርን መፍራት በዓይናቸው ፊት የለም። ሕዝቤን እንደ እንጀራ የሚበሉ ኃጢአት የሚሠሩ ሁሉ በውኑ አያውቁምን? እግዚአብሔርንም አይጠሩትም።» (መዝ ፲፬፥፮-፯)
ጭንብል ለባሽ፦
ማንነቱን ደብቆ፤
ጭንብል አጥልቆ፤
ሠይፍ ጎመድ ታጥቆ፤
የሠው አንገት አንቆ።
ጭንብሉ ቢገለጥ እኒያ የተከበሩ፤
እነማን እንደኾነ ይለዩ ነበሩ።
ጭንብል ትመቻለች፤
ማንነትን ትሸፍናለች፤
"አላህ ወክበር" ታሰኛለች፤
የሠው አንገት ታስቀላለች።
----------------------------------------------------------------------------
መሪር ዕንባችንና ኃዘናችን ከባድ ነው!።
«ድንግል ሆይ፦ ከዓይኖችሽ የፈሰሰውን፥ በተወደደው ልጅሽ ፊት የወረደውን፣ መሪር የሆነ እንባሽን፣ ኃዘንሽን፤ አሳስቢ። ያን ጊዜ በነቢዩ በኤርምያስ፥ ድምፅ በራማ ተሰማ፥ ልቅሶና ብዙ ዋይታ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፥ መጽናናትም አልወደደችም፥ የሉምና የተባለው ተፈጸመ።» (ኤር ፴፩፥፲፭፤ ማቴ ፪፥፲፯-፲፰፤ /አባ ሕርያቆስ)
፲፩/፰/፳፻፯ ዓ/ም
-----------------------------------------------------------------------------
No comments:
Post a Comment