Saturday, April 18, 2015

የኋላን 'ረሱ



የአፄውን ውለታ የነፃነትን ጮራ፤
የመንጌ ሜዳልያ ለታሪክ ሲጣራ።

ጭቆናን ናፍቆ ባርነትን ጠራው፤
ደቡብ አፍሪቃ ማንዴላን ገፋው።
... ያን የግፍ ቀንበርን በላያቸው፤
የኋላን 'ረሱ የፊቱን ተመልክተው።

ታሪክን 'ረሱ በጭካኔ ተሞሉ፤
በእርግጥ ደም እያፈሰሱ ዋሉ፤
በደልን ተጠይፎ አንቅሮ ለጣሉ፤
ቀንም አለ' ከቀንም ቀን ላስተዋሉ።

እኮ ማን ይንገራቸው፤
ኧረ ማን ያስረዳቸው፤
ይብቃ በቃ! የሚላቸው፤
ታሪክን የሚያስታውሳቸው።

-----------------------------------------
[በሠው ልጅ ላይ እንዲህ ሲደርስ፦ ዕንባዬ እንደ ወንዝ ጅረት ውኃ ይወርዳል፣ እንዲኹም ጽኑ የኾነና ጥልቅ ኃዘንም ይሰማኛል፣ ሞታቸው ሞቴ፣ ሕመማቸውም ሕመሜ ነው! ልዑል እግዚአብሔር መላእኩን ልኮ ከነበልባሉ እሳት ቅዱስ ገብርኤል ይታደጋቸው።] (//፳፯ /)




No comments:

Post a Comment