Thursday, April 17, 2014

ታትመናል፥ በደሙ በክርስቶስ!


ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ፥ የዓለም መድኃኒት፣
ተወልዶ፥ ከድንግ ማርያም ቅድስት፣
ፍቅሩን ሲገልፅላት፥ እነሆ፦ እናቴ አላት፣
እኛም እንበላት፥ በክርስቶስ ፍቅር እናታችን ናት።

ክርስትና፥ ኦርቶዶክ ዘ ተዋሕዶ ነች፣
የቅዱሳኑን ስማቸው፥ ታከብራለች፣
ከክርስቶስ ስርዓት፥ ያልበረዘች፣
ሁሉን ነገሯን፥  ስለ እርሱ ያደረገች።

መጥምቁ ዮሐንስ፥ ክርስቶስን ሲሰብከው፣
የዓለም በግ፥ መድኅነ ኢየሱስ ነው ሲለው፣
አይሁድ ፈሪሳዊያን፥ ለካስ ሞኞች ናቸው፣
አፍጥነው ለመስቀል፥ እቅድ አዘጋጅተው።

በተና በ ተመካ ሉ፣
ሁከት እንዳይነሣ በበዓል አይሁን አሉ።

ዕረቡ፥ የከንቱ ከንቱ ምክር ተፀነሰ፣
ቀኑ ጸጥ ብላ ዋለች ዕት ሐሙስ፣
በዚች ሌሊት ተያዘ የዓለም ንጉስ፣
ዓለሙን በደሙ ሊያነፃ ክርስቶስ።


Tuesday, April 8, 2014

የሌሊቱ ተማሪ

ከፍሪሳዊ ወገን፥ የአይሁድ አልቃ የሆነው፤
ከሕገ ልቦና እስከ ሕገ ኦሪት የተማረው

ኒቆዲሞስ የሌሊቱ ተማሪ
ሕጉን ሥርዓቱን አክባሪ
በሙኩራብ ቃሉን መስካሪ
ቅዱሳት መፅሐፍትን መርማሪ

የሌሊቱ ተማሪ፥ ምጡቅ ዕውቅት ቢኖረው
ያላወቀውና ያለተረዳው፥ ጉድለት ነበረው
ስለዚህ፥ የሃይማኖቱን ጉድለቱን ሊሞላው
ለሕሊናው እረፍት መላ ፈለጎ  አገኘው

ያሰላሰለ በሌሊቱ ጨልማ 
ለነፍሱ ጥማት ቃሉን ሊስማ
ይኼድ ነበር ወደ ቃሉ አውድማ
ቀረበ፥ ኢየሱስም ድምፁን አሰማ

ሠው ዳግምኛ ከውኃና ከመንፈስ
ይወለድ አለ የእኛ አምላክ ኢየሱስ

የሠውን ሠውነት የተዋሕደው
ለዓለም ኹሉ መድኃኒት የነው
ለኒቆዲሞስ ምስጢረ ጥምቀት የነገረው
የድንግል ዘር ኢየሱስ ክርስቶስ ነው!

ሠው ዳግምኛ እንዲወለድከውኃና ከመንፈስ
ነገረ ማና ለሌሊቱ ተማሪ ለኒቆዲሞስ

(ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወድንግል ማርያም ክብር!) 

Friday, March 21, 2014

ተግሣጽን አትቀበሉምን? /ኤር 35፥13/



የክብሩ ሞገሥ፦ በሠማያት፣ በምድር፣ በጥልቁም ሥፍራ ያለ፤ እግዚአብሔር ለፈጠረን ፍጥረቱ (በተለይ ለእኛ በአምሳሉ ለፈጠረን ሠዎች) ስለሚወደንና ስለሚያፈቅረን ይገሥጸና! በነጐድጓድና መባርቅት፣ በከባድም ደመና ድምፅ፣ በብርቱ የንፋሳት ውሽንፍር ድምፅ፤ እግዚአብሔር፥ ህዝቡን ይገስጻል!።

ከነዚህ፥ ከተፈጥሮ ተግሣጽ ይልቅ ግን ተግሣጽን በአንደበተ-ቃል (ከሠዎች በሚወጣ ቃል) ሲገሥጽ በብሉይም በሐዲስም እናያለን። ለምሳሌ ያህል፥ በብሉይ፦ እግዚአብሔር፥ በሚወዳቸውና እንደ ሐሳቡና እንደ ትህዛዛቱ የሚሄዱትን አገልጋዮቹን በመላክ፣ በነቢዩ ኤርምያስ አንደበት አድሮ፦ ተግሣጽን አትቀበሉምን? /ኤር 35፥13/ እያለ ያናግር ነበር እናነባለን።

ይህ ተግሣጽ፥ በብሉይ ብቻ ሳይሆን በሐዲስ ኪዳንም ቢሆን የምናገኘው እውነታ ነው! ይህ የተግሣጽ እውነታ ደግሞ እራሱ ባለቤቱ፦ የፍቅር አምላክ፣ የተግሣጽ ጌታ፣ መድኅነ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስም በመዓክለ ምድር ከእናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በስጋ ተወለዶ፣ (ከበረት ውስጥ መወለድ ጀምሮ እስከ በዓለ ዕርገት፤ የተተረከውን ብናነብና ብናስተውል፣ በመንፈሳዊ ዕይታ ብናያቸው፣ ፍቅርን ብቻ ሳይሆን ተግሣጽ እናገኛለን! ) ሲያስተምርና ይህንን ዓለም በፍቅሩ አቅርቦ፣ በተግሣጹ ገሥጾ፤ ሕይወትን እንድናገኝ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሐዋርያት እንዲህ ሲል ጥያቄ አቀረበላቸው፦ "ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደ ሆነ ይሉታል?" ብሎ ሲጠይቅ፥ ሐዋርያትም በፈሪሳውያንና በሰዱቃውያን፣ እንዲሁም በአይሁድ ረበናት ካህናት የሚባለውንና የሚናገሩት ቀድመው ስለሰሙ፦ "አንዳንዱ መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም ኤልያስ፥ ሌሎችም ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው፤ ይላሉ አሉት።"

Thursday, March 20, 2014

በመልአከ መንክራት ግርማ ወንዱሙ ላይ ማጉረምረም ለምን?


አንዳንድ ወንድሞችና እኅቶች በመልአከ መንክራት ግርማ ወንዱሙ ትምህርት ቢመሰጡም፤ የተስጧቸው፥ ያህል ግን አጥጋቢ መንፈሳዊ ስንቅ ያለመያዛቸው ጉዳይ በተጠይቅና በፍልስፍና ጥያቄዎች ሲዳክሩ ማየት የተለመደ ነው።

እንዚህ ሠዎች የዲያቢሎስ መንፈስ ስልትና ውጊያ አለማገናዘባቸው፣ በመንፈሳዊ ትምህርታቸው ውስጥ የሚያስተላልፉት መንፈሳዊ ትምህርቶች ወደጐን በመተው፤ ከአምላክ የተቸራቸውን የጸጋ ሃብተ-ፈውስን በመንተራስና በመለጠጥ፣ አጉልተው፥ ለማጣመምና ሃብተ-ፈውስን "በአጋንት አለቃ አጋንትን የሚያወጣ ሠው ናቸው" በማሰኘት፣ ከመንፈሳዊ ዕይታ ይልቅ በኢ-መንፈሳዊ ዕይታዎች በማቀናጀት፣ ለማጣጣልና ከእግዚአብሔር ጸጋ-በረከት ህዝቡ እንዲርቁ በአሳቻ ምክር በመምከርና በክፉ ዕይታ እንዲታዩ በማሳየት፤ ትልቁን፥ የማጥመቅ አገልግሎት ማለትም፦ ከቤተ-ክርስቲያን ምስጢራት አንዱ "ምስጢረ ጥምቀት" የወጣ ነው፤ ብለው፥ ሲያወሩና ሲፅፉ እያየን ነው።

ቢሆንም ምስጢረ ጥምቀት ከቤተ-ክርስቲያን ምስጢራት አንዱና ዋነኛው ሲሆን፤ እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ ሆነና ስለ ምስጢረ ጥምቀትን (-አማናዊ የሆኑ ሠዎች፦ ወደ ክርስትና ሊመጡ ቢወዱ ንስሐንና ክርስትና እንዲነሱ ሲፈቅዱ የሚያደርጉትን የቀኖና ስርዓት ከምስለ ወድምፅ VCD 1-27 እንዲሁም መፅሐፋቸው፣ በተጨማሪም በአቢሲኒያ የሚተላለፈው በመንፈሳዊ ትምህርታቸው የተካተተ ነው!) በተለይም እንዴት እንደሚፈጸም በ፪፯ኛው በምስለ ወድምፅ በየረር ቅድስት ሥላሴ ቤተ-ክርስቲያን በአውደ ምዕረት ላይ በተካሄደው ንስሐ ክርስትና እንዴት በቤተ-ክርስቲያን ምስጢራት እንደሚከናወን፤ የተገለጸና የታመነ በቂ ምስክር ነው!

እግዚአብሔር፥ ጸጋ በረከታቸውን ያብዛልን፤ እርሳቸውንም ከሠዎች ከንቱ ውዳሴና ከንቱ ማጉረምረም በተጋድሎና በጽናት ያቆይልን፤ አሜን!

Sunday, March 2, 2014

ግብረ-ሰዶማውያንና የባህድ ስውር መነፅር፤ ለሃገራችን አይበጃትም!



ሚኒስትር / ዘነቡ ሆኑ የኢአህዴግ ባለስልጣናት እንዲሁም የፖለቲካ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ቢሆኑም በግብረ-ሰዶማውያን ላይ በአፅኖት ማስገንዘብ አለባቸው። ዳር-ዳር ማለት አያዋጣም!

እውነት ነው ኢትዮጵያ የሴቶች፣ የወጣቶች፣ የሕጻናትና የእናቶችን ነገር በተመለከተ፤ ቡዙ የብዙ፣ ሕጎቿን በማጥበቅ እና እጅግ አድርጋ አርቅቃ መስራት ይጠበቅባታል እንጂ ለአስጸያፊ ድርጊት የአሜሪካንንና የአውሮፓ ሃገራትን የሞት ምኞት ማስተናገድም ይሁን በር መክፈት የለባትም!

እርግጥ ነው፤ በመንግስ መገናኛ-ብዙሃን፦ ስለ ግብረ-ሰዶማውያን አስከፊነት፣ የነውር ድርጊት መሆኑን፣ የሥነ-ልቦና ቀውስ እንደሚያስከትል፣ በዚህ አስጸያፊ ድርጊት የገቡና የኖሩ ሰዎች ለተለያየ በሽታዎች የመያዛቸው ዕድል በጣም ከፍ-ያለ ሰፊ መሆኑን፣ በጭንቀትና በውጥረት መሰቃየታቸው እንደሚጨምር፣ እራስ-በራስ የማጥፋት ደረጃ በነዚህ ሰዎች ላይ ቁጥሩ እንደሚያይል፣ አጠቃላይ ግብረ-ሰዶማውያን አስከፊነትና መራራነት፤ በዜና አውታራቸው አለመዘገባቸው፤ ወዴት እየሄድን ነውም? ያሰኛል!

ወዳጆች ሆይ፦ በውጭ ዓለማት ላላቹ፤ በተለይ ደግሞ በአሜሪካና በአውሮፓ ሃገራትን ያላቹ! ዘመኑ ከባርነት ዘመን ወደ ዲሞክራሲያዊ ባርነት ዘመን (ከሃገራችን የወጣንበት የተለያየ ምክንያት ቢኖረንም) ላይ መድረሳች ይታወቃል። ይህን ስል፥ ማንም ቢሆን ሃገሩ ላይ መኖን የሚጠላ ሠው ያለ̕ አይመስለኝም።

Saturday, February 15, 2014

“ግብረ ሰዶማዊነት ሊለወጥ የሚችል ክስተት ነው!”


“ግብረ-ሰዶማዊያን” ማለት፥ ስድብ ሳይሆን የሚፈፅሙት ከመደበኛው የመሳሳብና አንድ የመሆንን በመግፋትና  በመናድ፤ የተመሳሳይ የፆታ ውሕደት ለመፍጠር የሚደረጉ ማንኛቸውም ግንኙነቶች  ልዩ መጠርያ ስማቸው “ግብረ-ሰዶማዊያን፤ የሰዶም ነፍሳት” ናቸው የሚባለውም ከዚህ ነባራዊ ሁናቴ ስለለወጡት ነው። ይህምግብረ-ሰዶማዊያንየሚለው መጠርያ ስማቸውም የተገኘው በሁለቱ ከተሞች ስም ነው። በእነዛ ከተማ የተደረገውን የተመሳሳይ የፆታ ፍትወት መሰረት በማድረግ፤ ከዚያን ጀምሮ  ስማቸው በእነዚ ከተማ ስም መጠራት ተጀመረ። (በነገራችን ላይ ሌዝቢያን አልያም ጌይ ካልተባልን የሚሉ ከሆነ ደግሞሌዝቢያንማለትም የከተማ ስም እንደሆነ እናያለን።)
ከክርስቶስ ልደት በፊት 5 ክፍለ ዘመን ሌስቦስ በምትባል የግሪክ ደሴት እንስት የግጥም ጸሐፊ የሆነች ሳፕፎ በርካታ ወጣት ልጃገረዶችን ታስተምር ስለ ነበር ሌዝቦስ የሚለው የከተማው መጠሪያ ለእንስት ግብረ ሰዶማዊነት መጠሪያነት ውሏል፡፡ የእንግሊዘኛው ልዝቢያን የሚለው ቃል የተወረሰው ከዚሁ የግሪክ ቃል ነው፡፡ሲል የግብረ-ሰዶማዊያኑ ድርጅት በድረ ገፃቸው ላይ አስፍረውታል። ቢሆንም ግን እኛ የስራቸውን የወረደ ቅለትና በመጀመሪያውኑ ላልተገባ ባህርያት እራሳቸውን ለሚያረክሱ ሰዎችግብረ-ሰዶማዊ ወይም ግብረ-ሰዶማዊትእንላለን ማለት ነው።
ግብረ-ሰዶማዊ ተፈጥሮ ነው ወይስ ተጋቦሽ? ለሚለው ጥያቄ፥ ግብረ-ስዶምማዊ ተፈጥሮ የለም። የአሜሪካው የስነ ልቦና ድርጅት (..) .. 1973 ባወጣው መግለጫ ግብረ-ሰዶማዊነት መደበኛ የሰው ተፈጥሮ ነው ብሎ ድንገት ማስታወቁ ትዝ ሊለን ይገባል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የስነ-ልቦናውና የአእምሮ ህክምና ጥናት ዘርፉ በግብረ-ሰዶማውያን ልዩ አጅንዳ የተጥለቀለቀ ይመስላል፡፡ ስለሆነም የቅርብ ጊዜ የግብረ-ሰዶማዊነት ላይ ጥናቶችም ( በተለይም ጸሃፊዎቹ ራሳቸው ግብረ-ሰዶማውያን ከሆኑ) በጣሙን ሚዛናዊነት የጎደላቸው፤ በዘርፉ በሚደረገው ጥናት ላይ የተመራማሪዎችን እውቀት ታማኝነት የማይገልጡ መሆናቸው ልናጤነው ይገባዋል፡፡
ይህም ማለት ሠዎች በመለማመድ ወይንም በተለያየ ምክንያት ወደዚህ ወደ ተገቢ ያልሆነ፣ የነውርና የኃጢአት ርኩሰት በሆነ፤ በተመሳሳይ ፆታ የሕይወት ውጣ-ውረድ ውስጥ ሲገቡ ሱስ ሆኖ ይፀናወታቸውና በዛው እራሳቸውን ለዚህ ግብረ ሰዶማዊነት እንደተፈጠሩ ያስባሉ። ይህ ሐሳባቸው፥ ደግሞ ለሕይወት ሥኬትቸው መቃናት የሚመኙላቸውን ሠዎችን፤ ግሳጼና ምክር አይሰሙም።