Sunday, August 24, 2014

“ጆሮዬም ሹክሹክታውን ሰማች” (ኢዮ ፬፥፲፪)


ይኼንን ርዕስ የተናገረ  “ጆሮዬም ሹክሹክታውን ሰማች” ያለ ፃድቁ ው። ፃድቁ ብ በክፉ በሽታና በጽኑ በተከዘ ጊዜ፥  ሦስቱም የኢዮብ ወዳጆች የደረሰበትን ክፉ ነገር ሁሉ ሰምተው ሊያዝኑለትና ሊያጽናኑት እንደመጡ ታላጽሐፍ ቅዱስ ይተርክልናልም፣ ተጽፎም እናነባለን

ቢኾንም ግን ሦስቱም የኢዮብ ወዳጆች በትንሹ ሐዘኑን ሊጋሩት ሞከሩ፣ ነገር ግን እስከ-መጨረሻው ሐዘኑን ሊጋሩት አልሉም። የኢዮብን፥ ሐዘኑን ሊጋሩት የመጡት ሰዎች እንኳን ከልባቸው ሊያዝኑለት ይቅና ሌላ የሐዘን ቁስል እንደጨመሩበት፣ ከማጽናናትም ይልቅ፥ እንዳይጽና በቁስሉ ቁስል ጨመሩበት፣  የኢዮብን፥ ብርታቱንና የጥንካሬውን እንዲሁም የፈሪሐ-እግዚአብሔሩን ውጤት ፍሬ-አልባ ለማስመሰል ያደረጉት ጥረት በፃድቁ ብ ዘንድ ዋጋ የለውም ነበር። ሦስቱ የኢዮብ ወዳጆቹ ከንቱ ውትወታ፤ በፃድቁ ኢዮብ ዕይታ ሲታዩ እንዲህ ይገልፆቸዋል፦ "ለእኔም በምሥጢር ቃል መጣልኝ፥ ጆሮዬም ሹክሹክታውን ሰማች" ይላቸዋል።

በምሥጢር ቃል ማምጣታቸውና ጆሮውም ሹክሹክታቸውን መስማቱ፤ ለመጣበት ፈተና በብቃት ማለፍና ለመንፈሳዊ ተጋድሎውና ለሕይወቱ መቅረዝ እንዳደረገው እንመለከታለ። ወደ ታች ወረድ ሲል ደግሞ “የዝምታ ድምጽ ሰማሁ” ይላል። (ኢዮ ፬፥፲፮)

በዝምታ ድምጽ ውስጥ ብዙ መልእክት አለ! ነቢየ ኤልያስም በዝምታ ድምጽ ውስጥ ነበር እግዚአብሔር የተገለጠለት። እነሆም፦ “በእግዚአብሔርም ፊት ትልቅና ብርቱ ነፋስ ተራሮቹን ሰነጠቀ፣ ዓለቶቹንም ሰባበረ፥ እግዚአብሔር ግን በነፋሱ ውስጥ አልነበረም። ከነፋሱም በኋላ የምድር መናወጥ ሆነ፥ እግዚአብሔር ግን በምድር መናወጥ ውስጥ አልነበረም። ከምድር መናወጥ በኋላም እሳት ሆነ፥ እግዚአብሔር ግን በእሳቱ ውስጥም አልነበረም። ከእሳቱም በኋላ፥ ትንሽ የዝምታ ድምፅ ሆነ። በዚ በዝምታ ድምፅ ነበር የእግዚአብሔር ድምጽ የተሰማው። (፩ኛ ነገ ፲፱፥፲፪)

Tuesday, August 19, 2014

ከፕሮፌሰራችን ዕይታ፦ የማልስማማበት



ፕሮፌሰራችን መስፍን ወልደ ማርያም ለሃገራችን፣ ለሕዝባችን፣ ለሀሕጉራችን፤ ትልቅ አስተዋጽዎ ካበረከቱ አንዱ ምርጥ ኢትዮጵያዊ ናቸው። ስለ ፕሮፍ አጠቃላይ ስለሰሩት መልካም ስራዎች፣ ስላበረከቱት ታላቅ አስተዋጽዎ በዚች አነስተኛ ጹሑፍ ለመዘከር አይደለም፤ ይልቅ የፕሮፋችን ዕይታ፣ ተመክሮ፣ ልምድ፣ ሕይወት፤ በዚህ ባሳለፍነው ተከታታይ አምስት ሳምንታት ከምንወዳትና ከምናከብራት፥ ከመዓዛ ብሩ ጋር እያደረጉት ያለውን ቃለ-መጠይቅ እያዳመጥናቸው ነው።

ሦስት ነገስታንን በሕይዎታች የተመለከቱ እኚህ ፕሮፋችን፥ በንግግራቸውም ረጋ ያሉና አንደበተ ርዕቱ ናቸው፣ እጅግ ማራኪ በኾነ አገላለጽ ታሪኮችን ያማክላሉ፣ የራቀውን አቅርበው እያጣጣሙ እያስቃኙን ነው። ቢኾንም ከፕሮፌሰራችን ዕይታዎቻና ቅኝቶች፦ የማልስማማበት ነገሮች ቢኖሩም፤ ከማልስማማበት አንዱ ደግሞ “የመንፈሳዊ ልዕልና” ብለው በዘረዘሩት ውስጥ “የቱ ጳጳስ፣ የቱ ቄስ ነው? ድኾች ተጠቅተዋል፣ ፍትሕ ጎደለ፣ ሠው ተበደለ ብሎ የጮ። የለም!። ካሉ በኋላ በእርሶ ጊዜ፦ አቡነ ባስልዮስ፥ ከንጉስ እጅ እርስዎና ከእርስዎ ጋር ሊገረፉ የነበሩትን ሠዎች ስለታደጉ ብቻ “ከአቡነ ባስልዮስ በኋላ ማንም!” የለም ማለትዎን ስለማልቀበለው ከአቡነ ባስልዮስ በኋላ፦ ድኾች ተጠቅተዋል፣ ፍትሕ ጎደለ፣ ሠው ተበደለ ብው የጮኹ አሉ!፤  ለዚህም  ከታች ያለውን አነስተኛ ጹሑፍ ላዘጋጅ ወደድሁኝ። እንደ መረጃና እንደ-ማስረጃ ይኾነን ዘንድ እንሆ ኹለቱን፦

Sunday, August 10, 2014

የሁላችንም ሐሳብ



         በቅንነት፥ ብንነጋገርና ብንሠራ፣ የሁላችንም ሐሳብ ለኢትዮጵያ ይጠቅማል እንጂ አይጐዳም!”  (ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ)      

Sunday, July 6, 2014

ነገረ ክርስቶስ፦ ክፍል አንድ፤ በቀሲስ ታምራት ውቤ



            በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
         እግዚአብሔር ባዘጋጀልን ጉባኤ መንፈስ ቅዱስ በገለጠልን መጠን ስለጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መማር እንጀምራለን።

ስለ ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርቱ የሚዳስሳቸዉ ነጥቦች

  ቀዳማዊ ወድኅራዊ ሕያዉ ዘላለማዊ አምላክ ስለመሆኑ፤
 
  ቅድመ ዓለም ከእግዚአብሔር አብ ያለ እናት ድኅረ ዓለም ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ያለ አባት ስለመወለዱ (ስለ ሁለቱ ልደታት
 
ስለ ድንቅ ልደቱና የልጅነት ህይወቱ፣ ስለ ጥምቀቱ፣ ስለ ትምህርቱና ስለ ተዓምራቱ፣ ስለ ህማሙ፣ ስቅለቱ፣ ሞቱ፣ ትንሣኤዉና ዕርገቱ፣ ዳግመኛም ለፍርድ ስለ መምጣቱወዘተይሆናል
 
        በቅድሚያ አንድን አካል "አምላክ" ነው ለማለት የአምላክነት ባህርያት ምን እንደሆኑ መገንዘብ ያስፈልጋል የሁሉ ነገር የማንነቱ መገለጫ ባህርዩ ነውና ሰለዚህ የአምላክነት ባህርያት የሚባሉትና የየትኛዉንም ሃይማኖት ተከታይ ወይም ፍልስፍና አራማጅ የሚያስማሙት፡-

Tuesday, June 24, 2014

ሆ ማርያም ጽናትሽ፦



ተወልደሽ ከአባት ከእናትሽ፤
ከኹለት ቤተ እምነት ኾንሽ።

ከፍትሕ ፊት ቢያቆሙኝ፣
የክስ ፋይል ቢከፍቱብኝ፣
አንገቴን አቀርቅሬ አዳመጥኹኝ፤
ዳኛው ተናገሩ በቃ ትገደል አሉኝ።

በሕይወት ለመኖር፥ እድል ቢሰጠኝ፣
ለውሳኔ፥ ሦስት ቀን ብቻ ቢታወጅብኝ፣
በሃይማኖቴ አልግደረደርም ክርስቲያን ነኝ፤
አዋጁን ሰምቼ በአርምሞ ልቤን አጸናሁኝ።

ልቤ አይደነግጥም እጸናለሁ በአማላጁ፤
የማይተወኝ ገብርኤል ይቆማል ከደጁ።

ከትንታግ እሳት፥ የሚታደገኝ፣
ገብርኤል ነው ስሙ እወቁልኝ፣
የኢየሱስ ልጁ ነኝ የማይተወኝ፤
አለ የድንግል ልጅ ምንም አይነካኝ።

ምን እኾናለው ብኖርም ብሞትም፤
እኔ የኢየሱስ ነኝ አልደነገጥኹኝም።

ሆ ማርያም፦ ጽናትሽ ሃያልና ድንቅ ነው፣
የሃይማኖት ጽናትሽን እንዴት ተማርሽው፣
ሆ ማርያም ከወዴትና እንዴት አገኘሽው፣
እንደሚታረድ በግ አንገትሽን የሰጠሽው።

በሞሪያም ምድር የሄደውን፣
ምዕራፍና ጥቅስ ያላለውን፣
ዳግም ይስሐቅን አሳየሽን፤
ከሞት አፋፍ የነበረውን።

እኔማ፥ እኔማ አንብቤ ነበር፣
ያለያቸው ከክርስቶስ ፍቅር፣
ከቅዱሱ ቃል የቅዱሳኑን ክብር፤
በዘመኔ ዐየሁሽ የጽናትሽን ፍቅር።

በእጸ ሳቤቅ፥ ይስሐቅን ታድጎታልና፣
የማርያም ጽናት፥ ልዩና ድንቅ ነውና፣
ኅህቴ ማርያም፥ ጽናትሽ ይደርብኝና፤
ለታደገሽ አምላክ ይድረሰው ምስጋና።

(እንደ ሠልስቱ ደቂቅ፥ ማርያም ያህያ ኢብራሂምን በተስፋው ቃል ጎብኝቷት ከአንበሳ መንጋጋ ለታደጋት፤ ውዳሴና ክብር ምስጋና ለወልደ እግዚኣብሔር ለወልደ ማርያም ልጅ ለኢየሱስ ክርስቶስ ይሁን አሜን!!!)


[፲፯//፳፻፮ /]

Saturday, June 21, 2014

"መንፈሳዊ አገልግሎት" በዲ/ን ዳንኤል ክብረት

"የእግዚአብሔርን ሥራ በቸልታ የሚያደግ ርጉም ይሁን" (ኤር ፵፰፥፲)

"እንዲሁ እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ፤ የማንጠቅም ባሪያዎች ነን፥ ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል በሉ።" (ሉቃ ፲፯፥፲)

አንድን አገልግሎት "መንፈሳዊ አገልግሎት" ነው የሚያሰኙት፤ እነዚህ አራት ነገሮች ሲኖሩት ነው

፩፤ አገልግሎቱ፦ ሠማያዊ ዋጋ፥ ታስቦ የሚደረግ ከኾነ ነው። የሚመራውም በመንፈስ፣ የሚሠራውም በመንፈስ ከኾነ ነው "መንፈሳዊ አገልግሎት" የሚባለው። ምድራዊ ዋጋ ታስቦ የሚደረግ ከኾነ "መንፈሳዊ አገልግሎት" አይደለም፤ ይኼ ሥራ ነው።

፪፤ አገልግሎቱ፦ በመንፈስ የሚደረግ ከኾነ ነው። የሚመራውም በሥጋ፣ የሚሠራውም በሥጋ ከኾነ፤ "መንፈሳዊ አገልግሎት" ማለት አይቻልም።

፫፤ አገልግሎቱ፦ በትህትና ከኾነ ነው። ከትዕቢት፣ ከሥልጣን፣ ከክብር፤ እነዚህን ከመሳሰሉት ነገሮች የራቀ ከኾነና በትህትናና ራስን ዝቅ በማድረግ የሚደረግ ከኾነ ነው፤ ይኼ ነው "መንፈሳዊ አገልግሎት" ማለት የሚቻለው። "መንፈሳዊ አገልግሎት" ምድራዊ ክብርን የሚያመጣ፣ ምድራዊ ሥልጣንን የሚያመጣና በምድር ሠዎችን በጣም ከፍ የሚያደርጋቸው ከኾነ "መንፈሳዊ አገልግሎት" መኾን አይችልም። "መንፈሳዊ አገልግሎት" ኾኖ ቢጀመር እንኳን "መንፈሳዊ አገልግሎት" ኾኖ አያልቅም።

፬፤ አገልግሎቱ፦ መሥዋዕትነት ካለበት ነው፤ "መንፈሳዊ አገልግሎት" አገልግሎት የሚባለው። የሚያገለግለው ሠው እራሱ መሥዋዕት እየኾነ የሚያገለግለው ከኾነ ነው። ሌላውን እየሰዋ የሚያገለግለው ከኾነ፣ ወይም ደግሞ ምንም ዐይነት መሥዋዕትነት የማይከፈልበት ከኾነ አገልግሎቱ፦ "መንፈሳዊ አገልግሎት" ነው ማለት አይቻልም። አንድን አገልግሎት፦ "መንፈሳዊ አገልግሎት" ነው የሚያሰኙት እነዚህ አራት ነገሮች ናቸው።

         "መንፈሳዊ አገልግሎት" በሚል (በሰባኪ ወንጌል ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ) በዲ/ ዳንኤል ክብረት የተሰጠ መንፈሳዊ ትምህርተ ወንጌል ሰምተውና  አዳምጠው፤ ስጋዎትንና ነፍሶትን ይመግቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም ተጋብዘዋል።

         እግዚአብሔር አምላክ፦ ለወንድማችን ቃለ ሕይወትን ያሰማልን፤ መንግሥተ ሠማያት ያውርስልን። አሜን!

Wednesday, June 18, 2014

"ከእግዚአብሔር እንደ ሆንን ዓለምም በሞላው በክፉው እንደ ተያዘ እናውቃለን።" /፩ኛ ዮሐ ፭፥፲፱/



(በ፰//፳፻፮ / [15/6/2014 EC] በጣሊያን ሮማ ከተማ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ፥ የደብረ ከነዓን ቅድስት ሥላሴ / ቅጽር ግቢ ካነሳዋቸው ፎቶዎች።)

ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ በአንደኛው መልእክት በምዕራፍ አንድ ቁጥር አስራ ዘጠኝ ላይ እንዲህ ይላል፦ "ከእግዚአብሔር እንደ ሆንን ዓለምም በሞላው በክፉው እንደ ተያዘ እናውቃለን።" /፩ኛ ዮሐ ፭፥፲፱/

አምላካችንና መድኃኒታችን፣ መድኅነ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ፣ በዚህ ዓለም ላይ በነበረበት በሥጋ ወራት፤ "የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ" /፩ኛ ዮሐ ፫፥፱/ ይህ የተገለጠው፥ አምላክና መድኃኒት ነው። አልፋና ኦሜጋ ነው፣ አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው ነው፣ መጀመሪያውና መጨረሻው እርሱ ነው፤ እኔ ነኝም ይላል። /ራእ ፳፪፥፳፫/ እርሱ ከዳዊት ዘር የተወለደው፦ የእግዚአብሔር ልጅ፣ የድንግል ማርያም ልጅ፣ አማኑኤል የተባለው፤ እርሱ መድኃኒትና ፈዋሽ፤ ለዓለም የተሰዋ በግ ነው።

ይኼ ሥም፥ አጋንት የሚንቀጠቀጡበት፣ ኃያላን በረዓድ የሚርበተበቱበት፣ ነገሥታት ጉልበታቸውን የሚያንበረከኩለት፣ ጥበበኞች መዕባ የሚያቀርቡለት፣ ምላስ ሁሉ የሚያመሰግነው፣ ድንቅ መካር፣ ኃያል አምላክ፣ የዘለዓለም አባት፣ የሠላም አለቃ፣ አማኑኤል፣ ኤልሻዳይ፣ አዶናይ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

"ስለዚህ፥ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ" /፩ኛ ዮሐ ፫፥፱/ ለሠው ልጅ ጠላት የኾነው ርኩስ መንፈስ ቀርቦ፦ "ዲያብሎስም ረጅም ወደ ሆነ ተራራ አውጥቶ የዓለምን መንግሥታት ሁሉ በቅጽበት አሳየው።" ብሎ፤ ዲያብሎስ፥ ራሱን የስልጣን ባለቤት እንደኾነ በመቁጠር፤ ከአምላካችንና ከጌታችን ጋር ስለ ዓለማት ነገሥታት ክብርና ዝና፣ ላልተገባ የክፉ ስግደት እንዲሰግድለት በጠየቀው ጊዜ አምላካችን ክርስቶስ "ለጌታ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአል" /ሉቃ ፬፥፩-፲፫/ ብሎት፤ የዲብሎስን የተንኮል ሥራ እንዳፈረሰ፣ ርኩስ መንፈስ እንደገሰጸና ለመንፈሳዊ አባቶች ስልጣንን፣ ለእኛ ለምዕመናን አማኝ ደግሞ እንዴት መጽናት እንዳለብን የነፍሳችን መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ በቃል፣ በምግባር፤ አስተምሮናል።