Wednesday, December 25, 2013

"አቡነ ተክለሃይማኖት ሐዋርያ" በዲ/ን ዳንኤል ክብረት



በዲ/ ዳንኤል ክብረት ስለ አባታችን ጻድቅ "አቡነ ተክለሃይማኖት ሐዋርያ" በሚል የተሰጠ መንፈሳዊ ትምህርተ ወንጌል፥ አይተው፣ ሰምተውና አዳምጠው፤ ስጋዎትንና ነፍሶትን ይመግቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም ተጋብዘዋል።

በዚህ ትምህርት ውስጥ፦

* በዮዲት ጉዲት፥ የጥፋት ጊዜ፣ ለኢትዮጵያ ቤተ-ክርስቲያን የሚመጡ የነበሩ የግብፅ ጳጳሳት እንደቀሩና ክርስቲያን አማኞች የጠፉበት ጊዜ፤ እንደነበረ ይገልፅልናል።

* ዮዲት ጉዲት፥ አርባ ዓመታት ያህል፣ ታላቅ መከራና ከባድ ጥፋት ካደረሰች በኋላ፤ ባደረሰችው የቤተ-ክርስቲያን ብዝበዛ፣ ካህናትና ምዕመናን በጠፉበት ጊዜ፤ ከአንድ ትውልድ ጥፋት በኋላ፤ ፀሐየ ጽድቅ አቡነ ተክለሃይማኖት የተወለዱበትና የተነሱበት ጊዜ፤ ለኢትዮጵያ ቤተ-ክርስቲያን በጣም አስፈላጊ እንደሆነ፤ ወንድማችን ዳንኤል ክብረት፥ አልምቶና አብራርቶ ያስተምራል።

* በዚያን ግዜ፥ በመረጃ ያለመኖርና መለዋወጥ በማይቻልበት ወቅት፣ የግብፅ እስላሞች "ጳጳስ ነን" ብለው የመጡበት ጊዜ እንደነበረም ያትታል።

* በወቅቱ የነበረውን የኢትዮጵያን ታሪክ፣ ከዛም በኋላ የነበረውን የሃገሪቱን ታሪክና ሁናቴን፣ የቤተ-ክርስቲያን ታሪክ ይተርክልናል።

* አጠቃላይ፥ ስለ ፀሐየ ጽድቅ አቡነ ተክለሃይማኖት ተጋድሎና ሐዋርያዊ አገልግሎታቸውን በስፋት ያስቃኘናል።





ለወንድማችን / ዳንኤል ክብረት፥ እግዚአብሔር አምላክ የአገልግሎቱን ጊዜውን ይባርክለት፤ አሜን!

No comments:

Post a Comment