Friday, January 18, 2013

ስሞት እጸልይላችኋለሁ


                                                                           በዲ/ ሄኖክ ኃይሌ
  ከመውጣቴም በኋላ እነዚህን ነገሮች እንድታስቡ በየጊዜው ትችሉ ዘንድ እተጋለሁ!” /2 ጴጥ.113-15/

       ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም በመጣበት ወቅት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን መሥርቶአል፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያቱንእኔን ማን ትሉኛላችሁ?” ብሎ በጠየቃቸው ጊዜአንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህብሎ ቅዱስ ጴጥሮስ መልሶ ነበር፡፡ ከዚህም በኋላአንተ ዓለት ነህ በዚህችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራታለሁ፤ የሲኦልም ደጆች ሊያናውጿት አይችሉም፡፡በማለት ቤተ ክርስቲያንን በሐዋርያት መሠረት ላይ መሠረተ። /ማቴ.16÷16-18/

Wednesday, January 16, 2013

እጹብ ድንቅና ምርጥ የሆኑ አስራ ስድስቱ ብሒለ አበው!

 1 ‹ራስህን በሐሰት አትውቀስ ራስን መክሰስ ትህትና አይደለም ታላቁ ትህትና ሰዎች ሲወቅሱህ መታገስ ነው።›› /ቅዱስ ስራፕዮን/
2 ‹‹የማታምንበትን ነገር ለሰው ስትል አትስራው ከሰራኸው እንደምትጠፋበት እወቅ።›› /መጽሐፈ ምክር/
3 ‹‹አንደበቱን ከቧልት ከሐሜት ያየውንም ሚስጥር ከመናገር የሚከለከል ሰው ልቦናውን ከኀልዮ ኃጥያት ያርቀዋል።›› /አረጋዊ መንፈሳዊ/
4 ‹‹ ጸጋ ቢሰጥህ በተሰጠህ ጸጋ አመስግን ያልተሰጠህን እሻለሁ በማለት የተሰጠህን እንዳታጣ።›› /ማር ይስሐቅ/
5 ‹‹ራሱን የሚንቅ የሚያቃልል ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ እውቀትን ያገኛል አዋቂ ነኝ የሚል ሰው ከፈጣሪው ‹ጥበብ ይለየዋል።›› /አረጋዊ መንፈሳዊ/

Monday, January 14, 2013

ተግሳፅ፣ ምክርና ትዕዛዝ፦ (ክፍል ሦስት)

                ፈላስፋው ህርቃን፦ ያዘዘው ትዕዛዝ የመከረው ምክር ይህ ነው

ልጄ ሆይ፦ ከዐዋቂዎችና ከብልሆች ሰዎች አትራቅ፥ ምንም እንኳን ጥበባቸውን ባትየዝ ቁጥርህ ከእነርሱ ጋር ይሆናልና ሲልኩህም ሁለተኛ ጓደኛን ጨምሩልኝ በማለት አታስቸግራቸው።

ልጄ ሆይ፦ ባልንጀራህን ስትልከው እሺ በእጄ ያለህ እንደሆነ ባልንጀራው እንጂ ጌታው አለመሆንህን አስብ። ዳግመኛም የላከኸውን አቃንቶ ሲመለስ ይህን አጎደልኸ በማለት አታበሳጨው። እሱ ገንዘቡ ያልሆነውን አይበላምና ያንተም ያልሆንውን ለማምጣት አያዝንልህምና።

ልጄ ሆይ፦ ከባዕድ ሰው ማዕድ መቅረብን አትውደድ (ቀላዋጭ አትሁን) እንዲህ ያለው ነገር ያዋርድሃል ያስንቅሃልና።

“የሌላ ማዕድ ደጅ የሚጠና ተስፋ የሚያደርግ ሰው አነዋወሩ እንደ ሞተ ሰው ነው እንጂ እንደ ደኅነኛ አይደለም የሰው እህል የሚወድ ሰው ከሐሜት አይድንም የተመከረ አዋቂ ሰው ግን ከሁሉ ይጠበቃል።” /ሲራ 40፥29/

Saturday, January 12, 2013

"መንፈስ፣ አእምሮና ልሳን"


ይህቺን አነስተኛ ጽሁፍ እንድጽፍ ያነሳሳኝ ወንድም ታረቀኝ “የመንፈስ መውረድና ልሳን” በሚለ በመጣጥፉ በመነሳት ሲሆን ከአንዳንድ ወንድሞቼና እኅቶቼ ስለ አሉታዊ ግምት በመውሰድ ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃ እየተረሙት ስለ እግዚአብሔር በፈ መጠን እነአልኩኝ።

ከአንዳንድ ወንድሞቼና እኅቶቼ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ቃል ስንንነጋገር ስለ ልሳን በ1ኛ ቆሮንቶስ በምዕራፍ 14፥2 ላይ ያልውን ሐረፈተ ነገር  በመጥቀስ እንዲህ ብለውኝ ነበር  "በልሳን የሚናገርስ ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አይናገርም" እና እኛ በልሳን ብንናገር ለእግዚአብሔር፣ ከእግዚአብሔር ጋር እንጂ ለሰዎች ወይንም ከሰዎች ጋር አይደለምነበር ያሉኝ።  እኔም እነሱ ላነሱልኝ  መጽሐፍ ቅዱስ በ1ኛ ቆሮንቶስ በምዕራፍ 14፥2 ላይ ያለውን ቃል ስለጠቀሱልኝ ነገሩን በአርሞ ለትንሽ ደቂቃዎች አሰላሰልኩና ማለፍ ሳላልፈለኩኝ እንዲህ ነበር ያልኳቸው።

Tuesday, January 8, 2013

ተግሳፅ፣ ምክርና ትዕዛዝ፦ (ክፍል ሁለት)

               ፈላስፋው ህርቃን፦ ያዘዘው ትዕዛዝ የመከረው ምክር ይህ ነው
ልጄ ሆይ፦ እግዚአብሔር ባደለህና በወሰነልህ ሀብት አመስግነህ ኑር። እርሱ  እግዚአብሔር ከሰጠህ ሌላ ምን ምን የሚጨምሩልህ የለምና ተስፋህንና እምነትህን በአገልጋዮችህ ላይ አታድርግ።

ልጄ ሆይ፦ የማትወደውንና የማይወድህን ሰው ከማእድህ አታግባ። በማናኛቸውም ነገር ከማይወድህ ሰው ጋር አባሪ አትሁን። ከሁሉ ጋር መቀመጥን አትውደድ።

Monday, January 7, 2013

ተግሳፅ፣ ምክርና ትዕዛዝ፦ (ክፍል አንድ)

               ፈላስፋው ህርቃን፦ ያዘዘው ትዕዛዝ የመከረው ምክር ይህ ነው

ልጄ ሆይ፦ የምነግርህን ቃሌን ስማ ልዑል ክቡር የሚሆን እግዚአብሔርን እንድታስታውሰው ምክሬን ተቀበል።

ልጄ ሆይ፦  ነገርን (ምስጢርን) የሰማህ እንደሆነ በልብህ ውስጥ ሰውረው ለሌላ አትግለጠው። ተመልሶ የእሳት ፍም ሆኖ አንደበትህንና ኣካላትህን ሁሉ እንዳያቃጥልህ። በዚያው ላይ እገሌ ምስጢር አይቋጥርም አሰኝቶ ስድብንና ውርደትን ያስከትልብሃል።

ልጄ ሆይ፦  ዓይንህ ያየውን ሁሉ አትሳብ (አታንሣ)፣ ታስሮ ያገኘኸውን አትፍታ፣ ተፈትቶ ያገኘኸውን አትሰር፣ ተከድኖ ያገኘኸውን አትክፈት፤ ተከፍቶ የቆየህን አትክደን።

Saturday, January 5, 2013

ከንብ፣ ከውሻ፣ ከእባብ ምን እንማር?

            እውነት ነው፥ አብዛኞቻችን እነዚህ ስሞች ስንሰማ ከፊታች የሚታየንና በህሊናችን የምናስባቸው፣ የምናሰላስለው ጎጂ መሆናቸው ነው። ለመሆኑ በበጎ ጎን እይታ ስንቶቻችን ተመልክተናቸው። ማጋነን ባይሆንብኝም በተቃራኒ እይታ ነው አብዛኞቻችን የምንመለከታቸው። ለዚህም ነው ከንብ፣ ከውሻ፣ ከእባብ ምን እንማር?” ብዬ እርስ የሰጠሁት። ንብን የምናውቃት በተናዳፊነቷ ነው፣ ውሻን ደግሞ በተናካሽና በአስደንጋጭነቱ ነው፤ እንዲሁም ደግሞ እባብን መርዘኛና ገዳይ እንደሆነ ነው። እንግዲያውስ ከተለያዩ ጸሐፊያንና መምህራን ያነበብኳቸውንና የሰማሁትን እነሆ ለእናንተ ለወዳጆቼ አብረን በጎ በጎ ጎናቸውን እናነበው ዘንድ አቀረበኩ። መልካም ምንባብ!