Wednesday, January 16, 2013

እጹብ ድንቅና ምርጥ የሆኑ አስራ ስድስቱ ብሒለ አበው!

 1 ‹ራስህን በሐሰት አትውቀስ ራስን መክሰስ ትህትና አይደለም ታላቁ ትህትና ሰዎች ሲወቅሱህ መታገስ ነው።›› /ቅዱስ ስራፕዮን/
2 ‹‹የማታምንበትን ነገር ለሰው ስትል አትስራው ከሰራኸው እንደምትጠፋበት እወቅ።›› /መጽሐፈ ምክር/
3 ‹‹አንደበቱን ከቧልት ከሐሜት ያየውንም ሚስጥር ከመናገር የሚከለከል ሰው ልቦናውን ከኀልዮ ኃጥያት ያርቀዋል።›› /አረጋዊ መንፈሳዊ/
4 ‹‹ ጸጋ ቢሰጥህ በተሰጠህ ጸጋ አመስግን ያልተሰጠህን እሻለሁ በማለት የተሰጠህን እንዳታጣ።›› /ማር ይስሐቅ/
5 ‹‹ራሱን የሚንቅ የሚያቃልል ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ እውቀትን ያገኛል አዋቂ ነኝ የሚል ሰው ከፈጣሪው ‹ጥበብ ይለየዋል።›› /አረጋዊ መንፈሳዊ/

6  ‹‹እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለ ጻድቅ አድርገው  ከሚቆጥሩኝ ሰዎች አድነኝ።›› /አባ እንጦንስ/
7 ‹‹ፍጡራንን መርምሮ ማወቅ ካልተቻልን ሁሉን የፈጠረ እርሱን መርምሮ ማወቅ እንደምን ይቻልናል።›› /ቅዱስ አትናቴዎስ/ 
8 ‹‹ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ሁሉ የክርስቶስንም ፀጋና ክብር ሳይፈተኑ ማግኘት አይቻልም የዚህ ዓለም ፈተናና እሳት ቶሎ ያልፋል ይጠፋል ኃጢያተኞች የሚገቡበት የገሀነም እሳት ግን ለዘላለም እንደ ነደደ ይኖራል።›› /ቅዱስ ሚናስ/

9  ‹‹በማንም ላይ ክፈትን አትስሩ አትፍርዱ ይህንን ከጠበቃችሁ ርስቱን ትወርሳላችሁና።›› /ታላቁ አባ መቃርስ/
10 ‹‹ብዙ ጊዜ ብዙ እናገራለሁ በመናገሬም አዝናልሁ በዝምታዬ ግን ያዘንኩበት ጊዜ የለም።›› /ቅዱስ አርሳንዮስ/
11 ‹‹ቤተክርስትያን መጠጊያችን ነች ቤተክርስትያን የኖኅ መርክብ ነች በውስጧ እንጠለላልን ከውጭዋ ግን ማዕበልና ቀላያት ተከፍተዋል።›› /ቅዱስ እንድርያስ/
12 ‹‹ልባችንን ጠፊና በስባሽ ከኾነው ከምድራዊው ምኞት አርቀን ከበደል በንስሐ ነጹሕ ካደረግነው በጸጋ መንፈስቅዱስ የተሞላን እንሆናለን።›› /አባ አብርሃም መፍቀሬ ነዳያን/
13 ‹‹ስጋዊ ፍላጎቶችን ማሸነፍ ለአክሊለ ህይወት የሚያበቃ ሰማዕትነት ነው።›› /ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ/
14 ‹‹የቤተክርስቲያን ህይወት በመስቀል ላይ ስለሆነ ፈተና ይበዛበታል ስለዚህ ከግል ህይወታችሁ ይልቅ የቤተክርስቲያናችሁን አቋም አጠንክሩ።›› /ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ/
15 ‹‹ከመኝታህ በፊት የምታደርገውን ፀሎት ትተህ እንድትተኛ መንፈስህ ሲገፋፋህ እሺ ብለህ አትቀበለው፡፡ እንዲያውም መዝሙረ ዳዊትን ጨምርና ሌሊቱን በሙሉ ስትፀልይ እደር።›› /ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ/
16 ‹‹ኃጥያታችንን እኛ እያሰብን የምንፀፀት ከሆነ እግዚአብሔር ይረሳልናል  ኃጥያታችንን እኛ እረስትን የምንፅናና ከሆነ እግዚአብሔር ያስብብናል።››  /ቅዱስ እንጦስ/

No comments:

Post a Comment