Saturday, November 16, 2013

ሰበር ዜና፦ የመጨረሻው መጀመርያ



ሳውዲ ከሪስ አብደላ ሚባል አካባቢ ዝናብ በአሁን ሰዓ መብራት ፍቶ ከተማው ጎረፍ ላይ ነው በአረባ አመት ውስጥ ታይቶ ማይታወቅ ይለኛ ዝናብና ጎርፍ አስተናግዳለች ሳውዲ ሆይ የማይነኩትን የቅድስት አገር ኢትዮጵያ ልጆች ነክተሻልና ፍርድሽን ከላይ ተቀበይ! (ፍሪደም ፎር ኢትዮጵያ)


የመጨረሻው መጀመርያ፦

የመጨረሻው መጀመርያ፥ ማለቴ፦ ለእነርሱ የመጨረሻ፣ ለፈጣሪያችን ደግሞ ሥራውን የሚጀምርበት መጀመርያ፤ ማለቴ ነው!!!

እግዚአብሔር፥ በነቢዩ ኢሳያስ አንደበት አድሮ፤ ሕዝብን ለሚጨፈልቁ፣ ክቡር የሆነውን የሰውን ደም እንደ ውሃ ጅረት በእጃቸው ላጨማለቁ፣ እንደዚህ ይላል፦ "በዚያም ቀን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ወደ ልቅሶና ወደ ዋይታ ራስን ወደ መንጨትና ማቅንም ወደ መልበስ ጠራ።" እውነት ነው! በየትኛውም ዘመን ይሁን - በየትኛው ጊዜ፤ አምላክ ብድራታቸውን ጠርቶ ይመልስባቸዋል።

በመቀጥል፥ ለተበደሉ፣ ላዘኑ፣ ለተጨነቁ፤ ሕዝብ ደግሞ፦ "እኔም በኢየሩሳሌም ሐሤት አደርጋለሁ በሕዝቤም ደስ ይለኛል ከዚያም ወዲያ የልቅሶ ድምፅና የዋይታ ድምፅ አይሰማባትም።" /ኢሳ 2212 እና 6519/ ብሎ ተናግሯል!

ኧረ ለመሆኑ፥ ደስታና ሐሤት የሚያደርግባቸው፣ ሕዝቦች የተባሉት እነማን ይሆኑ? ሕዝብን እየጨፈልቁ፣ ክቡር የሆነውን የሰውን ደም እንደ ውሃ ጅረት በእጃቸው እያጨማለቁ፣ እያረዱና እየገደሉ፤ "ይቅርታ" ጠይቁኝ በሚሉት ይሆን ሐሤት የሚያደርገው? እንደ መለኮታዊ ቃሉ ግን፥ በኢየሩሳሌም አምሳል የተጥራችው ሃገረ ኢትዮጵያና ፈሪሐ እግዚአብሔር ባደረባቸው ሕዝቦች ደስታና ሐሤት ያደርግባቸዋል።

ለምን ቢሉ እንደ ሰማእቱ እስጢፋኖስ፥ እያዘኑ፣ እየተጨነቁ፣ እየተበደሉ፣ እየታረዱና እየተገደሉ፤ ሰይፍና ጎመድ ይዘው አልዝመቱምና። እንደውም አብዝተ እንደ መዝሙረኛው ንጉሡ ዳዊት "ጠላቶቼ ሁልጊዜ ይሰድቡኛል፥ የሚያሳድዱኝም ተማማሉብኝ። አመድን እንደ እህል ቅሜአለሁና፥ መጠጤንም ከእንባዬ ጋር ቀላቅያለሁና" /መዝ 1028-9/ በማለት የዘመረውን ዝማሬ አብዝተው ዘመሩ እንጂ!!!

ታዲያ ንጉሣችንና አምላካችን ይታደገናል! ስለዚህ ደስታና ሐሤት የሚያደርግባቸው ሕዝቦች ስለሆንን ክብር ይመስግንልን  ለምላካችን!!!
 
                    ዋቢ፦
 
       2  አረብ ኒውስ

Saturday, November 9, 2013

የመድኀነ-ዓለም ወዳጅ ሆይ፦


የመድኅነ-ዓለም ወዳጅ ሆይ፦ አንተ የኢየሱስ ክርሰቶስ ወንጌል አምናለሁ ብለህ፥ የማዳኑን፣ የቤዛነቱን፣ የቸርነቱን፣ የምህረቱን፣ እንዲሁም የሁሉ ነገር ማሰሪያና መቋጫ የሆነውን የፍቅሩን ብዛት ቀመሰህ፤ ቃሉን ስትሰማ፣ ወንጌሉን ስታነበው፣ ልብህ በሐሴት እንደሚረካ አልጠራጠርም።

የመድኅነ-ዓለም ወዳጅ ሆይ፦ ታዲያ ልብህ በቃሉ የሚረሰርስና የሚረካ ከሆነ፥ ለአገልግሎት ስትዘጋጅ፤ ማለትም፦ ለማሰተማር፣ ለመስበክ፣ ለሕዝበ-ክርስቲያኑ ሆነ ለዓለም በሥነ-ጹሑፍ ስትገልጠው፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለም ካዳነበት ምስጢረ ሥጋዌ እያነፃፀርኸ፥ ነቢያቱን፣ ሐዋርያቱን፣ ሰማእታቱን፣ ቅዱሳን መልአክቱንና የጌታ እናቱን ቅድስት ድንግል ማርያምን፤ ተገቢውን ቦታ አለመስጠት፥ ለማሳነስ መሞከር፤ አትሞክር። ምክንያቱም በእርሱ ዘንድ ሁሉ እንደተፈጸመ እወቅ።

ምኑ እንደተፈጸመ ትል ይሆናል። ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን መድኃኒዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ፥ ለወዳጆቹ ለቅዱሳኑ የእርሱ የነበረውን፥ ሥልጣን፣ ኃይልን፣ የተለያዩ የመንፈስ ቅዱስ የፀጋ ስጦታዎች እንደሰጣቸው ልብ ይመን። እንግዲህ እነርሱ ከባለቤቱ የተቀበሉት ስጦታ ስለሆነ፤ ክብር ለሚገባው፥ ክበር መስጠት ተገቢ ነውና ነው።

የመድኅነ-ዓለም ወዳጅ ሆይ፦ ፍጹም የሆነ፥ የመንፈስ ቅዱስ የፀጋ ስጦታዎች ስለሆነ ነው። እነዚህ የፀጋ ስጦታዎች የተለያዩ ቢሆኑም፥ የማዳን፣ የመገሰፅ፣ የመፈወስ፣ የማስተማር፣ የመተርጎም፣ የመዘመር፣ የማመስገንና የተመስጦ፤ እርሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አንዴ ባርኮና አበዘቶ ስለሰጣቸው እንደሆነ ሁሌም ቢሆን ከሕሊናህ፣ ከልቦናህ፣ ከአእምሮህ፣ ከሃይማኖትህና ከእምነትህ ቃል አንፃር እየው።


Thursday, November 7, 2013

ኧረ ሃገር አለኝ!



ሃገር አለኝ፥ ኧረ ሃገር አለኝ!
ያውም ቅኝ ግዛት ያልገዛኝ፣
በጀግኖቿ ልጆች ደም ታሪክ  ያለኝ፣
የፍቅር ሃገር አብሲኒያዊነኝ።

ከያኔዎች መሪዎች ወኔና ጥንካሬያቸው፤
እስኪ አንዱን አጼ አይለስላሴን እናውሳቸው

ጀርመኖች በሁለተኛ ዓለም ጦርነት ሳለች፣
ወደ ኢትዮጵያ ንጉስ መልዕክት ላከች፣
ለሥራችን የሚሆን ሰራተኛ ስጡኝ አለች፣
አይሆንም ብላ ኢትዮጵያም መለሰች።

በሠራተኛ ሒሳብ ይወስዱና፣
ላልተገባ ሥራ ያቆሙና፣
ቁረጥ ፍለጥ ያስብሉና፣
እኛንም ያስቆጥሩን ነበርና።

Friday, October 25, 2013

“ስለ ኢትዮጵያ ዝም አንልም ግብረ ሶዶማዊነት በኢትዮጵያ የ666 አሰራር”

              "ግብረ ሶዶማዊነት በኢትዮጵያ" በሚል፦ መምህር ደረጄ ዘወይንዬ፤ በግብረ ሶዶማዊያኖች፥ ላይ ባደረገው ጥናታዊ ዳሰሳ፣ ከድምጸ ተዋህዶ የሬድዮ ፕሮግራም አዘጋጆች ጋር ባደረገው የቃለ መጠይቅ ቆይታ፥ እንዴት ወደ ግብረ ሶዶማዊነት ሕይወት እንደገቡ፣ በግብረ ሶዶማዊነት ሕይወታቸው ምን እንደሚመስል፣ ሥራዎቻቸውና እንቅስቃሴዎችቸውን፤ በተመለከተ ሰፋ ያለ፥ በተበራራና ግልፅ በሆኑ ቃላቶች፣ ግብረ ሶዶማዊያን ሕይወትና ተመክሮ በመነሳት፣ ስለ ግብረ ሰዶማውሪያን እንቅስቃሴ የሚያመለክትና ግንዛቤ የሚያስጨብጥ፣ ወደዚህ ሕይወት ለገቡት የመውጪያውና የማምለጫው በር፣ ወደዚህ ሕይወት ለመግባት ዳር ዳር ላሉ ደግሞ የደውል ምልክት ነውና። ታዲያ በግብረ ሶዶማዊያን ዙርያ የቀረበው በተጨባጭ ሁናቴ በመረጃና በማሰረጃ ስለሆነ ግንዛቤ እንዳስጨበጠን የታመነ ሃቅ ነው!


“ስለ ኢትዮጵያ ዝም አንልም ግብረ ሶዶማዊነት በኢትዮጵያ የ666 አሰራር” የሚለውን በደረጀ ነጋሸ ዘወይንዬ አዘጋጅና አቅራቢነት በቪዲዮ ወምስል ካቀረበልን ግብረ ሶዶማዊያን መካክል አንዱና ዋነኛ የሆነው አብይ (ኤሊያና) ስለራሱና ስለ ጓደኞቹ ስል ግብረ ሶዶማዊያን ሕይወታቸው ምን እንደሚመስል፣ በእውነተኛ ታሪካቸው በተፃፈው መፅሐፍ አማካይነት ስለ ግብረ ሶዶማዊነት ሲናገር እንዲህ ነው የሚለው፦

* “ግብረ ሰዶማዊነት፥ እንደ ማግኔት ነው! አንድ ጊዜ ስቦ ካጣበቀ በኋላ የማይለቅ” ነው ብሎ ይገልፀዋል። (መፅሐፍ፦ የሰዶም ነፍሳት፥ ሙሉ በሙሉ እውነተኛ ታሪክ)

Tuesday, October 15, 2013

“እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም”



(እውነት ነው እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም!!! እናሳ ከወለደች በኃላስ እንዴት አወቃት?)

አቤቱ ጌታችን ሆይ፦ ተቀዳሚ ተከታይ ስለ ሌለው ስለ ልጅህ ስለ ወደዳጅህ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ አማኑኤል ብለህ ይቅርታህን ከኛ አታርቅ፤ መሐላህንም አታፍርስ በእውነት ያለሐሰት።

በአብ በመንፈስ ቅዱስ ህልውና ሆነው የሚኖር፣ ኢየሱስ ክርስቶስ። በሱም አብ መንፈስ ቅዱስ ህልውና ሆነው የሚኖሩ። ልቦናው አብ፣ ያንደበቱም ትንፋሽ መንፈስ ቅዱስ፤ የሚሆን ኢየሱስ ክርስቶስ። እርሱም የአብ የመንፈስ ቅዱስ ቃላቸው የሚኖር ኢየሱስ ክርስቶስ።

በልዕልና ሳለ በመሠረት ያለውን የሚያይ። በውነት ከሰማይ በቸርነቱ ወርዶ ክብርት ድንግል ከምትሆን ከእመቤታችን በሰው ሥጋ ተወለደ። ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀኗ ተወስኖ፣ ልጅነትን ሰጥቶ፤ በሥጋው ወገኖቹን ያደርግ ዘንድ።

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስም ልደቱ ነገር እንዲህ ነው፦ እናቱ እመቤታችን ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ ሳይገናኙ በግብረ መንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች። ድንጋሌ ሥጋ ድንጋሌ ነፍስ ስላት። ከማየት፣ ከመስማት፣ ከመናገር፣ ከመዳሰስ፤ ድንግል ስትሆን።

ዕጮኛዋ ዮሴፍ ግን ደግ ሰው ነውና ሊገልጣት፣ ሊያጣላት አልወደደም። ሰውሮ ሊያኖራት ወደደ እንጂ! ይህንንም ሲያስብ እነሆ የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ታየው፣ በሕልምም ተነጋገረው።

የዳዊት ልጀ ዮሴፍ ሆይ ዕጮኛህ ማርያምን መቀበል አትፍራ። ከሷ የሚወለደው በግብረ መንፈስ ቅዱስ ነውና። እነሆ፦ ወንድ ልጅ ትወልዳለች ስሙንም ኢየሱስ (መድኃኒት) ትለዋለች። እሱ ወገኖቹን ከኃጢአታቸው ፍዳ ያድናቸዋልና።

ይህ ሁሉ የተደረገው፥ ነቢይ ከእግዚአብሔር አግኝቶ፤ እነሆ፦ ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ይሉታል ብሎ የተናገረው ይደርስ፣ ይፈጸም ዘንድ ነው።

አማኑኤል ማለት እግዚአብሔር ከኛ ጋር የሆነ ማለት ነው። ዮሴፍም ከእንቅልፉ ተነሥቶ የእግዚአብሔር መልአክ እንዳዘዘው አደረገ። ዮሴፍም ለድንግልናዋ ሰገደ። ለንጽሕናዋ፣ ለቅድስናዋም። ተገዛ። ዕጮኛው የምትሆን ማርያምንም ወሰዳት። በኵር ተብሎ የተጠራ ልጅዋን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም። (ጻድቁ ዮሴፍ እመቤታችንን ድንግል ማርያም በድንግልና ጸንሳ በድንግልና የመውለዷ ምስጥር፣ የኢየሱስ ክርስቶስ እናት መሆኗን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም፣ አልተረዳም ነበር።) /ድርሳነ ማሕየዊ ምዕ 113-38/



Monday, October 14, 2013

ምርጥና እጹብ ድንቅ አስር የአብው ብሂላዊ ምክር፦



1. ትግል፣ ተናና መከራ ከሌሉ የድል አክሊል፤ ጠላት ከሌለ ድል ማድረግ አይቻልም። /ታላቁ ባስልዮስ/

2. በመንፈሳዊ መንገድ ውስጥ ዝግ ብለህ አትጓዝ። በጎዳና ላይ በምትመለከታችው ትዕይንቶች አማካይነት አትማረክ፤ አትቁምም ጠላቶችህም ሆኑ ወዳጆችህም ያሰናክሉህ ዘንድ አትፍቀድላቸው። /አቡነ ሺኖዳ/

3. የከበሩ አባቶቻችን ልጆች ልትሆኑ ከወደዳቹሁ እነርሱ የጻፉትን (ያስተማሩት) እንጂ ምንም ሌላ አትመኑ። /ቅዱስ አትናቴዎሰ/

4. ጠላት በበዛበት ቦታ የምኖር ከሆነ ብርቱ ወታድር እሆናለሁ። /አባ ጴሜን/

5. ፍቅር፦ በእውነት ሰማያዊ ኀብስትና የአእምሮ ምግብ ነው። /ቀለሜንጦስ ዘእስክንደርያ/

6. ከሰው ተለይቶ ወንድሙን የሚመክር ሰው እነሆ የፍቅሩን ጽናት ብዛት ያስረዳል፤ ባልንጀሮቹ ፊት የሚነቅፈው ግን የቅናቱን ጽናት ያስረዳል፣ የምቀኝነቱን ጽናት ያስረዳል። /ማር ይስሐቅ/

7. ፍቅር፦ መያዣ የሌለውን የሰው ልብ አስሮ ለመሳብ የሚያገለገል የሠላም መንገድ ነው። /አንገረ ፈላስፋ፤ ሊቀ መዘምራን ሞገስ ዕቁበ ጊዮርጊስ/

8. አሁን የምንኖራት ሕይወት ምን ያህል ውድ እንደሆነች ልታውቅ ትወዳለህን? ይህች ሕይወት ለዘለዓለማዊ ሕይወታችን መሠረት የትግል ዐውድማ፣ እንዲሆም በገነት ያለችውን አክሊል የምትሰጥ ናት። /ዮሐንስ አፈወረቅ/

9. ልማት ማለት መሬትን መቆፈር ብቻ አይደለም። የሰውን ልቦና በትምህርተ ወንጌል ቆፍሮ ማለምለም፣ በሰው አእምሮ ፍቅርና ስምምነት መዝራትና መትክል፣ ሰውን ከስህተት መመለስና ማስተማር፤ ከልማቶች ሁሉ የበለጠ ነው። /ብፁዕ አቡነ ጳውሎስ/

10. የትሕትና ከፍታ እጅግ ታላቅ ነው፤ የመታበይ ጥልቀት ደግሞ እጅግ ጥልቅ ነው፤ የመጀመረያውን እንድትከተል፥ ወደዚህኛው ደግሞ እንዳትወድቅ እመክርሃለሁ። /አባ ኤስድሮስ/


ዋቢ መፅሐፍ ብሂለ አበው 2005 @ማኅበረ ቀዱሳን