Saturday, November 9, 2013

የመድኀነ-ዓለም ወዳጅ ሆይ፦


የመድኅነ-ዓለም ወዳጅ ሆይ፦ አንተ የኢየሱስ ክርሰቶስ ወንጌል አምናለሁ ብለህ፥ የማዳኑን፣ የቤዛነቱን፣ የቸርነቱን፣ የምህረቱን፣ እንዲሁም የሁሉ ነገር ማሰሪያና መቋጫ የሆነውን የፍቅሩን ብዛት ቀመሰህ፤ ቃሉን ስትሰማ፣ ወንጌሉን ስታነበው፣ ልብህ በሐሴት እንደሚረካ አልጠራጠርም።

የመድኅነ-ዓለም ወዳጅ ሆይ፦ ታዲያ ልብህ በቃሉ የሚረሰርስና የሚረካ ከሆነ፥ ለአገልግሎት ስትዘጋጅ፤ ማለትም፦ ለማሰተማር፣ ለመስበክ፣ ለሕዝበ-ክርስቲያኑ ሆነ ለዓለም በሥነ-ጹሑፍ ስትገልጠው፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለም ካዳነበት ምስጢረ ሥጋዌ እያነፃፀርኸ፥ ነቢያቱን፣ ሐዋርያቱን፣ ሰማእታቱን፣ ቅዱሳን መልአክቱንና የጌታ እናቱን ቅድስት ድንግል ማርያምን፤ ተገቢውን ቦታ አለመስጠት፥ ለማሳነስ መሞከር፤ አትሞክር። ምክንያቱም በእርሱ ዘንድ ሁሉ እንደተፈጸመ እወቅ።

ምኑ እንደተፈጸመ ትል ይሆናል። ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን መድኃኒዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ፥ ለወዳጆቹ ለቅዱሳኑ የእርሱ የነበረውን፥ ሥልጣን፣ ኃይልን፣ የተለያዩ የመንፈስ ቅዱስ የፀጋ ስጦታዎች እንደሰጣቸው ልብ ይመን። እንግዲህ እነርሱ ከባለቤቱ የተቀበሉት ስጦታ ስለሆነ፤ ክብር ለሚገባው፥ ክበር መስጠት ተገቢ ነውና ነው።

የመድኅነ-ዓለም ወዳጅ ሆይ፦ ፍጹም የሆነ፥ የመንፈስ ቅዱስ የፀጋ ስጦታዎች ስለሆነ ነው። እነዚህ የፀጋ ስጦታዎች የተለያዩ ቢሆኑም፥ የማዳን፣ የመገሰፅ፣ የመፈወስ፣ የማስተማር፣ የመተርጎም፣ የመዘመር፣ የማመስገንና የተመስጦ፤ እርሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አንዴ ባርኮና አበዘቶ ስለሰጣቸው እንደሆነ ሁሌም ቢሆን ከሕሊናህ፣ ከልቦናህ፣ ከአእምሮህ፣ ከሃይማኖትህና ከእምነትህ ቃል አንፃር እየው።


No comments:

Post a Comment