Tuesday, November 19, 2013

የተቃውሞ ሰልፍ በሮም ከተማ



       



       የተቃውሞ ሰልፍ በሮም ከተማ የሳዑዲ አረቢያ ኤንባሲ፤ በመሄድ የተቃውሟችን ድምፃችንን ለማሰማት፥ በሰልፍ ላይ ትውለደ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊን፣ ሃገር ቢለየንም ደማችን አንድ ነው ብለው ትውልደ ኤርትራውያንና ኤርትራዊያን፣ እንዲሁም በሰልፍ ላይ የተካፈሉ በርከት ያሉ የኢትዮጵያዊያን ወዳጆች ጣልያዊያን፤ አብረን ነበርን። ለሦስት ሰዓታት ያህል፥ በሳዑዲ ሃገር፦ በዜጎቻችን ላይ የሳዑዲ ሕዝብና መንግስት የሚደርሱባቸውን ጥቃት፣ እንግልት፣ ድብደባ፣ ግድያ፤ በጥብቅ ተቃውመን፤ ለዓለሙ ሕዝብ በአጽኖት እንዲመለከተውና እንዲከታተለው እኛ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያን ወዳጆች በሙሉ፤ ተቃውሟችንን በጋለ ሃገራዊ የፍቅር ስሜት፣ በሠላማዊ መንገድ፤ በሚገርምና በሚያስደንቅ ሁኔታ አሰምተናል።

ይህንን ሃገራዊና የማንንታችንን ጥያቄ በመጠየቅ፥ ላስተባበሩና በተቃውሞ ሰልፍ ላይ የታደሙትን፣ እንዲሁም የሮም ከተማ አስተዳደርን እጅግ ከፍ አድርጌ ከልብ አመሰግናቸዋለሁ።


በተቃውሞ ሰልፍ ላይ የተፈቀደልን የሰዓት ሁኔታ ከ8-10 ሰዓት ነበር። ነገር ግን የሮም ከተማ አስተዳደር ከወሰነልን ሰዓታት ብንዘገይም ምንም ዓይነት በፖሊሶች ምላሽ በቃቹ ሂዱ አላሉንም ነበር። እንደዚህም ቢሆን የኛ ሰው ግን አላስፈላጊ ነገሮችን በማድረግ፣ በፖሊሶች ላይ ወረቀቶችን በመጨማደድ የተወሰኑ ሰዎች ወርውረዋል፤ ቢሆንም ግን ተገቢያቸው አነበረም የዚህ ዓይነት ድርጊት። በአፀፈው ፖሊሶች ምንም ዓይነት እርምጃ አለመውሰዳቸው ያስመሰግናቸዋል!

ይህ እንዳለ ሆኖ አንዳንድ ሰዎች ስሜታቸው መቆጣጠር ካለመቻላቸው የተነሳ የተቃውሞ ሰልፍ ካለቀ በኋላ ከሳዑዲ አረቢያ ኤንባሲ እስከ ኢትዮጵያ ኤንባሲ በመሄድ ላይ እያሉ ነበር፤ ፖሊሶች መጥተው፦ “የተሰጣቹ ሰዓት በማለቁ ወደየመጣቹበት ሂዱ የሚል መልእክት አዘልና መንገድ ሳትዘጉ እግረኛ በሚሄድበት መንገድ ተጓዙ” ቢሉም መንገድ የጀመሩት በተቃወሞ ሰልፍ ላይ የነበሩ ሰዎች፦ የፖሊሶችን ወደየመጣቹበት ሂዱ የሚል መልእክት አዘልና መንገድ ሳትዘጉ እግረኛ በሚሄድበት መንገድ ተጓዙ ያሉትን ባለመትግበራቸው ምክንያት እሰጥ-እገባ ውስጥ ለመግባት ትንሽ ቀርቷቸው ነበር። 

ፖሊሶቹም፦ ጭማሪ የፖሊሶ ኃይል በማጠናከር፥ ተጓዦችን ለመበተን የመጣው የፖሊሶ ኃይል የሚጓዙበትን መንገድ በፖሊሶች በማጠር፣ መንገዱን በመዘጋት፣ በክብ መሐል ላይ በማስገባት፣  ̋በቃቹ ወደየመጣቹበት ሂዱ˝ በማለት በድጋሚ አስረግጠው ተናገሩ።

        እሰጥ-እገባው እየቀጠለ በሚሄድበት ጊዜ ከላይ ከስማይ የዝናብ ካፊያ መጣል ጀመረ፥ ሕዝቡም ተበተነ፣ ሁሉም ወደየመጣበት ተመለሰ።

        እኔ ግን እንደዚህ ያህል ከፖሊሶች ትግዕስትና ነፃነት ተችረን ሳለ፥ ይሁሉ እሰጥ-እገባው ለመግባት ለምን አስፈልጎ ይሆን?  ትላንትናም ቢሆን (በተቃውሟችን ላይ ከዚህ የወጣ ዓላማን ተገን በማድረግ እርስ በራሳችን እንዳንወቃቀስና በዓለሙ ሕዝብ እይታ ትዝብት ውስጥ እንዳንገባ አጥብቄ አደራ እላለሁኝ።) ብዬ ነበር። ግን ያ የዝናብ ካፊያ በመጣሉ ተመስገን አልኩኝ፤ ምክንያቱም፦ የዝናብ ካፊያ ባይጥል ኖሮ ከዛ በኋላ የሚደርሰው ነገር ማሰብ ቀላል ነውና።

አሁንም ቢሆን በተለያየ ዓለማት ያላቹ ውድ ወገኖቼ ሆይ፦ በሳዑዲ ሃገር፣ በዜጎቻችን ላይ የሳዑዲ ሕዝብና መንግስት የሚደርሱባቸውን፥ ጥቃት፣ እንግልት፣ ድብደባና ግድያ፤ በጥብቅ ለመቃውም የተቃውሞ ሰልፍ ስትወጡ፤ እርስ በራሳቹ እንዳትወቃቀሱና በዓለሙ ሕዝብ እይታ ትዝብት ውስጥ እንዳያስገባን አጥብቄ አደራ እላለሁኝ።

በተረፈ፥ በሳዑዲም ይሁን በተለያየ ዓለማት፣ እንዲሁም በሃገራች በኢትዮጵያ ያሉ ዜጎቻችን ወደነፃነት ሕይወት ይመልሳቸው ዘንድ ፈጣሪ እግዚአብሔር ይርዳቸው፤ ሠላምና አንድነት ለኢትዮጵያ!!!




እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክልን!

19/11/2013

1 comment: