Thursday, November 7, 2013

ኧረ ሃገር አለኝ!



ሃገር አለኝ፥ ኧረ ሃገር አለኝ!
ያውም ቅኝ ግዛት ያልገዛኝ፣
በጀግኖቿ ልጆች ደም ታሪክ  ያለኝ፣
የፍቅር ሃገር አብሲኒያዊነኝ።

ከያኔዎች መሪዎች ወኔና ጥንካሬያቸው፤
እስኪ አንዱን አጼ አይለስላሴን እናውሳቸው

ጀርመኖች በሁለተኛ ዓለም ጦርነት ሳለች፣
ወደ ኢትዮጵያ ንጉስ መልዕክት ላከች፣
ለሥራችን የሚሆን ሰራተኛ ስጡኝ አለች፣
አይሆንም ብላ ኢትዮጵያም መለሰች።

በሠራተኛ ሒሳብ ይወስዱና፣
ላልተገባ ሥራ ያቆሙና፣
ቁረጥ ፍለጥ ያስብሉና፣
እኛንም ያስቆጥሩን ነበርና።


ከዘር ጨፍጫፊዎች መካክል፣
እጃችን እንዳያርፍ በመሐል፣
ከተወቃሽነት ትውልድ ይድን ዘንድ ብለዋል፣
ከለከሉ የያኔው ንጉስ በማስተዋል።

ዛሬ ዛሬማ እነማን ፓርቲዎች ከለከሉ፣
ምን ችግር አለው እያሉ ለጥቅም ሲሉ፣
በሕጋቸው ውስጥ ሁሉን ተቀበሉ፣
ሕዝቡማ ሲጎዳ  መች አስተዋሉ?

የሃገሬ ልጆች፥ እሪታቸው በዛ፤
የመሪዎች ቦታ እየተንዛዛ።

አንድና አንድ ነው እሪታችን፣
በውጭ ዓለማትም በሃገርም ይሁን፣
እንፈልጋለን ሠላም ተከበሮ የቆየልን፣
መሪዎች ሆይ፦ ድምጻችን ሱሙልን።

እንግልት በዛና፣
ጠያቂ የሌላቸው ሆንንና፣
ደማችንን በመሬት ፈሰሱና፣
ኧረ ማን ይጠይቃቸው እንላለንና።

ሃገር አለኝ! ኧረ ሃገር አለኝ!
መሪዎች የነበሯት ስመ-ጥሩ የሚያሰኝ።

የቱን ጠርቼ የቱን ልተወው፣
ለጠላቶች ክፍተት የማይተው፣
እንደ ንስር ዓይን ሁሉን የሚቃኘው፣
በዛሬ ጊዜ የኢትዮጵያ መሪ የት ላግኘው።

ሃገር አለኝ! ኧረ ሃገር አለኝ!
ያውም ቅኝ ግዛት ያልገዛኝ፣
በጀግኖቿ ልጆች ደም ታሪክ  ያለኝ፣
የፍቅር ሃገር አብሲኒያዊነኝ።


(ማስታዎሻ፦ በተለያየ ዓለማት ደማቸው በግፍና በጭካኔ ተገለው ጠያቂ መሪ ተከራካሪ ላላገኙ፣ ደማቸውን በመሬት ፈሶ ለቀረ በሙሉ ይሁንልኝ።)


፳፰/፪/፳፻፮ (7/11/2013)

No comments:

Post a Comment