Showing posts with label ብሒለ አበው. Show all posts
Showing posts with label ብሒለ አበው. Show all posts

Sunday, November 23, 2014

መልካምና ክፉ ልጅ


   በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ሜን!


ልጅህ፥ ክፉ ከሆነ፦

* እንደ ቃየል በቅናት ካደገ የገዛ ወንድሙን ይገድላል። (ዘፍ ፬፥፭)

* እንደ ካም ካደገ ያንተኑ ሃፍረት ይገልጥብሃል። (ዘፍ ፱፥፳፩-፳፪)

* እንደ ዲና ካደገች ሂዳ ከጠላቶችህ ትወዳጃለች። (ዘፍ ፴፬፥፩)

* እንደ ዔሳው ካደገ ምቀኛ ይሆንብሃል። (ዘፍ ፲፯፥፵፩-፵፭)

* እንደ ይሁዳ ልጆች ካደገ የከፋ ይሆንብሃል። (ዘፍ ፴፰፥፩-፲፩)

* እንደ ሮቤል ካደገ ሚስትህን ይቀማሃል። (ኩፍ ፳፰፥፴፭-፵፬)

* እንደ አፍኒንና ፊንሐስ ካደገ ታቦት ሻጭ ይሆንብሃል። (፩ኛ ሳሙ፪፥፲፪)

* እንደ አምኖን ከደገ የገዛ ኅህቱን ይደፍርብሃል። /፪ኛ ሳሙ ፲፫፥፩-፲፱)

* አንደ አቤሴሎም ካደገ አንተንም ያሳድድሃል። (፪ኛ ሳሙ ፲፯፥፳፩-፳፬)

ልጅህ፥ መልካም ከሆነ፦ 

* አንደ ሴምና ያፌት ካደገ ሃፍረትህን ይደብቅልሃል። (ዘፍ ፱፥፳፫)

* አንደ ዮሴፍ ካደገ በችግርህ ደራሽ ይሆንልሃል። (ዘፍ ፴፱፥፯-፳፫)

* እንደ ይስሐቅ ካደገ ታማኝ ሆኖ ራሱን ይሰዋል። (ዘፍ ፳፪፥፱)

* እንደ ሳሙኤል ካደገ የእግዚአብሔር ሰው ይሆንልሃል። /፩ኛ ሳሙ ፫፥፲፯-)

* እንደ ዳዊት ካደገ የአገርህን ጠላት ያጠፋልሃል፤ በሰውም በእግዚአብሔር ፊት የተወደደ ይሆንልሃል። /፩ኛ ሳሙ ፲፯፥፴፬-፶፬)

"ልጆች ኖሩህ (በክርስቶስ ፍቅር) ምከራቸው፤ ከሕፃንነታቸው ጀምረህ ትሕትናን አስተምራቸው።" (ሲራ ፯፥፳፫)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ ክብር ለድንግል ማርያም!

ምንጭ፦ ዛክ ኢትዮጵያ

Monday, May 19, 2014

ቅን ትችት፥ ለሚቀበለው ሠው፦


      ቅን ትችት እንዴት ደስ ይላል፣ ቅን ተቃውሞም ልብን ያረሰርሳል በንዴት ለጦፈውም፣ በኃይል ለተነሳው በቃ፥ ብሎ ቁርጥ-ውሳኔ ለቆረጠው ኅሊናው፥ እንዲሟገተውና ወደ ራሱ እንዲመለከት ያግዘዋልከቀየሰ ት ጐዳናም ይታደገዋል!።

 
 

 

Friday, December 20, 2013

ሥራህን ሥራ፦ በብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ



ሥራህን ሥራ፦ ጌታ ለእያንዳንዱ ሰው ሥራ ሰቶታል፤ ያንን መስራት የእሱ ፈንታ ነው። ቢቻለው እሱን ማገድ የዲያብሎስ ሥራ ነው። በርግጥ ሥራውን እግዚአብሔር እንደሰጠህ ያህል ሰይጣን ሊያግድህ ይጥራል። ሌላ ነገር በበለጠ ደስ የሚያሰኝ ሊያቀርብልህ ይጥራል፤ በዓለማዊ ተስፋዎች ያባብልሃል። የሃሜት ጎርፍ ያስወርድብሃል። ደራሲያን እንዲጠይቁህ፣ እጅግ ስመጥር ሰዎችም በክፉ እንዲናገርብህ ይጠቀምባቸዋል።

ጲላጦስ፤ ሔሮድስ፤ ሐናንያ፤ ቀያፋ ሁሉም በአንተ ላይ ያድማሉ። ይሁዳም በአጠገብህ ቆሞ በሰላሳ ብር ሊሸጥህ ይከጅላል። ይሄ ሁሉ የደረሰብህ ሰይጣን በዚህ ከስራህ ሊስብህና እግዚአብሔርን ከመታዘዝ ሊያሰናክልህ መሆኑን ልትገነዝብ አትችልምን?
ሥራህን ሥራ፦ አላማህ እንደ ኮከብ የጸና ይሁን ተወው አለም እንደፈለገው ይነታረክ ይጨቃጨቅ፡፡ አንበሳው ሲያጋራ ፍንክች አትበል የሰይጣንን ውሻዎችን ለመውገር አትቁም፡፡ ጥንቸሎችን በማባረር ጊዜህን አታጥፋ

ሥራህን ሥራ፦ ዋሾች ይዋሹ፣ ጠበኞች ይጣሉ፣ ማህበሮችም ይወስኑ፣ ደራሲዎችም ይድረሱ፤ ሰይጣንም የፈለገውን ያድርግ። አንተ ግን ምንም ነገር እግዚአብሔር የሰጠህን ሥራ ከመፈፀም እንዳያግድህ ተጠንቀቅ።

ሥራህን ሥራ፦ ገንዘብ እንድታተርፍ አልተላክህም፣ እንድትበለጽግም አልታዘዝክም፣ ለክብርህ ተከላከል ብሎ አልተነገረህም፤ ሰይጣን አገልጋዮቹ የሚነዙትን የሐሰት ወሬ እንድታስተባብል አልተጠየቅህም እነኚህን ሁሉ ነገሮች ብታደርግ ሌላ ሥራ ልትሰራ አትችልም፤ ይህም ብቻ ሳይሆን ለራስህ እንጂ ለጌታ አልሰራህም።

ሥራህን ሥራ፦ አላማህ እንደ አለት የፀና ይሁን፣ ጥቃት ይደርስብህ፣ ትበደል፣ ትሰደብ፣ ትታማ፤ ትቆስልና ትናቅ ይሆናል። አንተ ግን በፀና ውሳኔ የማያወላውል ቅናት በመጨረሻ ላይ ፀንተህየሰጠኽኝን ሥራ ፈፀምኩ ሃይማኖትንም ጠበቅሁ” ለማለት እስክትችል ድረስ የሕይወትህን አላማና የተፈጠርክበትን ግብ ተከትል።

  --------------------------------------------------------------------------------
        (ምንም ብታደርጉ ሠዎች *በአራቱም አቅጣጫ* ከማውራት ስለማይመለሱ ዝም ብላቹ ሥራችሁ ላይ ትኩረት አድርጉ!!!)
   ---------------------------------------------------------------------------------

Monday, October 14, 2013

ምርጥና እጹብ ድንቅ አስር የአብው ብሂላዊ ምክር፦



1. ትግል፣ ተናና መከራ ከሌሉ የድል አክሊል፤ ጠላት ከሌለ ድል ማድረግ አይቻልም። /ታላቁ ባስልዮስ/

2. በመንፈሳዊ መንገድ ውስጥ ዝግ ብለህ አትጓዝ። በጎዳና ላይ በምትመለከታችው ትዕይንቶች አማካይነት አትማረክ፤ አትቁምም ጠላቶችህም ሆኑ ወዳጆችህም ያሰናክሉህ ዘንድ አትፍቀድላቸው። /አቡነ ሺኖዳ/

3. የከበሩ አባቶቻችን ልጆች ልትሆኑ ከወደዳቹሁ እነርሱ የጻፉትን (ያስተማሩት) እንጂ ምንም ሌላ አትመኑ። /ቅዱስ አትናቴዎሰ/

4. ጠላት በበዛበት ቦታ የምኖር ከሆነ ብርቱ ወታድር እሆናለሁ። /አባ ጴሜን/

5. ፍቅር፦ በእውነት ሰማያዊ ኀብስትና የአእምሮ ምግብ ነው። /ቀለሜንጦስ ዘእስክንደርያ/

6. ከሰው ተለይቶ ወንድሙን የሚመክር ሰው እነሆ የፍቅሩን ጽናት ብዛት ያስረዳል፤ ባልንጀሮቹ ፊት የሚነቅፈው ግን የቅናቱን ጽናት ያስረዳል፣ የምቀኝነቱን ጽናት ያስረዳል። /ማር ይስሐቅ/

7. ፍቅር፦ መያዣ የሌለውን የሰው ልብ አስሮ ለመሳብ የሚያገለገል የሠላም መንገድ ነው። /አንገረ ፈላስፋ፤ ሊቀ መዘምራን ሞገስ ዕቁበ ጊዮርጊስ/

8. አሁን የምንኖራት ሕይወት ምን ያህል ውድ እንደሆነች ልታውቅ ትወዳለህን? ይህች ሕይወት ለዘለዓለማዊ ሕይወታችን መሠረት የትግል ዐውድማ፣ እንዲሆም በገነት ያለችውን አክሊል የምትሰጥ ናት። /ዮሐንስ አፈወረቅ/

9. ልማት ማለት መሬትን መቆፈር ብቻ አይደለም። የሰውን ልቦና በትምህርተ ወንጌል ቆፍሮ ማለምለም፣ በሰው አእምሮ ፍቅርና ስምምነት መዝራትና መትክል፣ ሰውን ከስህተት መመለስና ማስተማር፤ ከልማቶች ሁሉ የበለጠ ነው። /ብፁዕ አቡነ ጳውሎስ/

10. የትሕትና ከፍታ እጅግ ታላቅ ነው፤ የመታበይ ጥልቀት ደግሞ እጅግ ጥልቅ ነው፤ የመጀመረያውን እንድትከተል፥ ወደዚህኛው ደግሞ እንዳትወድቅ እመክርሃለሁ። /አባ ኤስድሮስ/


ዋቢ መፅሐፍ ብሂለ አበው 2005 @ማኅበረ ቀዱሳን

Monday, June 17, 2013

አስሩ ምርጥ ብሒላዊ ምክር፦

1 ሐሜት፦ ያለ መሣሪያ ሰውን መግደል ነው።

2 ማጉረምረም፦ ባገኙት በቃኝ ብሎ አለማመስገን ነው።

3 ቁጣ፦ ከስድበ የሚያደርስ የክፉ አድራጎት መሠረት ነው።

4 ብስጭት፦ የተበሳጩበትን ነገር ሳይሆን ተመልሶ ራስን የሚጎዳ መርዝ፣ ከክህደት የሚያደርስ የኃጢያት     ምንጭ፤ ጭንቀትን የሚያነድ ትንሽ ክብሪት ነው።

5 መዋሸት፦ እውነተኛ ሠው ሳይታዩ የሚጎዱበት ረቂቅ የሰይጣን ጦር ነው።

6 መርገም፦ አቅም ሲያን ወደ ላይ የሚወረወር የደካማ ሰዎች ቀስት ነው።

7 መሳደብ፦ ህሊናን የሚያቆስል ቁስሉ ቶሎ የማይድን አቅም የሌላቸው ሰዎች ዱላ ነው።

8 ዋዛ ፈዛዛ፦ በስልት የሚቃኙት የሥራ ፈቶች ገበና ነው።

9 የማይገባ ሳቅ፦ ሐላፊ አገዳሚውን የሚያጠመዱበት የአመንዝራዎች ወጥመድ ነው።

10 መሳለቅ ፦ በአካል ጉዳተኛ ሰው ላይ የሚዘበቱበት የመርገም ስንቁ ወግ ነው።

ዋቢ መፅሐፍ ፦ ያለ ጭንቀት የመኖር ምስጢር

Sunday, January 27, 2013

“ቁጣንና ሌሎችንም አስመልክቶ የቅዱስ ኤፍሬም ተግሣጽ”


      "አንተ መንፈሳዊ ተፈጥሮ" አለህ። ነፍስህም የእግዚአብሔር አርዓያና አምሳል ናት። እናም ከሰው ሁሉ ጋር በፍቅር በመኖር የእግዚአብሔር አርዓያ የሆነችውን ነፍስህን አክብራት። በምትኖርባቸው ዘመኖችህ ሁሉ በተቻለህ መጠን ሰውነትህን ከቁጣ ጠብቅ። ያለበለዚያ አንተን ወደ ሲኦል ታወርድሃለች፤ ጎዳናዎቿም ወደ ገሃነም የሚያመሩ ናቸው። እናም ቁጣን በልብህ አታኑራት መራርነትንም በነፍስህ አታሳድር በነፍሰህ ላይ አንዳች ሥልጣን የለህምና ነፍስህን መልካም በማድረግ ጠብቃት

 

አንተ በእግዚአብሔር ደም ወደ እርሱ ቀርበሃል በክርስቶስ ሕማምም ድነኀል፤ አንተ በፈንታህ ለኃጢአት ሥራዎች የሞትክ ትሆን ዘንድ ስለአንተ መተላለፍ እርሱ ሞቷል አይሁድ በመዘበት በፊቱ ላይ ምራቃቸውን ሲተፋበት መታገሡ ሰዎች ቢያፌዙብህ እንኳ እንድትታገሣቸው አርአያ ሊሆንህ ነው መራራና ሆምጣጣ የሆነውን ወይን መጎንጨቱ ከቁጣ ትሸሽ ዘንድ ነው በጅራፍ ተገርፎ በሰንሰለት ታስሮ መጎተቱ ስለጽድቅ ስትል መከራን እንዳትሰቀቅ ነው

   ስለእውነት አንተ የእርሱ አገልጋይ ባሪያው ከሆንክ ቅዱስ የሆነውን ጌታህን ፍራው ስለእውነት አንተ የእርሱ እውነተኛ ደቀመዝሙር ከሆንክ የመምህርን ፈለግ ተከተል የክርስቶስ ወዳጅ ትባል ዘንድ ባልንጀራህ በአንተ ላይ ቢሳለቅ ታገሠው ከመድኃኒዓለም የተለየህ እንዳትሆን በሰው ላይ ቁጣህን አትግለጥ